Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የአላህ ባህሪዎችን በተመለከተ ለብዥታዎች መነሻ ከሆኑት ውስጥ በጥቂቱ:

http://www.facebook.com/asmaewesifat 
ይህ የተውሂድ ክፍል ቀላልና ግልፅ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ብዙ የሙስሊም ቡድኖች ለቁርዓንና ለሀዲስ መረጃዎች እጅ ባለመስጠታቸዉና አጉል ፍልስፍናን በመጠቀማቸው ከትክክለኛው መንገድ ሲያፈነግጡና የተምታቱ ሀሳቦችን ሲያራምዱ ይስተዋላል፡፡ 
ከፊሎቹ የአላህን ባህሪዎች የተመለከቱ መረጃዎች፤ አላህን ከፍጡራን ጋር ስለሚያመሳስሉ አንቀበላቸውም ይላሉ፤ የተለየ ትርጓሜ በመስጠትም መልዕክታቸውን ያዛባሉ። መረጃዎቹን ተቀብሎ ማጽደቅም አላህን ከፍጡራን ጋር ማመሳሰል እንደሆነ ያስባሉ። ከዚህም አልፈው የሀቅ ባለቤቶችን በኩፍር ይፈርጃሉ።

ሌሎች ደግሞ “አላህ በምናውቀው ቋንቋ ነውና የሚያናግረን በቁርዓንና በሀዲስ የአላህን ባህሪዎች የተመለከቱ መረጃዎችን የምንረዳው ፍጡራን ላይ ባወቅነው ትርጉም ብቻ ነው” በማለት የአላህ ባህሪዎች ልክ እንደ ፍጡራን ባህሪዎች እንደሆኑ ይገልጻሉ። መረጃዎችን ከማየታቸው በፊት አላህ ፍጡራኑን እንደማይመስል እና ከፍጡራኑም እርሱን የሚመስል እንደሌለ የሚያስረዱ መረጃዎችን ቢያጤኑ ኖሩ ለዚህ ስህተት ባልተዳረጉ ነበር።

የሚከተለው ምሳሌ በዚህ ጉዳይ ላይ የሰዎች ውዝግብ ምንን መነሻ እንዳደረገ የምናይበት ነው።

የአላህን ከዓርሽ በላይ መሆን በተመለከተ፤ አላህ እንዲህ ብሏል፦

الرحمن على العرش استوى

“አረህማን ከዐርሽ በላይ ከፍ አለ (ሆነ)” (ጣሃ 5)

አንዳንድ ቡድኖች “አላህ ከዓርሽ በላይ ነው” የሚሉ ሰዎች ለአላህ የፍጡራንን ባህሪ ስለሰጡ “ካፊር ናቸው” በማለት ይናገራሉ። በእነርሱ አመለካከት አንድ ሰው “አላህ ከዓርሽ በላይ ነው” ካለ አንድ ፍጡር ከሌላ ፍጡር በላይ እንዲሆን የሚያስፈልጉት ነገሮች ሁሉ ያስፈልጋሉ። የአላህን ከዓርሽ በላይ መሆን “ኢስቲዋዕ” ፍጡራን ከነገሮች በላይ ከመሆናቸው ጋር መለየት አልቻሉም። ስለዚህም የፈጣሪን ኢስቲዋዕ የተቀበለና ያመነ ሁሉ እነርሱ ቀድመው በአዕምሯቸው የቀረጹትን ምስል እንደተቀበለ አድርገው በማቅረብ ‘ካፊር ነው’ ይላሉ። ከእነዚህ ሰዎች መካከል ከፊሎቹ ስሞችንና ባህሪዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን ሁሉ በማጣመም ትርጉም አልባ አደረጓቸው። ስለዚህም «የአላህን ስሞችና ባህሪዎች ትክክለኛ ትርጉም አልባ አድራጊዎች» ‘‘ሙዓጢላህ’’ ተባሉ። ከእነርሱ መካከል ከፊሎቹ ደግሞ እነዚህን መረጃዎች አይተረጎሙም፤ በሌላ በማይታወቅ ቋንቋ እንደተነገሩ ታስበው እንዲሁ ይታለፋሉ፤ በማለት በአዕምሯቸው ከሳሉት ጣዖት ለማምለጥ ሞከሩ። እነዚህ ደግሞ «የአላህ ስሞችና ባህሪዎች ትርጉም አይታወቅም ባዮች» “ሙፈዊዳህ” ተብለው ተሰየሙ። እነዚህ ቡድኖች ባህሪዎችን አያጸድቁም ነገር ግን አቋማቸውን ሲያስረዱ ከሰለፎች አቋም ጋር ለማመሳሰል ጥረት ስለሚያደርጉ ብዙ ሰዎችን ሊያምታቱ ይችላሉ። ሰለፎች የባህሪዎችን ትርጉም ያጸድቃሉ፤ ትርጉሙ አይታወቅም የሚሉት የባህሪዎችን ምንነት “ከይፊያ” ብቻ ነው።

ሌሎች ደግሞ የአላህን ከዓርሽ በላይ መሆን ይቀበላሉ። ይሁንና የአላህን ከዓርሽ በላይ መሆን የሚረዱት ልክ ፍጡር ከፍጡር በላይ እንደሚሆነው ነው። ስለዚህም “አላህ ከዓርሽ በላይ ነው” ስንል ልክ “ሰው ዙፋን ላይ እንደሚቀመጠው ነው” በማለት ያብራራሉ። እነዚህ ፈጣሪን «ከፍጡራን ጋር አመሳሳዮች» “ሙሸቢሀ” ወይም “ሙመሲላ”ይባላሉ።