Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መንዙማና ውስጡ ያዘላቸው የሽርክ፤ የቢድዓና የተራ ዛዛታ ወሬ

መንዙማና ውስጡ ያዘላቸው የሽርክ፤ የቢድዓና የተራ ዛዛታ ወሬ

By Sadat Kemal Abu Nuh
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩህሩህ በሆነው፡፡ ከሽርክ እራሳችንን እንጠብቅ፡፡ ልብ ብሎ ላየው ለተመለከተው፤ የአላህ መልክተኛ የተነበዩት እውነት ሆኖ እየታየ ይገኛል፡፡ የአላህ መልክተኛ ‹‹ዘምን ይመጣል እውነተኛው ውሸተኛ፤ ውሸተኛው እውነተኛ የሚባልበት›› እንዲሁም የአላህ መልክተኛ ‹‹ከንግግርም ድግምት አለ›› ይሉናል፡፡ በአላህፈቃድ ማንሳት የፈለግኩት አርዕስት መንዘማ በሚል ይሆናል፡፡

የምትከተለውን ነጥብ ልብ ማለት ግድ ይላል፡፡ ከአላህ ውጭ መለመን፤ ከአላህ ውጭ ሸሸሁባችሁ ማለት፤ ከአላህውጭ ያለን ልክ እንደ አላህ መውደድ፤ ከአላህ ውጭ ባለ አካል ድረሱልኝ ማለት፤ ከአላህ ውጭ የሩቅን የሚያውቅ አለማለት፤ከአላህ ውጭ ወንጀልን የሚምር አለ ብሎ ማመን እና መናገር፤ እንደው በጠቅላላ የአምልኮ ክፍሎችን በንግግርም ይሁን በእምነት ወይንም በተግባር ከአላህ ውጭ ላለ አካል ማድረግ የኩፍር እና የሽርክ ተግባር መሆኑን ማንም ሊዘነጋው አይገባውም፡፡ ይህንን ተግባር እየሰራ የሞተም ሰው የእሳት ጓድ ነው፤ የአላህ ወልይም ሊባል አይችልም፤ የነብያችን ተከታይም ሊባል አይችልም፡፡

የሰው ልጆች ሁሉ አለቃ፤ የነብያት መሪን አላህ እንዲህ በል ይላቸዋል፡፡
قُلْ إِنَّمَآ أَدْعُو رَبِّى وَلاَ أُشْرِكُ بِهِ أَحَداً - قُلْ إِنِّى لاَ أَمْلِكُ لَكُمْ ضَرّاً وَلاَ رَشَداً - قُلْ إِنِّى لَن يُجِيرَنِى مِنَ اللَّهِ أَحَدٌ وَلَنْ أَجِدَ مِن دُونِهِ مُلْتَحَداً
እኔ የምገዛው ጌታዬን ብቻ ነው፤ በርሱ ላይ አንድንም አላጋራም በል፡፡ እኔ ለናንተ ጉዳትንም ቀጥታንም አልችልም፤ በላቸው፡፡ እኔ ከአላህ (ቅጣት) አንድም አያድነኝም፤ ከርሱም ሌላ መጠጊያን አላገኘም፤ በላቸው፡፡

ذَلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ الْمُلْكُ وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ - إِن تَدْعُوهُمْ لاَ يَسْمَعُواْ دُعَآءَكُمْ وَلَوْ سَمِعُواْ مَا اسْتَجَابُواْ لَكُمْ وَيَوْمَ الْقِيَـمَةِ يَكْفُرُونَ بِشِرْكِـكُمْ وَلاَ يُنَبِّئُكَ مِثْلُ خَبِيرٍ ﴾
ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው ንግስና ለእርሱ ብቻ ነው፤ እነዚያም ከርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሺፋን እንኳ አይኖራቸውም፡፡ ብትጠሯቸውም ጥሪያችሁን አይሰሙም፤ ቢሰሙም ኖሮ ለናንተ አይመልሱላችሁም፤ በትንሳኤም ቀን(እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ፤ እንደ ውስጠ አዋቂው ማናም አይነግርህም፡፡

መንዙማና ውስጡ ያዘላቸው የሽርክ፤ የቢድዓና የተራ ዛዛታ ወሬ እንደሚከተለው ይሆናል
 

1. በዝቶብኛልና አያሌ ነገር

አቤት ብዬ ልጩህ እባሮቹ በር

ቀሌቤን ወዳሳቸው አድርጌ ሰንዘር

አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር

ከሙስጠፋ ይዤ እስከ አቡል በሸር

አምቢያ ሙርሰልም አንድ እንኳን ሳይቀር

2. በዘመን ያላችሁ ሳዳቶች አኽያር

ቀኝ እጄን ጨብጡኝ ወድቄ እንዳልቀር

ሺሊላህ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱር

መቼም ያለናንተ ሁለም አያምር

በናንተ የሸሸ ምንም አያፍር

ጌቶቼ አትለፉኝ አዳቤም ባያምር

አደበቢስ ቡልሀ እንደኔ ቢኖር

ባሪያ ሲባሌ ማጥፋት እለት ነው እድር

ለናንተ ይገባል ያጠፋን መማር፡፡

3. አልሀምዱሊላሂ ይመስገን ገፋር

ቀልቤን ያዞረልኝ ወደናንተ በር

በናንተ የሸሸ ያገኛል ሹም ሽር

ሊለግስ ነው መሰሌ ዳመናው ዟዟረ

የስልካችሁ ንባብ ይሰማ ጀመረ፡፡

4. ሁለም ባንድ ሆነው ከሙስጠፋ ጋር

ዛሬ ይድረሱልን ላገኘን ችጋር

5. አንተል ቁረይሺዩ አንተ ነብዩና

ቢሲሪ ሲሪከ ዘይን ባጢነና

6. የቦረናው ደግዬ

እርዱኝ አባብዬ

7. ሰለፍም ኸለፍም ማወረአል ባህር

በሁለም ሸሸሁኝ አንድ እንኳን ሳይቀር

ከዛፍ ከቅጠሉ በዝቶብኝል ነውር

እሜዳው ላይ ሆኜ ወድቄ በዱር

መግቢያ በር አጥቼ ታግቼ ባጥር

አልሄድ ወደፊት ወደኋላ አልበር

በቀኝ በግራዬ እሳት ገደል ባህር

አቤት ጠራኋችሁ ጌቶቼ ዱስቱር፡፡

ረዳቴ ማንነው ከናንተ በቀር

8. የአበራ ሙዝ አባት የማይደፈር

አቤት ይታይልኝ ምነው የኔም ዱር

ዘሩልኝ ጌቶቼ በአውን በነስር

ከጃችሁ ከጅዬ ቆሜያለሁ ከበር፡፡

በናንተ የሸሸ ምን ጊዜም አያፍር

ሀጃዬን አውጡልኝ በዟሂር በሲር

9. ሺሊላህ ያሰይድ አብዱል ቃድር እርዳታቸው አይውል አያድር

10. ሺሊላህ ሸህ ሙሃመድ ባህሩ ለጠራው ደራሽ ነው ምን ቢርቅ አገሩ፡፡ እኔስ ይገርመኛል የሰው ነገር ይላል እንዘይርቀልቡን ሳያጠራ የማያውቁ መስሎት የቀልቡን የሰድሩን

11. መጀን በኑር ሁሴን በአሩሲው ኑር

የአውሉያዎቹ ሻምበል የበርም የባህር

ከራማው ይፋ ነው አይደለም መስቱር

እጣው እንደ ነቢይ በርዳዳው ገበር፡፡

የሪጀልች አባት የነዚያ ያብራር

የነአህመድ ኑረላህ ዚልፈይዲል ሚድራር

ተብል አላህ ዘንዳ በሻሀው አብሽር

ጌታዬ ኑር ሁሴን በለኝ እንጂ አጀብ

በለኝ የኔ አሽከር

በዱንያ በአኸይራም እንዳልቸገር

በናንተ የሸሸ እንዲሁም አይቀር

አላህ ሰጥቷቸኋል ሳይሰፍር ሳይቆጥር፡፡

12. ጌታችን ቃዲር እኩሉንም አለው

አብሽር አጋፍር

አልብስም አጉርስም አመኩስ አክብር

ኢንስም ጂን ቢሆን በጫማህ ይደር

ይፍራህም ይወቅህ አውሪ እንኳ በዱር

አውቆና ለጥቆ ሰልቶ ባንተ አምር

ለሀልቁ ገበያ መድሀኒት ነበር፡፡

የቸገረው ሄዶ የለውም ማፈር

ከሀያቱ በልጧል ውለታው በቀብር

ወዲያልኝ የሱ ጉድ አያልቅም ይቅር

13. የሀድራ ጦያራ ይዞ የሚበር

ሲጠሩት ፈጣን ነው ቶል የሚሀድር

ተምኪን የተሰጠው ዞሂር ወባጢን

እኔ ያለሁበት እክጀላ በር

ቀድሬም አያደርሰኝ መቃም ለመቁጠር

ስንቱን አሳደገው ገና በነዝር

ፈይዱ ከአፍ ሲፈልቅ የአጀብ ነበር

እንኳን ሰው መላኢካ ያዳምጠው ነበር፡፡

14. ጌታው ሰይድ አህመድ የደባቱ ኑር

ዶላል ያስፈቀተው የዲኑ ጨረር

ስፍር ቁጥር የለው ስንቱ በእጁ ሻረ

አላህ ዘንድ ነበር ተናግሮ የማያፍር

ቢያለብስም ቢገፋም ቢያደኸይ ቢያከብር

ይግባኝ የለበትም በፈረደው አምር

ተብሎ አላህ ዘንዳ በሻሀው አብሽር

15. ጌታው ሸረፈዲን የደግየው ኑር

አላህ ትላቅ እጣ አድሎት ነበር

ሰውም ጂንም ቢሆን አውሬውም የዱር ሁለም አቤት ብሎ ተገዝቶ ነበር

ጥላው የሚበቃው በሁለት አገር

በሱ ይወሰላል እስላምም ካፊር

ሴትም ወንድ ቢሆን

አብድ ቢሆንም ሁር

በሱ ተወስል የለውም ችጋር

16. ይመነጥቁታሌ ያወጡታሌ ከጭንቅ

17. እኝህን ሳዳቶች ድረሱ አንበላቸው

እሱ ወደደና እሱ መረጣቸው

አመሀባው ባህር ሺህ አመት አስዋኛቸው፡፡

እሱ ወደዳቸው በፊት ሳይሰራቸው

ዩሂቡሁም ወዩሂቡነሁ አላቸው ጀባሩ፡፡

አቤት እርዱኝ ይላል የቤት ልጅ አሽከሩ

በናንተ የሸሸ የቂን ነው ማማሩ

ጥላቸው ጠባቂ በሁለት አገር

18. ደግሞ ጌታ ሰይድ የማይባሩ ኑሩ

ረህመት አድርጎ አላህ አዝልቆት ነበረ

ለኸልቁ ነበረ በልግና መህር

ሰውም ጂንም መላኢካም ተገዝቶ ነበር

19. አልዩ ሀይደር ነበረ

ለነቢ ማኖሪያ ሚስጥር

ኢልመልገይብ ከሱ ይጠየቅ ነበር፡፡

20. ሙሀመዱ ሰማን ገፍታሪው ቀደር

21. ሸህ ሙሳ ሰገራት ውስጡ ላዩ ኑር

የከሽፋን መነጥር ታድል ነበር፡፡

22. ሸህ ሙሀመድ ሸሪፍ የርጎየው ገበር

ሲሞድህ ሙስጠፋን እያየ ነበር፡፡

23. ሰይድ ቡሽራ ገታ ቀምጣላው ገበር

ከልካይ የለበትም ሲዘልቅኝ እልፍኝ በር

ጨወታው ነበር ቀዷ ቀደር ጋር

ከሙስጠፋ ጋራ የሚነጋር

ማሂሩ ወጌሻ ለዟሂር ለሲር

ስንቱ በሽተኛ ዛቱን አይቶ ሻረ

ሰውም ጂንም ለሱ ታጠቀ ገበረ

ከራማ በበጠልሻ ነዳፊ ነበረ

ሙቶም በሀያቱ ጠቃሚ ገበር፡፡

24. መጂት ሀጅ ቡሽራ የራቀው ገበር

አገላባጭ ነበር የቀዷ ደብተር

ለውሀል መህፉዝ አይቶ ነበር ሲናገር፡፡

25. እነሀጅ አረቦ የሳልመኔው ኑር

ሀለዋውን ያደረገው ከነብዩ ጋር

26. ሸህ መሀመድ ፈቂህ ባለመነጽር

የታደለው ገበር ከአላህ ዘንዳ ሲር

27. ለካ ገረዋ ላይ አብርቷል ጀምበር ሲፈቱ መለኪያ ዛቱ በበሽር

ተብሎ አላህ ዘንዳ በሽር ወአንዙር

ጎራ የማይጋርደው ይዟል መነጸር

ይናገር ነበረ የዟሂር የሲር

ይገልጠው ነበረ የኸልቁን ሀጢር

28. እንደሁሴን ጂብሪል ደግሞ ማን ነበረ

የከሽፉን መነጸር አይኑ ላይ ነበር

የፊቱን የኋላን ይናገር ነበር

ሁለም ተገላሌጦ ይታየው ነበር፡፡

29. እነሸህ ሀቢቡ ጉደኛው ገበር

ከአርሽ እስከ ሰራ ይታየው ነበር

አላህ እድርጎት ነበር የሚስጥር ሰፈር

30. ቁንዲ ሸህ አብደላ ወልዩ ገበር

ከአላህ ጋር የፈጀው ሚስጥሩን በሲር

ይናገረው ነበር አሟቱ በቀብር

31. አላሁ መሰላ አላ ሙሀመዴ

መገን ነቢ የሁለ ቀላቢ

32. የቃጥባሪው ጌታ ኢሳ የአላህ ኑር

ከሚን ኢንደላሂ የተባለ አብሽር

33. ለገሂዳም ጃማ ስንቱ ጉድ ነበር

እነ ነብዩ ሀድራ የተባሉ አብሽር

ባልከው ይሁን ያለው ገና ሲፈጠር

34. ጌታው አባ ረህማ የአውሉያ መምህር

ጨዋታው ነበረ ሰይድ ከድር ጋር

ሁለም ከሀድራው ይቀስም ነበር፡፡

35. ኢስማኢል ጀበርቲ ጉድ ያለው ነበር

ከራማው እንደ ባህር የሞላው ገበር

ሰውንም ጂንም ጨልጦ የሚያስቀር

እሱነው ይባላል የቃማቴ ሲር

36. እነሱ ይበራሉ በመቶ ሃምሳ ጀት

እኛ ቀደምናቸው በአንድ ዘርባ ጫት

የሰው ልጆች ሁሉ አለቃ፤ የነብያት መሪን አላህ እንዲህ በል ይላቸዋል፡፡
قُلْ إِنَّمَآ أَدْعُو رَبِّى وَلاَ أُشْرِكُ بِهِ أَحَداً - قُلْ إِنِّى لاَ أَمْلِكُ لَكُمْ ضَرّاً وَلاَ رَشَداً - قُلْ إِنِّى لَن يُجِيرَنِى مِنَ اللَّهِ أَحَدٌ وَلَنْ أَجِدَ مِن دُونِهِ مُلْتَحَداً
እኔ የምገዛው ጌታዬን ብቻ ነው፤ በርሱ ላይ አንድንም አላጋራም በል፡፡ እኔ ለናንተ ጉዳትንም ቀጥታንም አልችልም፤ በላቸው፡፡ እኔ ከአላህ (ቅጣት) አንድም አያድነኝም፤ ከርሱም ሌላ መጠጊያን አላገኘም፤ በላቸው፡፡

ذَلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ الْمُلْكُ وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ - إِن تَدْعُوهُمْ لاَ يَسْمَعُواْ دُعَآءَكُمْ وَلَوْ سَمِعُواْ مَا اسْتَجَابُواْ لَكُمْ وَيَوْمَ الْقِيَـمَةِ يَكْفُرُونَ بِشِرْكِـكُمْ وَلاَ يُنَبِّئُكَ مِثْلُ خَبِيرٍ ﴾
ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው ንግስና ለእርሱ ብቻ ነው፤ እነዚያም ከርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሺፋን እንኳ አይኖራቸውም፡፡ ብትጠሯቸውም ጥሪያችሁን አይሰሙም፤ ቢሰሙም ኖሮ ለናንተ አይመልሱላችሁም፤ በትንሳኤም ቀን(እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ፤ እንደ ውስጠ አዋቂው ማናም አይነግርህም፡፡ 

Post a Comment

0 Comments