Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከቢድአ ተግባረር መጠንቀቅ

“ከቢድአ ተግባረር መጠንቀቅ”


“ከቢድአ ተግባረር መጠንቀቅ” ከምእመናን እናት እንደተዘገበው የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብላዋል፡- “በዚህ ዲናችን ላይ ከሱ ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ ወደ ሰሪው ተመላሽ ነው፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ሀዲሱን ዘግበውታል) ሀዲሱን የዘገቡት ሶሃባ አጭር ታሪክ
ስማቸው ፡- ዓኢሻ ቢንት አቡበከር ሲዲቅ ዐብደላህ
ከታሪካቸው ፡- ከሴቶች በእውቀትና በግንዛቤ ብሩህ ጭንቅላትን የተጎናጸፉ፣የምእመናን እናት፣የነቢያችን ባለቤት ነበሩ፡፡ነቢያችን ዓኢሻን እጅግ አድርገው ይወዱ ነበር፡፡
ኣኢሻ በእውቀት ከመጠቁ ታላላቅ ወንድ ሶሃቦች የሚመጣጠን ዕውቀት የነበራቸው በመሆኑ በርካታ ሶሃባዎች ከዓኢሻ የረሱልን ሱና ዕውቀት ይወስዱ ነበር፡፡
ዕለተ ህልፈት -በ58ኛው አመተ ሒጅራ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
የሀዲሱ ትምህርቶች
1.ዲነል ኢስላም በነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ)አማካኝነት ተብራራ በመሆኑ እሳቸውን ከመከተል በስተቀር አዲስ ነገርን መፍጠር አላህ ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
2. የነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ)መመሪያ የሌለበትን ስራ መስራት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያላወቁትን እኔ አውቃለሁ ወይም ማድረስ ያለባቸው በሚገባ አላደረሱም እንደ ማለት ነው፡፡
3. ሱና የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግርና ስራ ወይም በሳቸው ጊዛ ሲሰራ አይተው ያልተቃወሙት ተግባር ሲሆን ከዚህ ውጭ የሆነና ወደ እነዚህ የሚመለስ መሰረት የሌለው ስራ ሁሉ ፈጠራ (ቢድዓ) ይባላል

By Haider Khedir on Wednesday, August 22, 2012 at 3:35pm

Post a Comment

0 Comments