Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የነቢያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የአመጋገብ & የአጠጣጥ ሱና
የነቢያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የአመጋገብ ሱና
1 ነቢያችን ከምግብ በፊት ይታጠቡ ነበር። የሚበሉትም ከፊታቸው ነበር
2 ነቢያችን ተደግፈው በልተው አያውቁም። ለምግብ ሲቀመጡ ወይ ተሸሁድ ላይ አይነት፣ ወይም እንዲሁ ተቀምጠው አንድ እግራቸውን ጉልበት ደረታቸው ላይ በማቀፍ ወይ ደግሞ ቁጢጥ በማለት ነበር።
3 ነቢዩ ምግብ ሲጀምሩ ቢስሚላህ በማለት ነው።
4 ነቢያችን ምግቡን ካልወደዱት ስለምግቡ ምንም ሳይናገሩ መመገብ ይተው ነበር።
5 የማያውቁት ምግብ ከገጠማቸው አስቀድመው ስለምግቡ ይጠይቁ ነበር።
6 ነቢያችን ምግባቸውን አሽትተው አያውቁም። ጥሩ ያለሆነ ልምድ እንደሆነም ይቆጥሩታል።
7 በጣም የሞቀ ምግብ አይመገቡም ያቀዘቅዙት ነበር። «አላሁ ተዐላ እሳት አይነመግበንም» ይሉ ነበር። በጣም የሞቀ ምግብ ውስጥ በረካ የለውም ብለዋል።
8 ነበዩ ምግብም ሆነ መጠጥ ላይ ተንፍሰው አያውቁም። መጠጥን በትንፋሽ ማቀዝቀዝ አይወዱም ነበር።
9 ነቢዩ ሀብታሞች ቤት እንደሚሆነው በብዙ ሳህን የሚቀርብ ምግብ አይወዱም ነበር።
10 በአብዛኛው ነቢዩ ሲመገቡ በሶስት ጣታቸው(አውራ፣ ጠቋሚና መሐል ጣታቸውን) በመጠቀም ሲሆን ምግቡ ቀጠን ያለ ከሆነ ቀለበት ጣታቸውን ይጨምሩ ነበር።
11 አንድ አይነት ምግብ ከቀረበላቸው ከፊታቸው ይመገባሉ የተለያየ አይነት ከሆነ ግን ከሌላ ቦታ ከመመገብ አይቆጠቡም ነበር።
12 ነቢዩ ከሰው ጋር እየበሉ ከሆነ የሚነሱት በመጨረሻ ነበር። ቀስ ብለው የሚመገቡ ሰዎችን ላለማሳፈር።
13 ሲጨርሱ ጣታጫውን በአፋቸው ያፀዱ ነበር።
14 ነቢዩ ተመግበው ሲጨርሱ እንዲህ ይሉ ነበር «የምንበላውና የምንጠጣውን የሰጠኸን፣ ሙስሊምም ያደረግኸን አምላክ ምስጋና ይገባህ!» ይሉ ነበር።
ነቢዩ ምግብ ለተሰባሰቡ ሰዎች የሚያከፋፍሉ ከሆነ በቀኝ ይጀምሩ ነበር። በግራ መጀመር ከፈለጉ በቀኝ ያለውን ያስፈቅዱ ነበር።
ነቢያችን ስጋ ወደ ቤት ሲያመጡ ለጎረቤት እንዲበቃ ተደርጎ እንዲሰራ ያደርጉ ነበር።
ነቢዩ ሀለዋ፣ ማር፣ ኮምጣቴ፣ ተምር፣ ሀብሀብ፣ ኪያር እና ዝኩኒ ይወዱ ነበር።
የአጠጣጥ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና
1 ነቢያችን ውሀ ሲጠጡ ድምፅ አይሰማባቸውም ነበር።«ጎርጎጥ» እያደረጉ ጠጥተው አያውቁም።
2 ነቢዩ ከሙዕሚኖች ሁሉ ነቢያችን ለዓኢሻ ጥልቅ ፍቅር ነበራቸው። እናታችን ዓኢሻ በጠጡበት ኩባያ ከንፈራቸው ያረፈበትን ስፍራ ፈልገው ይጠጡ ነበር።
3 ነቢያችን ወተት በጣም ይወዱ ነበር።
4 ለሰዎች መጠጥ የሚከፋፈል ከሆነ በዕድሜ ቅደም ተከተላቸው ከታላቅ ጀምሮ እንዲሰጥ ያደርጉ ነበር።

5 ነቢያችን ሲጠጡ ተቀምጠው ነበር። ቢስሚላህ በማለት ሶስቴ ይጀምሩ ነበር።

Post a Comment

0 Comments