Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሩቅ ምስጢር አዋቂ ነን ባዮች ስራ

የሩቅ ምስጢር አዋቂ ነን ባዮች ስራ

1. ድግምት፦ “ሲህር” (ድግምት) በዓረብኛ ቋንቋ ስውር የሆነና ምክንያቱ ያልታወቀ ነገር ማለት ነው፡፡ 
ሸሪዓዊ ትርጉሙ፦ ልብን ወይም አካልን በማሳመም ወይም በመግደል ተፅዕኖ የሚያሳድር እንዲሁም በባልና ሚስት መካከል የሚለያይ ልፍለፋና ትብተባ ሲሆን ነገር ግን ሁሉም ተፅዕኖ ሊያደርግ የሚችለው በአላህ ፍቃድ ብቻ ነው::
ድግምት ኩፍር ሲሆን ድግምተኛም በአላህ የካደ ካፊር በመሆኑ አኺራ ላይ ምንም ዕጣ ፈንታ የለውም፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፦

وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ وَمَا أُنزِلَ عَلَى الْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَارُوتَ وَمَارُوتَ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّى يَقُولَا إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌ فَلَا تَكْفُر فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِ بَيْنَ الْمَرْءِ وَزَوْجِهِ وَمَا هُم بِضَارِّينَ بِهِ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ وَيَتَعَلَّمُونَ مَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَلَقَدْ عَلِمُوا لَمَنِ اشْتَرَاهُ مَا لَهُ فِي الْآخِرَةِ مِنْ خَلَاقٍ وَلَبِئْسَ مَا شَرَوْا بِهِ أَنفُسَهُمْ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ

‹‹ሰይጣናትም በሱለይማን (ሰሎሞን) ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን (ድግምት) ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ (ድግምተኛ አልነበረም)፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩትና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር (ያስተምሩዋቸዋል)፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ፡፡ እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፡፡ የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ፡፡ የገዛውም ሰው ለርሱ በመጨረሻይቱ አገር ምንም እድል የሌለው መኾኑን በእርግጥ ዐወቁ፡፡ ነፍሶቻቸውንም በርሱ የሸጡበት ዋጋ ከፋ! የሚያውቁ በኾኑ ኖሮ (ባልሠሩት ነበር)፡፡›› (አል በቀራህ 1ዐ2)

በተቋተሩ ክሮች ላይም መትፋት አንዱ የድግምት ክፍል ነው::
አላህ እንዲህ ይላል፦

قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ
مِن شَرِّ مَا خَلَقَ
وَمِن شَرِّ غَاسِقٍ إِذَا وَقَبَ
وَمِن شَرِّ النَّفَّاثَاتِ فِي الْعُقَدِ
وَمِن شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ

በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ፡፡ ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት፡፡ ከሌሊትም ክፋት ባጨለመ ጊዜ፤በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከኾኑት (ደጋሚ) ሴቶችም ክፋት፡፡ከምቀኛም ክፋት በተመቀኘ ጊዜ፤ (እጠበቃለሁ በል)፡፡» (አል ፈለቅ 1-5)

2. ኮከብ ቆጠራ፡- በኮከቦች ሁኔታ ምድር ላይ የሚከሰትን ነገር መተንበይ ማለት ነው፡፡ ኢብኑ ዓባስ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ከከዋክብት እውቀት የተወሰነ የወቀነጨበ ከድግም የተወሰነ ቀነጨበ ማለት ነው:: በጨመረም ቁጥር ከድግምት ጨመረ ማለት ነው፡፡››

3. ወፍ ማባረርና መሬት ላይ ማስመር፡- ቀጠን ኢብን ቀቢሳ ከአባቱ እንዳስተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው ብለዋል ‹‹ወፍ ማባረር፣ ገድ ማለትና መሬት ላይ ማስመር ከድግምት ነው›› ወፍ ማባረር ማለት ወፍ በመልቀቅ በአበራረሯና በሁኔታዋ ገድ ማለት ሲሆን መሬት ላይ ማስመር ደግሞ መስመር በማስመርና ጠጠሮችን በመወርወር የሩቅን ምስጢር አውቀለሁ ባይነት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ በጃሒሊያ ስርዓት የነበሩ ጥንቆላዎች ናቸው::

4. ጥንቆላ፡- ጥንቆላ የሩቅን ምስጢር አውቃለው ማለት ሲሆን መሠረቱ ጂኖች የመልአኮችን ንግግር መስረቅና ለጠንቋዩ ጆሮው ላይ ሹክ ማለት ነው፡፡
አቡ ሑረይሪ እንደተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ወደ ጠንቋይ በመሄድ የሚለው የተቀበለ ሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል››

5. የ “አባጃድ” ፊደሎችን መፃፍ፡- ማለት ለፊደሎች ቁጥር በመስጠትና የሰዎችን የጊዜያትንና የቦታን ስም በመስጠት አንዱ እድለኛ ነው ሌላው እደለቢስ ነው የመሳሰሉትን እያሉ መፍረድ፡፡
ኢብኑ ዓባስ “አባጃድ የሚፅፉና ከዋክብትን የሚቆጥሩ ሰዎችን በተመለከተ ይህን የፈፀመ አላህ ዘንድ ምንም እጣ ፈንታ የለውም እላለው” ብለዋል::

6. መዳፍንና የቡና ሲኒን ማንበብ፡- ይህም አንዳንዶች መሞት፣ መኖር፣ ድህነት፣ ሀብት፣ ጤንነትና በሽታን የመሳሰሉትን የወደፊት ክስተት የሚተነብዩበት ነው፡፡

7. ሟች ነፍስን ማናገር፡- የዚህ ተጠሪዎች ሰው ሲሞት ነፍሱን እንደሚያናግሩና እዚያ ያለውን ፀጋና ቅጣት የመሳሰሉት እንደሚያውቁ በሀሰት ይናገራሉ፡፡
ይህ ተግባር ቅጥፈት ሸይጧናዊ ማጭበርበሪያ ሲሆን የሰዎችን እምነትና ስነምግባር ለማበላሸትና የሩቅ ምስጢርን አውቃለሁ በማለት የአላዋቂዎችን ገንዘብ አጭበርብሮ ለመብላት የሚደረግ ነው፡፡

8. በገድ ማመን፡- በበራሪ ወፎችና በቀበሮ በመሳሰሉት ጩኸቶች ይህ ይቀናኛል ወይም አይቀናኝም እያሉ ገድ ማለት ሲሆን ይህ ሽርክና ሸይጧናዊ ማስፈራሪያ ነው፡፡
ዒምራን ኢብኑ ሁሰይን እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል ‹‹ገድ ያለ ወይም እንዲባልለት ያደረገ፣ የጠነቆለ ወይም የተጠነቆለለት፣ ድግምት የሰራ ወይም እንዲሰራለት ያደረገ ከእኛ አይደለም፤ ወደ ጠንቋይ በመሄድ የሚለውን አምኖ የሚቀበል ሙሐመድ ላይ በተወረደው ክዷል፡፡››
አላህ የሙስሊሞችን ጉዳይ እንዲያሳምር፣ ሃይማኖታቸውን እንዲያስገነዝባቸውና ከሙጅሪሞችና ከሸይጧን ረዳቶች ተንኮል እንዲጠብቃቸው እንለምናለን፡፡


http://www.facebook.com/emnetihintebiq

Post a Comment

0 Comments