Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ያልተኮረጀው

ያልተኮረጀው

====
By Abubekr Siraj

ኣንድ ነገር አለስለ ፍቅር፣ወንድማማችነት፣የሀሜት መጥፎነት፣ለሰው ጥሩ መሆን (ለቤተሰብ)፣ሰው መምታት(መግደል)፣ስለ ሰላም፣የቲሞችን ስለመርዳት ወዘተ ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉንም ሁሉም በየፊናው ይሰብካል አምነስቲ፣ዩኒሲኤፍ፣የእምባ ጠባቂ ተቋማት፣ቤተ ክርስትያኖች፣ፍርድ ቤቶች፣የመብት አስጠባቂ ተቋማት ወዘተ ሁሉም ከነቢያችን ሰለላሁአለይሂወሰለም ኮርጀዋል ነገር ግን አንዲት ነገር ብቻ ስትቀር እስዋም ተውሂድ ናት ከላይ የተዘረዘሩትን መልካም ተግባራት ሁሉም ዱዓት ከላይ እንደተጠቀሱት ድርጅቶች ሊጣራ ይችላል። ነገር ግን ማን ነው ደፍሮ ያልተኮረጀችዋን ተውሂድ የሚያስተምር እና ስለሱዋ የሚጣራ?ማን ነው እስኪ ይቺ የነቢያት ተልዕኮ የሆነችውን ርዕስ አንስቶ ኑ ወደርስዋ የሚል?ማነው ሰማይና ምድር የተፈጠሩበትን አላማ ተውሂድን የሚያስተጋባማነው ፈርጡ ነቢያችን ሰለላሁአለይሂወሰለም ዳዕዋቸውን የጀመሩበትን ተውሂድን እርሱም ፈለጋቸውን ተከትሎ ጥሪውን ከተውሂድ የሚጀምር?ማነው አገሩ፣አካባቢው፣አለም ላይ ያለው አላህ ላይ የሚሰራ ትልቁ በደል (ሽርክ) አሳስቦት የሚያስጠነቅቅ?
አላህ በችሎታው ወደ ተውሂድ የሚጣሩ ባሮቹን ይጠብቅልን