Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መዉሊድን አላከብርም!


መዉሊድን አላከብርም!
መውሊድ በኢስላም ውስጥ መሰረት የሌለው፤ ሰሀቦችም ይሁኑ ታቢዒዮች የማያወተቁት የኀያላ ዘመን ቢድአ ነው።
አዳዲስና መጤ ከሆኑ አመለካከቶችና አምልኮዎች እራስን ማላቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በዲን ዉስጥ አዲስ መጤ ነገር ሁለ ቢድዓ ነዉ፡፡ ቢድዓ ደግሞ የተወገዘ ነዉ፡፡ መልዕክተኛዉ እንዲህ ብለዋል
‹‹በዚህ በጉዳያችን (በዲናችን) ከእርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ (ስራው) ተመላሽ ነው።›› ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡
በሌላ ተመሳሳይ ሀዲስ ፡-
‹‹ትዕዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ (ስራው) ተመላሽ ነው።›› ሙስሊም ከዓኢሻ ዘግበውታል፡፡
Ø ኢስሊም የተሟላ በመሆኑ ምንም አይነት ጭማሪን አይቀበልም፡፡የተላለፈልንን ሱና ብቻ ብንተገብር ተጠቃሚዎች እንሆናለን፡፡ ታላቁ ሰሀቢይ ኢብን መስዑድ አንዲህ ብለዋል፡-
"ተከተሉ! ቢድዓንም አትፍጠሩ! ሱና በቂያችሁ ነውና!!" ፡፡
ሁዘይፋ ኢብኑል የማን ደግሞ እንዲህ ይላል፡-
‹‹የመልዕክተኛው ሰሃቦች ባልሰሩት ማንኛውም የዒባዳ ተግባር አምልኮን አትፈፅሙ! የመጀመሪያዎቹ ለመጨረሻዎቹ ምንም የተዉት ነገር የለም!›› አቡ ዳዉድና ሌሎች ዘግበውታል፡፡