Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለ አድሉ አስናን ብዥታ የተሰጠ ማስተካከያ

Sadat Kemal Abu Nuh

ለ አድሉ አስናን ብዥታ የተሰጠ ማስተካከያባለፈው ቅዳሜ ‹‹ድንበር ማለፍ›› የሚል ፖስት መደረጉ ይታወቃል፡፡ አብዛኞች ቃጥባሬ፤ አብሬት፤ አልከሶ ላይ ድንበር ታልፏል የሚለውን ከተቀበሉ በኋላ አቡክር አህመድ ላይ ድንበር ታልፏል እንዲህም ሲባል «የአቡበክር አህመድ ፎቶ ፌስቡክ ላይ ተለጥፎ የጀነት ሙሽራ ይባላል» የሚለውን አባባል ድንበር ማለፍ እንዳለበት መቀበል ከበዳቸው፡፡ እውነት ለመናገር ግን ይሄ እራሱ የሚያሳየው ድንበር ማለፉ በተጨባጭ እንዳለ ነው፡፡ ነገር ግን እድሉ አስናን የተባለው ምን እንደሚል ተመልከቱማ=============================================== (ለመሆኑ «የጀነት ሙሽራ» ማለት ምን ማለት ነው?
ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ሁሉም ሰው በሚያውቀው ሀዲስ «ላኢላሃ ኢለሏህ ያለ ሁሉ ጀነት ይገባል» ብለዋል::
እናም «ሙሽራ» ማለት በቀጥተኛው አማርኛ «እጩ» ፤ «ተመራጭ» ማለት ነው:
ከላይ በተጠቀሰው ሀዲስ መሠረት ደግሞ ሁሉም ሙስሊም ለጀነት ታጭቷል ፤
ፈተናውን ያለፈ ጀነትን ያገኛል ማለት ነው::
ስለዚህ ሁሉም ሙስሊም ለጀነት የታጨ ሙሽራ ወይም እጩ ነው ማለት ነው!
ይህ እንግዲህ አማርኛ የሚያቅ ማንኛውም ሰው የሚረዳው ግልፅ አማርኛ ነው:) ===============================================

እንግዲህ ለዚህ አባባሉ መልስ ይሻል ጥቂት ልበል

1) የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹ላኢላሃኢለላህ ያለ ጀነት ይገባል›› ወይም ‹‹ከዱንያ ሲለቅ የመጨረሻ ቃሉ ላኢላሃኢለላህ የሆነ ሰው ጀነት ገባ›› ወይንም ‹‹ላኢላሃኢለላህ ከልቡ ጥርት አድርጎ ያለ›› ወይነም ‹‹በእውቀት ላይ ሆኖ ከአላህ ውጭ በሃቅ የሚመለክ እንደሌለ የመሰከረ›› ሲሉ እንዲሁ ነገሩ ህግና ደንብ የሌለው አይደለም፡፡
ላኢላሃኢለላህ ሸርጥ ያላት መሆኑን ያስይዛል (እውቀት፤ እርግጠኝነት፤ ኢኽላስ፤ እውነተኝነት፤ መታዘዝ፤መውደድ፤ መቀበል፤ ከአላህ ውጭ በሚመለኩት መካድ)


2) አድሉ አስናን እንዲህ ብሏል («ሙሽራ» ማለት በቀጥተኛው አማርኛ «እጩ» ፤ «ተመራጭ» ማለት ነው:)

ስለዚህ እንደፀሀፊው አቡበክር አሕመድ የጀነት ሙሽራ ነው ማለት ለጀነት የተመረጠ ነው ማለት ነው፡፡ ሱብሐነላህ!! አሁን ይሄ አልሸሹም ዞር አሉ” አይሆንም ወንድሞችና እህቶች ደግሞስ በየትኛው አገር አማርኛ ይሆን (ሸዋ፤ ወሎ፤ ጎጃም፤ ጎንደር) ሙሽራ ማለት ‹‹እጩ፤ ተመራጭ›› ማለት የሆነው፤ ወይንም የትኛው መዝገበ ቃላት ላይ ነው እንዲህ ተብሎ የተተረጎመው???

‹‹እጮኛ›› ......... ‹‹እጩ›› የተመራረጡ፤ የተጫጩ ...
‹‹ሙሽራ›› ..........ሁሉን ጣጣ የጨረሰ፤

የአማርኛ ጨዋታው ይቅር እና ሃቁን መቀበል ይበጃል፡፡

3) ዛሬ በዘመናችን ‹‹አቡበክር አህመድ የጀነት ሙሽራ›› የሚሉት የዘመናችን ሰዎች ሲሆኑ፡፡ ረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከሰሃባዎች ጋር የተሳተፉበት ጂሃድ ላይ ከረሱል ጋር አብሮ የዘመተ አንድ ሰው የጠላትን አንገት ሲቀላ ከባድ የሆነ ተጋድሎ ሲፈፅም የነበረ ሰው፤ ሌሎች ሰሀባዎች ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ፊት ‹‹ሸሂድ ነው›› ብለው ሲመሰክሩለት፤ የአላህ መላክተኛ ደግሞ ‹‹የእሳት ነው አሉ››

ኢማሙ ቡኻሪም ይህን ሃዲስ ምእራፉን ሲጠቅሱ ‹‹እገሌ ሸሂድ ነው አይባልም›› ብለው አስቀመጡ፡፡

ኧረ እባካችሁ ደሊል እናክብር!!! አንድ ሰው ሸሂድ ነው፤ የጀነት ነው፤ የጀነት ሙሽራ ነው ብሎ ሊመሰክርለት የሚችለው አላህ እና ወህይ የማይለያቸው መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ብቻ ናቸው፡፡ በሳቸው ሞት ደግሞ ወህይ ተቋርጧል፡፡ ታድያ ይህን ድንበር ማለፍ ላለማስተካከል ዙርያ ጥምጥም መሄዱ እና የሌለን አማርኛ ትርጉም መስጠቱን ማንን ይጠቅማል ሰዎችን ከጥፋት እንዳይወጡ ያደርግ ካልሆነ በቀር፡፡

ከሃቅ በኋላ ጥመት እንጂ ምን አለ???

ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሃቅን ቢመርም ተቀበለው እንዳሉት መቀበል ነው ለሙስሊም የሚገባው፡፡
አላህ ድንበር ከማለፍ ይጠብቀን፡፡