Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወንጀል ልብ ላይ ሲያርፍና ቅባት ልብስ ላይ ሲያርፍ አንድ ነው .....


Ibnu Munewor

{وَأَقِمِ الصَّلَاةَ طَرَفَيِ النَّهَارِ وَزُلَفًا مِنَ اللَّيْلِ إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ ذَلِكَ ذِكْرَى لِلذَّاكِرِينَ} (هود: 114)((ሰላትንም በቀኑ ጫፎች እና በሌሊቱም ጨለማ ስገድ፡፡ መልካም ስራዎች መጥፎ ስራዎችን ያብሳሉ፡፡ ይህ ለአስታዋሾቹ ማስታወሻ ነው፡፡)) (ሁድ፡ 114)1. ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ “አንድም ሙስሊም ወንጀልን አይወነጅልም ከዚያ በኋላ ወዱእ አድርጎ ሁለት ረከዐ ከሰገደ ወንጀሉ የሚማርለት ቢሆን እንጂ፡፡” ሸይኹል አልባኒ ሰሒሕ ብለውታል፡፡2. ዑሥማን ዐፋን ረዲየላሁ አንሁ ልክ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አይነት ውዱእ ካደረገ በኋላ እንዲህ አለ “የአላህ መልእክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዚህ መልኩ ዉዱእ ሲያደርጉ አይቻቸዋለሁ፡፡” ከዚያም እንዲህ አሉ “ይህን ዉዱኤን ያደረገ ከዚያም ሁለት ረከዐ የሰገደ በነሱ ውስጥ እራሱን (በዱንያ ጉዳይ) ካልጎተጎተ ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት)
3. አሁንም ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን ረዲየላሁ አንሁ የአላህ መልእክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው ይላል፡ “አሳምሮ ዉዱእ ያደረገ ሰው ወንጀሎቹ ከአካላቱ ይወጣሉ፡፡ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር፡፡” (ሙስሊም የዘገቡት)
4. ከአቡ ሁረይራህ ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ሙስሊም ወይም ሙእሚን ባሪያ ዉዱእ እያደረገ ፊቱን ሲያጥብ በዐይኖቹ በመመልከት የፈፀማቸው ወንጀሎች በሙሉ ከውሃው ጋር ከፊቱ ይወጣሉ፡፡ ወይም ከመጨረሻዋ የውሃ ጠብታ ጋር፡፡ እጆቹን ሲያጥብ ደግሞ እጆቹ የፈፀሟቸው ወንጀሎች በሙሉ ከውሃው ጋር ከእጆቹ ይወጣሉ፡፡ ወይም ከመጨረሻዋ የውሃ ጠብታ ጋር፡፡ እግሮቹን ሲያጥብ ደግሞ እግሮቹ የሄዱባቸው ወንጀሎች በሙሉ ከውሃው ጋር ይወጣሉ፡፡ ወይም ከመጨረሻዋ የውሃ ጠብታ ጋር፡፡ መጨረሻ ላይ ከወንጀል ንፁህ ሆኖ እስከሚወጣ ድረስ፡፡” (ሙስሊም የዘገቡት)
5. አቡ ዘር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፡፡ ነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ምከረኝ” አልኳቸው፡፡ “ወንጀል ከሰራህ በመልካም ስራ አስከትለው ያብስልሃል” አሉኝ፡፡ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! (ላኢላሀ ኢለላህ) ማለት ከመልካም ስራ ነው” አልኳቸው፡፡ እሳቸውም “#ከመልካም_ስራ_ሁሉ_በላጩ_ነው!” አሉኝ፡፡” (ሸይኹል አልባኑ “ሰሒሕ” ነው ብለውታል፡፡)
6. አቡ ሁረይራህ ረዲየላሁ ዐንሁ ባስተላለፉት ደግሞ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “የአምስቱ ወቅት ሰላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው ለተፈፀሙ ወንጀሎች አባሽ /አስወጋጅ ናቸው፡፡ #ባይሆን_ከታላላቅ_ወንጀሎች_ከተራቀ_ነው፡፡” (ሙስሊም የዘገቡት)
}وَسَارِعُوا إِلَى مَغْفِرَةٍ مِنْ رَبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ (133) الَّذِينَ يُنْفِقُونَ فِي السَّرَّاءِ وَالضَّرَّاءِ وَالْكَاظِمِينَ الْغَيْظَ وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ (134) وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنْفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَنْ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَى مَا فَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ (135) أُولَئِكَ جَزَاؤُهُمْ مَغْفِرَةٌ مِنْ رَبِّهِمْ وَجَنَّاتٌ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَنِعْمَ أَجْرُ الْعَامِلِينَ (136) { آل عمران
((ከጌታችሁ ወደ ሆነ ምህረትም ተሽቀዳደሙ፡፡ ወርዷ ሰማያትና ምድር ወደሚያክል ጀነትም እንዲሁ፡፡ እሷ አላህን ፈሪ ለሆኑት ተዘጋጅታለች፡፡ እነዚያ በድሎትም በችግርም ጊዜ የሚለግሱ፣ ቁጭታቸውንም የሚውጡ፣ ከሰዎችም ይቅር የሚሉ ለሆኑት፡፡ አላህ ደግሞ አሳማሪዎችን ይወዳል፡፡ እነዚያ ጥፋትን በፈፀሙ፣ ወይም እራሳቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱ ከዚያም ለወንጀሎቻቸው ምህረትን የሚጠይቁ የሆኑት፡፡ አላህ እንጂ ሌላ ወንጀልን የሚምር ማን አለ?! በሚሰሩት ጥፋትም ላይ እያወቁ የማይቀጥሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ምንዳቸው ከጌታቸው የሆነ ምህረትና ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የሆኑ ጀነቶችን ነው- በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ፡፡ (የመልካም) ሰሪዎች ምንዳ ምንኛ ያማረ ነው?!)) (ኣሊ ዒምራን፡ 133-136