እንደሚታወቀው የሰው ልጆች በእውቀት ደረጃቸው፣ በተቅዋቸው፣ በአስተሳሰብ ብልጠታቸው፣ በአስተዋይነታቸው ይበላለጣሉ፡፡ ፊትናም የተለያየ እንደመሆኑ መጠን ሰዎች ለፊትና ያላቸው አመለካከት አቋምና ግንዛቤ ይለያያል ይሁንና ሰዎች ፊትናን በተመለከተ ያላቸውን አቋም በሶስት ደረጃ መክፈል ይቻላል፡፡
1. አዋቂ (ምሁር) አላህ ወፍቆት (ለግሶት) ቁርአንና ሀዲስን በመቅራት ፊትናን ያወቀና ከፊትና የተጠነቀቀና ሰውንም ያስጠነቀቀ ከፊትና በሰላም ነፃ የወጣ ነው በዚህ ላይ የሁዘይፋ ሀዲስ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡ ሁዘይፋ እንዲህ ይላል “ሰዎች ረሱልን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ መልካም ነገር ይጠይቋቸው ነበር እኔ ግን ስለመጥፎ ነገር ነበር የምጠይቃቸው ምክንያቱም እንዳያጋጥመኝ በመፍራት ነው፡፡”
2. የፊትና ተቀባይ የፊትና ባንዲራ አውለብላቢ ጠሞ ሰው የሚያጠም በዚህ ዙሪያ ከሚጠቀሱት ሀዲሶች ውስጥ “ፊትና ትመጣለች የተቀመጠው ከቋሚው የተሻለ ነው የቆመው ከተራማጁ የተሻለ ነው …” ቡኻሪ ዘግበውታል የሁዘይፋ ሀዲስም እንደዚሁ “… በጀሀነም በሮች ላይ ሆነው የሚጣሩ የተቀበላቸውን ወደሷ ወርውረው የሚጥሉ አለ” የሚለው ሀዲስ ይጠቀሳል
3. በፊትና ላይ ጃሂል (መሀይም) የፊትናን አደገኝነት የማያውቅ ነው ይህ ፊትና ላይ ከመግባት ራሱን ካልቆጠበ ወደ ፊትና ከመጣራት ካልተከለከለ በጣም አደገኛ ሁኔታ ላይ ነው የሚወድቀው ምክንያቱም እሱን ከፊትና የሚከለክለው እውቀት ስለሌለው የፊት ባለቤቶች እንደፈለጉ ሊጐትቱት ስለሚችልና ስለሚቀል ነው ለዚህ መሰሉ ሰው የአላህ ቃል ተዛማጅ ነው፡-
وَمِنَ النَّاسِ مَنْ يَعْبُدُ اللَّهَ عَلَى حَرْفٍ فَإِنْ أَصَابَهُ خَيْرٌ اطْمَأَنَّ بِهِ وَإِنْ أَصَابَتْهُ فِتْنَةٌ انْقَلَبَ عَلَى وَجْهِهِ خَسِرَ الدُّنْيَا وَالْآخِرَةَ ذَلِكَ هُوَ الْخُسْرَانُ الْمُبِينُ
‹‹ከሰዎችም (ከሃይማኖት) በጫፍ ላይ ሆኖ አላህን የሚግገዛ ሰው አልለ፡፡ ታዲያ መልካም ነገር ቢያገኘው በእርሱ ይረጋል፡፡ መከራም ብታገኘው በፊቱ ላይ ይገለበጣል፡፡ የቅርቢቱን ዓለምም የመጨረሻይቱንም ከሰረ፡፡ ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው፡፡›› አል ሀጅ 11
http://www.facebook.com/