Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እህቴ ሆይ ሂጃብ ከማረግ የከለከሉሽ ስህተቶችሽ



እህቴ ሆይ ሂጃብ ከማረግ የከለከሉሽ ስህተቶችሽ
  1. “እምነት ሂጃብ ስለለበሱ ሳይሆን ዋናው ከልብ መስተካል ነው......” ከየት አመጣሽው? በእርግጥ የሰው ልጅ ሙሉ አይደለም ይሄ ስህተትሽን ለመሸፈን የመጣ ተራ ምክንያት ነው:: በእውነት በልቡ የተስተካከለ በድርጊቱ ይስተካከላል 
  2.  አንዳንዴ ደግሞ “እኔ አላህና መልክተኛውን እወዳለሁ ለመውደዴ የግድ ሂጃብ መልበስ አይጠበቀኝም....” ያንቺ ሃሳብ ነው?ወይስ የቁራአንና የሐዲስ? አላህ እንዲህ ይላል 
    “በላቸው አላህን የምትወዱ ከሆነ ተከተሉኝ አላህ ይወዳችኋልና ኃጢያቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና አላህ መሀሪ እና አዛኝ ነው::”(አል-ኢምራን 31)
    አዎ አላህና መልክተኛውን የምትወጂ ከሆነ የግድ ሂጃብ መልበስ አለብሽ  
  3. ”ወላጆቼ ሂጃብ እንዲለብስ አይፈቅዱልኝም”  ነብዩ “የፈጣሪን ትዕዛዝ ለመጣስ ለፍጡር መታዘዝ የለም” ብለዋል፡፡ አሳምኛቸው አስረጃቸው ካልሆነ ግን በዲን ጉዳይ ዝም ብለሽ አላህን መታዘዝ እንጂ ሌላን አካል በጭራሽ  
  4. “ሂጃብ ስለብስ ይጨንቀኛል እራሴን ያመኛል.....”ይህ ሸይጣን በአንቺ ላይ የሚጫወትብሽ ጨዋታ ነው፡፡ እራስሽን አሳምነሽ ከእርሱ ራቂ::እርሱ በርግጥም የኔ፤ያንቺ፤ የጌታሽም ግልፅ ጠላት ነው፡፡  
  5. መደነቅን ስለምወድ ቁንጅናዬና ደም ግባቴ አቋሜ እንዲታይልኝ በሂጃብ ግን ይህን አላገኝም” እዚህ ጋር አንድ ጥያቄ አለኝ የዓለም ህዝቦች በአጠቃላይ ቁንጅናሽን ቢያደንቁ አንቺን ከአንቺነትሽ ስንዝር ከፍ ያደርጉሽ ይመስልሻል? መልስሽ አያደርጉኝም ነው ታደያ ይሄ ጉራ ነው! አላህን ጉረኛን አይወድም መሸፈንሽ በአላህና በመልእክተኛው ቆንጆ ሲያስብልሽ መገለጥሽ በሰይጣንና በጭፍሮቹ መደነቅን ይቸርሻል፡፡ ምረጪ የትኛው ይሁንልሽ?  
  6. “ሂጃብ በመልበስ አምናሁ ግን እኔ ወጣት ነኝ” የትኛው ኢንሹራንስ ነው ችግር የለም ለዚህ ጊዜሽ ያለሽ ለአቅመ ሄዋን አልደረስሽም? በቃ! ሂጃብም ማድረግ ግዴታሽ ነው! 
    ጌታሽ እንዲህ ይላል ”......ወደመልካም ሥራ ተሽቀዳደሙ::”(አል-በቀራ 148)
ያ ዓመተላህ አንቺ መልካም የአላህ ባሪያ ራስሽን አሳምኝው::አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራሽ

Kalí Ad'ífaah