Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸይኽ 'አል ጀሊል' አብደላህ አል-ሀረሪና 'አንቱ' ያሰኟቸው ተግባሮች

By  Hassen Mohammed
ሸይኽ 'አል ጀሊል' አብደላህ አል-ሀረሪና 'አንቱ' ያሰኟቸው ተግባሮች******************************************************** ልፋ ያለው በሬ ምን ይሆናል ነበር የሚባለው? ...... ብቻ የሆነ ነገር ይሆናል፥ ትዝ ካለኝ ኋላ ላይ እነግርሀለው:: "المرشد المربي، الولي الصالح، العالِم الجليل، قدوة المحقّقين، عمدة المدقّقين، صدر العلماء العاملين، الإِمام المحدّث، التقي الزاهد، الفاضل العابد، صاحب المواهب الجليلة، الشيخ أبو عبد الرحمن " ከሚሉ የሙገሳና የውዳሴ ቅድመ-ቅጥያዎች በኋላ ስማቸው የተኖረ 'ምናልባትም ብቸኛው' ሰው አብደላህ አል-ሀረሪ ይሰኛሉ:: እንዳይደብርህ ብዬ ነው እንጂ ከስማቸው በኋላም ውዳሴና ሙገሳው ቢያንስ ለአንድ መስመር ተኩል ያህል ይቀጥል ነበር::
እሺ! ወደ ቁም ነገሩ ከመግባታችን በፊት የሚከተለውን ጥያቄ ብጤ አነሳለሁ::
ሸህ አብደላህ አል-ሀረሪ ወይንም አህባሽ ሲባል ምን ትዝ ይልሀል? ጭንቅላትህ ላይ ቀድሞ ትውስ የሚልህ ነጥብስ ምንድን ነው? "አወልያ እንገናኝ ከሚለው መፈክር ውጪ"
ከአህባሽ ጋር ተያይዞ የሰዎች አእምሮ ላይ በብዛት ተስሎ የምታገኘው ምስል የአላህን ስሞችና ባህሪያትን መሰረት ያደረገው ብቻ ነው:: በተለይም الرَّحْمَـٰنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىٰ ከሚለው ሀሳብ በተጻራሪ የሚነዙ ውዥንብሮችን አስመልክቶ ማለቴ ነው:: ይሁንና የዚህ ቡድን አደገኛ ፍጻሜዎች ከላይ የጠቀስነውን ማወናበጂያ ሀሳብ መሰረት ያድርጉ እንጂ የኋላ ኋላ ብዙሀኑን ህብረተሰብ አዳራሽ ወደሆነ አስቸጋሪ የቀብር እምነት ይነዱታል:: ለምሳሌ አላህ ከአርሽ በላይ ነው፥ አይደለም የሚለው ጭቅጭቅ አገራዊ ስምምነት ላይ ተደርሷል ቢባል እንኳ ቀጥለው ከሚረጩት እሳቤዎቻቸው መካከል ቅድሚያ የሚወስደው "በሞቱ ሰዎች ተወሱል ማድረግ ይበቃል!" የሚል ሆኖ ታገኘዋለህ:: እዚህ ላይ ስለ"ተወሱል" ማብራሪያ ማስቀመጥ አልሻም ነገር ግን "በሞቱ ሰዎች" የምትለዋን ሀረግ ጥቁረት ለመረዳት ቀጣዩን ታሪክ ልክ ከኡስታዜ በሰማሁት መልኩ ላቅርብልህ::
ቦታው በተለምዶ ድሬ ሸከና ሁሴን (አናጂና) ይባላል:: እዛ ያሉ ሰዎች ወይንም ወደ እዛ የሚሄዱ ባለጉዳዮች በሸከና ሁሴን ላይ ያላቸው ድንበር የለቀቀ እምነት ጉዳያቸውን ለአላህ "አድርሱልኝ ብሎ" ከመጠየቅ ባሻገር "አንቱ አድርጉልኝ" ወደሚል እርከን ተሻግሯል:: ታዲያ አንድ የቦታው ሙሪድ (مريض ብለው ሊያነቡት ይችላሉ) እንዲህ አለ ይባላል:- "እኔ ሸከና ሁሴንና ረሱል صلى الله عليه وسلم በአንዳች ጉዳይ ቢጣሉ የረሱልን እግር በያዝኩት ከዘራ እመታቸው ነበር፥ እንዴት ከሀበሻ ቁጥብ ጋር ይጣላሉ ብዬ?":: الله أكبر! ወዳጆቼ እንድታውቁት ያህል ነው እንጂ ስጽፈውም እየሰቀጠጠኝ ነው:: ሌላም ግዜ አዲስ አበባ ሀሽም መስጂድ ውስጥ እኔው ራሴ በነበርኩበት አጋጣሚ አንድ በእድሜ ተለቅ ያለ ሰውዬ የአስር ሰላትን ሰግዶ እየተቀራ የነበረውን ሀለቃ ተቀላቀለ:: ትንሽ እንደቆየም ለካ ትኩሳቱ ተነስቶበት ኖሮ እንዲህ ሲል ተቆጣ:- "የአብሬት ሼህ ከረሱል صلى الله عليه وسلم ይበልጣሉ፥ ረሱሉ 23 አመት ብቻ ነው ዳእዋ ያደረጉት፥ አብሬትዬ ግን ከዛ በላይ!" ብሎ አረፈው:: لا إله إلا الله "وَمَا قَدَرُوا اللَّـهَ حَقَّ قَدْرِهِ " ወደዚህ ነው እንግዲህ የምንሰበከው ሰዎች:: ልብ በል ከላይ ያነሳኋቸው ሁለት ምሳሌዎች ከአህባሽ ጋር የሚዛመዱት "ቀብርና ተወሱል" በሚለው ርእስ ስር ይሆናል:: እንዴት የሚለውን ወደፊት አጫውትሀለው إن شاء الله
አንዲት ቢድአ ስትወለድ "ምን ችግር አላት" የሚል ርእስ ይጻፍባታል፣ ቀጥሎም እድሜዋ ለአቅመ "ሙስተሀብ" ይደርስና በስተመጨረሻም "ግዴታ" ወይንም እሷን ከተቃወምክ "ልታከፍርህ" የምትችል ትሆናለች:: እንዳው የኢስቲዋእን ጉዳይ ብቻ ብናይ እንኳ መልእክተኛው صلى الله عليه وسلم ከአርሽ በላይ ነው ብላ የመለሰችውን "ሙእሚን ናት" አሉ፥ ከጊዜ ሂደት በኋላ ጉዳዩ "ኺላፍ አለበት" በሚል አረፍተነገር ተለወሰ፥ በስተመጨረሻም 180 ዲግሪ ዞሮ "ሙእሚን ናት" የሚለው የመልእክተኛው ብይን "ካፊር ናት" በሚል ተፈጸመ::
ለማንኛውም ምናልባት ጊዜውን ካገኘሁት አህባሽና ቀብር ያላቸውን ፍቅር በቀጣይ ቀናት ለማንሳት እሞክራለሁኝ አላህ ከፈቀደ:: አሁን ላይ ግን ቢያንስ ከአንተ አህባሽ ሲባል የአላህ ስምና ባህሪያት ብቻ ሳይሆን ባእድ አምልኮ፥ የቀብር ኢባዳና መሰል ጨለማዎች አብረው ትዝ እንዲሉህ እፈልጋለሁ:: ለአብነት ያህል እኮ የእራሱ የሸኽ አብደላህ ሀረሪን ቀብር ማንሳት ትችላለህ፥ ከታች ምን እንደሚሰራበት ባላውቅም ከላይ ግን በርካታ ሰዎች ከቀብሩ ላይ አፈር በሶፍት እየዘገኑ ሲሄዱ ይታያል:: ምን ሊያደርጉት ነው? አበባ ሊተክሉ? የጓሮ አትክልት ምናምን? ኧረ አትድከም ባክህ በጥብጠው ይጠጡታል፥ "ቱራብ" እኮ ነው ምን ሆነሀል!
እንዲያውም ትዝ አለኝ መግቢያዬ ላይ የጀመርኩት አባባል: "ልፋ ያለው በሬ ከሞተ በኋላ ቆዳው ከበሮ ሆኖ ሲደበደብ ይኖራል"! ይላል ሀገሬው ሲተርት፥ ተረቱበት እንጂ .......
ከሰነበትን እናወራለን እስቲ إن شاء اللهልፋ ያለው በሬ ምን ይሆናል ነበር የሚባለው? ...... ብቻ የሆነ ነገር ይሆናል፥ ትዝ ካለኝ ኋላ ላይ እነግርሀለው:: "المرشد المربي، الولي الصالح، العالِم الجليل، قدوة المحقّقين، عمدة المدقّقين، صدر العلماء العاملين، الإِمام المحدّث، التقي الزاهد، الفاضل العابد، صاحب المواهب الجليلة، الشيخ أبو عبد الرحمن " ከሚሉ የሙገሳና የውዳሴ ቅድመ-ቅጥያዎች በኋላ ስማቸው የተኖረ 'ምናልባትም ብቸኛው' ሰው አብደላህ አል-ሀረሪ ይሰኛሉ:: እንዳይደብርህ ብዬ ነው እንጂ ከስማቸው በኋላም ውዳሴና ሙገሳው ቢያንስ ለአንድ መስመር ተኩል ያህል ይቀጥል ነበር::
እሺ! ወደ ቁም ነገሩ ከመግባታችን በፊት የሚከተለውን ጥያቄ ብጤ አነሳለሁ::
ሸህ አብደላህ አል-ሀረሪ ወይንም አህባሽ ሲባል ምን ትዝ ይልሀል? ጭንቅላትህ ላይ ቀድሞ ትውስ የሚልህ ነጥብስ ምንድን ነው? "አወልያ እንገናኝ ከሚለው መፈክር ውጪ"
ከአህባሽ ጋር ተያይዞ የሰዎች አእምሮ ላይ በብዛት ተስሎ የምታገኘው ምስል የአላህን ስሞችና ባህሪያትን መሰረት ያደረገው ብቻ ነው:: በተለይም الرَّحْمَـٰنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىٰ ከሚለው ሀሳብ በተጻራሪ የሚነዙ ውዥንብሮችን አስመልክቶ ማለቴ ነው:: ይሁንና የዚህ ቡድን አደገኛ ፍጻሜዎች ከላይ የጠቀስነውን ማወናበጂያ ሀሳብ መሰረት ያድርጉ እንጂ የኋላ ኋላ ብዙሀኑን ህብረተሰብ አዳራሽ ወደሆነ አስቸጋሪ የቀብር እምነት ይነዱታል:: ለምሳሌ አላህ ከአርሽ በላይ ነው፥ አይደለም የሚለው ጭቅጭቅ አገራዊ ስምምነት ላይ ተደርሷል ቢባል እንኳ ቀጥለው ከሚረጩት እሳቤዎቻቸው መካከል ቅድሚያ የሚወስደው "በሞቱ ሰዎች ተወሱል ማድረግ ይበቃል!" የሚል ሆኖ ታገኘዋለህ:: እዚህ ላይ ስለ"ተወሱል" ማብራሪያ ማስቀመጥ አልሻም ነገር ግን "በሞቱ ሰዎች" የምትለዋን ሀረግ ጥቁረት ለመረዳት ቀጣዩን ታሪክ ልክ ከኡስታዜ በሰማሁት መልኩ ላቅርብልህ::
ቦታው በተለምዶ ድሬ ሸከና ሁሴን (አናጂና) ይባላል:: እዛ ያሉ ሰዎች ወይንም ወደ እዛ የሚሄዱ ባለጉዳዮች በሸከና ሁሴን ላይ ያላቸው ድንበር የለቀቀ እምነት ጉዳያቸውን ለአላህ "አድርሱልኝ ብሎ" ከመጠየቅ ባሻገር "አንቱ አድርጉልኝ" ወደሚል እርከን ተሻግሯል:: ታዲያ አንድ የቦታው ሙሪድ (مريض ብለው ሊያነቡት ይችላሉ) እንዲህ አለ ይባላል:- "እኔ ሸከና ሁሴንና ረሱል صلى الله عليه وسلم በአንዳች ጉዳይ ቢጣሉ የረሱልን እግር በያዝኩት ከዘራ እመታቸው ነበር፥ እንዴት ከሀበሻ ቁጥብ ጋር ይጣላሉ ብዬ?":: الله أكبر! ወዳጆቼ እንድታውቁት ያህል ነው እንጂ ስጽፈውም እየሰቀጠጠኝ ነው:: ሌላም ግዜ አዲስ አበባ ሀሽም መስጂድ ውስጥ እኔው ራሴ በነበርኩበት አጋጣሚ አንድ በእድሜ ተለቅ ያለ ሰውዬ የአስር ሰላትን ሰግዶ እየተቀራ የነበረውን ሀለቃ ተቀላቀለ:: ትንሽ እንደቆየም ለካ ትኩሳቱ ተነስቶበት ኖሮ እንዲህ ሲል ተቆጣ:- "የአብሬት ሼህ ከረሱል صلى الله عليه وسلم ይበልጣሉ፥ ረሱሉ 23 አመት ብቻ ነው ዳእዋ ያደረጉት፥ አብሬትዬ ግን ከዛ በላይ!" ብሎ አረፈው:: لا إله إلا الله "وَمَا قَدَرُوا اللَّـهَ حَقَّ قَدْرِهِ " ወደዚህ ነው እንግዲህ የምንሰበከው ሰዎች:: ልብ በል ከላይ ያነሳኋቸው ሁለት ምሳሌዎች ከአህባሽ ጋር የሚዛመዱት "ቀብርና ተወሱል" በሚለው ርእስ ስር ይሆናል:: እንዴት የሚለውን ወደፊት አጫውትሀለው إن شاء الله
አንዲት ቢድአ ስትወለድ "ምን ችግር አላት" የሚል ርእስ ይጻፍባታል፣ ቀጥሎም እድሜዋ ለአቅመ "ሙስተሀብ" ይደርስና በስተመጨረሻም "ግዴታ" ወይንም እሷን ከተቃወምክ "ልታከፍርህ" የምትችል ትሆናለች:: እንዳው የኢስቲዋእን ጉዳይ ብቻ ብናይ እንኳ መልእክተኛው صلى الله عليه وسلم ከአርሽ በላይ ነው ብላ የመለሰችውን "ሙእሚን ናት" አሉ፥ ከጊዜ ሂደት በኋላ ጉዳዩ "ኺላፍ አለበት" በሚል አረፍተነገር ተለወሰ፥ በስተመጨረሻም 180 ዲግሪ ዞሮ "ሙእሚን ናት" የሚለው የመልእክተኛው ብይን "ካፊር ናት" በሚል ተፈጸመ::
ለማንኛውም ምናልባት ጊዜውን ካገኘሁት አህባሽና ቀብር ያላቸውን ፍቅር በቀጣይ ቀናት ለማንሳት እሞክራለሁኝ አላህ ከፈቀደ:: አሁን ላይ ግን ቢያንስ ከአንተ አህባሽ ሲባል የአላህ ስምና ባህሪያት ብቻ ሳይሆን ባእድ አምልኮ፥ የቀብር ኢባዳና መሰል ጨለማዎች አብረው ትዝ እንዲሉህ እፈልጋለሁ:: ለአብነት ያህል እኮ የእራሱ የሸኽ አብደላህ ሀረሪን ቀብር ማንሳት ትችላለህ፥ ከታች ምን እንደሚሰራበት ባላውቅም ከላይ ግን በርካታ ሰዎች ከቀብሩ ላይ አፈር በሶፍት እየዘገኑ ሲሄዱ ይታያል:: ምን ሊያደርጉት ነው? አበባ ሊተክሉ? የጓሮ አትክልት ምናምን? ኧረ አትድከም ባክህ በጥብጠው ይጠጡታል፥ "ቱራብ" እኮ ነው ምን ሆነሀል!
እንዲያውም ትዝ አለኝ መግቢያዬ ላይ የጀመርኩት አባባል: "ልፋ ያለው በሬ ከሞተ በኋላ ቆዳው ከበሮ ሆኖ ሲደበደብ ይኖራል"! ይላል ሀገሬው ሲተርት፥ ተረቱበት እንጂ .......
ከሰነበትን እናወራለን እስቲ إن شاء الله