Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሚንሀጁ ሱናህ


By Mohammed Iberahim
قال شيخ الإسلام ابن تيمية: "وطريقة سلف الأمة وأئمتها: أنهم يصفون الله بما وصف به نفسه وبما وصفه به رسوله مِنْ غَيْرِ تَحْرِيفٍ وَلا تَعْطِيل، وَلا تَكْييفٍ وَلا تَمْثِيل، إثبات بلا تمثيل، وتنزيه بلا تعطيل، إثبات الصفات، ونفي مماثلة المخلوقات، قال تعالى: {لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ} فهذا رد على الممثلة {وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ} الشورى: 11 رد على المعطلة." منهاج السنة 2/523ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ብለዋል፡ {የዚህ ኡማህ ቀዳሚ ትውልዶች (ሰለፎች) እና ታላላቅ ኢማሞች አካሄድ፡- አላህ እራሱን በገለጸባቸው እና መልዕክተኛው እርሱን በገለጹባቸው ባህሪዎች አላህን ይገልጹታል፤ ይህንን ሲያደርጉም፤ ያለ “ተህሪፍ” (ትርጉም ማዛባት) እና ያለ “ተዕጢል” (ትርጉም አልባ ማድረግ)፣ እንዲሁም ያለ “ተክዪፍ” (የባህሪዉን ሁኔታና ምንነት መግለጽ) እና ያለ “ተምሢል” (አምሳያ ማድረግ) ነው፤ ባህሪዎችን ሲያጸድቁ አያመሳስሉም፤ አላህን ከአምሳያና ከጉድለት ባህሪዎች ሲያጠሩም ባህሪዎችን ትርጉም አልባ አያደርጉም፤ ከፍጡራን ጋር ያለን መመሳሰል ውድቅ በማድረግ ባህሪዎችን ማጽደቅ ነው መንገዳቸው።አላህ እንዲህ ይላል፦
{لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ} الشورى: ١١
የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡) አል ሹራ 11)
«የሚመስለው ምንም ነገር የለም» የሚለው ክፍል አላህን ከፍጥረታቱ ጋር ለሚያመሳስሉ “ሙሸቢሀዎች” መመሳሰል እንደሌለ ምላሽ ይሰጣል።
«እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡›› የሚለው ክፍል ደግሞ ባህሪዎችን ለሚያስተባብሉ “ለሙዓጢላዎች” ለአላህ
የተገቡ ባህሪያት እንዳሉት ምላሽ ይሰጣል።
ሚንሀጁሱናህ ቅጽ 2 ገጽ 523