Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

«ክህደት ነው!» - አል-ኢማም አሽ-ሻፊዒ!

By Ilyas Ahmed 

አል-ኢማም አሽ-ሻፊዒ እንዲህ ብለዋል፦
« لِله -تبارك وتعالى- أسماءٌ وصفاتٌ، جاء بها كتابُه وخبَّر بها نبيُّه -صلى الله عليه وسلم- أمّتَه، لا يَسَعُ أحدًا مِن خلْقِ الله -عزَّ وجلَّ- قامت لديه الحُجّةُ أنّ القرآنَ نزل به، وصحَّ عنده قولُ النبيّ -صلى الله عليه وسلم- فيما رَوى عنه العدلُ خلافُه، فإنْ خالف ذلك بعد ثبوت الحجّة عليه؛ فهو كافر بالله -عزَّ وجلَّ-. فأما قبل ثبوت الحجّةِ عليه من جهة الخبر؛ فمعذور بالجهل؛ لأن عِلم ذلك لا يُدرك بالعقل، ولا بالرَّوِيّة والفِكر...»
«ለአላህ በመፅሐፉ ውስጥ የመጡና ነብዩም ለህዝባቸው የተናገሯቸው ስሞችና ባህሪዎች አሉት ከአላህ ፍጡራን ማንም ቢሆን በቁርኣን እንደተወሱ ግልፅ መረጃ ከደረሰውና የነብዩም ንግግር ታማኝ አስተላላፊ ባወራው ትክክለኛ ዘገባ እርሱ ዘንድ ከተረጋገጠ በኋላ የተለየ አቋም የመያዝ ምርጫ አይኖረውም፤ መረጃው (በግልፅ ሁኔታ) ከፀናበት በኋላ ከተፃረረው በአላህ የካደ ይሆናል፤ መረጃው በዘገባ በኩል (ግልፅ ሆኖ) ሳይፀናበት በፊት ከሆነ ግን ባለማወቁ ምክንያት ይታለፋል (ከሀዲ አይሆንም)፤ ምክንያቱም ይህ በአዕምሮ (ምርምር)፣ ወይም በእርጋታ በማሰብና በማሰላሰል የሚደረስበት አይደለምና..!»  ይህንን ካሉ በኋላ አንዳንድ የአላህ ባህሪያት የፀደቁባቸውን ማስረጃዎች በምሳሌነት አጣቀሱና ንግግራቸውን እንዲህ ብለው ቋጩ፦
«(لكن نُثْبِتُ هَذِهِ الصِّفَاتِ، وَنَنْفِي التَّشْبِيهَ كَمَا نَفَى عَنْ نَفْسِهِ -تعالى ذِكْرُه- فَقَالَ: (لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ»
«..ግን እነኚህን ባህሪያት እናፀድቃለን፤ ማመሳሰልንም (አላህ) እራሱ «እንደርሱ ያለ (አምሳያ) ምንም የለም» ብሎ ውድቅ እንዳደረገው ውድቅ እናደርጋለን።»
[“ጁዝኡን ፊ’ዕቲቃዲ’ል-ኢማም አሽ-ሻፊዒይ” (የአቡ ጣሊብ አል-ዑሻሪ ዘገባ የእጅ ፅሁፍ መዝገብ) ገፅ 3፣ “መናቂቡ’ሽ-ሻፊኢይ” ሊ’ብኒ አቢ ሃቲም [ኢብኑ ሐጀር በ“ፈትሁ’ል-ባሪ” (13/407) እንደጠቀሱት]፣ “ጠበቃቱ’ል-ሀናቢላ” ሊ’ብኒ አቢ የዕላ (1/283)፣ “ዘምሙ’ት-ተእዊል” ሊ’ብኒ ቁዳማ ገፅ 124]