Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስእል (ተስዊር)

ስእል (ተስዊር)

 "አላህ መልካም የሻለትን ሠው ዲኑን ያሣውቀዋል "
    (ቡኻሪና ሙሥሊም)
    ስእል (ተስዊር)
    የአንድን ነገር ምስል ከወረቀት ላይ ማስቀመጥ ወይም አካላዊ ገፅታውን መቅረፅ ማለት ነው:: ቀጥሎ ይህን በተመለከተ ከአላህ የወረዱ የቁርዐን አንቀፆችንና ነቢያዊ ሀዲሶችን እንመለከታለን አላህ ያግዘን!!
    <<እርሡ አላህ ፈጣሪው አስገኚው ቅርፅ አሳማሪው ነው >>(አል-ሐሽር24)

    አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ተከታዩን ተናግረዋል:-
    " አላህ የእኔን ፍጡራን አስመስሎ ለመፍጠር ከሚሞክር የበለጠ ግፈኛ የለም ከቻለ አቶም (ቅንጣት) ወይም ገብስ ይፍጠር"
    (ቡኻሪና ሙሥሊም)
    አናታችን አኢሻ:-
    " የቂያማ እለት ከማንም በከፋ ሁኔታ የሚቀጡት በፈጠራ ከአላህ ጋር የሚፎካከሩ ናቸው"
    (ቡኻሪና ሙሥሊም)
    ኢብኑ አባስ
    "ሠአልያን የእሳት ሠዎች ናቸው በሳሉት ስዕል ልክ ነፍስ ይበጅላቸውና ጀሀነም ውስጥ ይቀጡበታል"
    (ቡኻሪና ሙሥሊም)
ፎቶ አንሺዎች  (ሠአሊዎች) በጀሀነም የሚቀጡ ከሆነ ተነሺዎቹ ደግሞ ለራሳቸው የሆነ ቅጣት ይቀጣቸዋል የሚለውን ያሳየናል::
    አላህ ይጠብቀን!!!!
    ፎቶ መነሣት የተፈቀደባቸው ምክንያቶች
    1.ለመታወቂያ
    2.ለመንጃ ፍቃድ
3. ለፓስፖርት ነው

በአሁን ዘመን ግን ለማስታወሻ ለምርቃት ለሠርግ በሚሊ ምክንያቶች ፎቶን እንደቀልድ ሲነሳ እና ሲያጠራቅም ይታያል ይህም የሚያሣየው ኡማው ምን ያክል በዩሁዳና በክርስቲያኖች ተፅእኖ እንደወደቀና ከዲኑ እንደራ ቀን::

    ሐያጅ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል ዓሊይ (ረዐ) እንዲህ አሊኝ
    "የአላህ መልዕክተኛ የሠጡኝን ተልኮ አስጨብጨ ልላክህን ስዕል ካገኘህ አጥፋ ከፍ ብሎ የተገነባ ቀብር ካገኘህም አስተካክል"
    (ሙሥሊም)
    የተከለከለበት ምክንያት
    1የአላህና የረሡል (ሠዐወ) ክልከላ ስላለበት
    2.ለሽርክ መንስኤ ስለሚሆን
    3 ከሀዲያን ጋር ስለሚያመሣስል
    አላህ ከተከለከሉ ነገሮችን ከመዳፈር ይጠብቀን!!

    <<በላቸው አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ አላህ ይወዳችኃልና ሃጢአታችሁንም ለናንተ ይምራልና አላህ መሀሪ አዛኝ ነው:: አላህ እና መልዕክተኛውን ታዘዙ ብትሸሹ አላህ ከሀዲዎችን አይወድም በላቸው >>
    (አል ኢምራን:31-32)
    <<አላህና መልዕክተኛው ምንም ነገርን በፈረዲ ጊዜ ለምእመናንና ለምዕመናት ከነገራቸው ለነርሡ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም>>
    (አልአህዛብ36)

"አላህን የሚፈራ ሠው ለርሡ መውጫውን ያደርግለታል ከማያስበውም በኩል ሲሳይን ይሠጠዋል"
(አል ጦለቅ 2)

    እና አላህ በከለከለው ጉዳይ ምንም ድርድር የለም መተው ነው:

Post a Comment

0 Comments