Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኑህ (አለይሂ ሰላም) መርከብ፡፡


የኑህ (አለይሂ ሰላም) መርከብ፡፡
ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ ‹‹የነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና ልክ እንደ ኑህ መርከብ ናት፤ የተሳፈረባት ይድናል፤ ወደ ሀሏ የቀረ (ከነብያችን ሱና) ይሰምጣል›› 
1) የኑህን መርከብን ታሪክ ካስታወስን፤ ያቺ አነስተኛ መርከብ አማኞች እና ከእንስሳት ጥንድ ጥንድ ብቻ ተጫነባት፤ እንሰሳዎቹ ካላመኑት አመፀኞች ተሸለው ነፃ ወጡ (ይህ ትልቅ ትምህርት ነው)

2) ከባድ የአላህ ቁጣ ሲመጣ የሚዳነው አላህን በብቸኝነት በማምለክና የነብያችንን ሱና በመያዝ ነው
ነብየላህ ኑህ ልጃቸው ሰመጠ፡፡ ከዚህም የምንረዳው እምነት በነፍስ ወከፍ ነው፡፡ የነብይ ልጅ በመሆን አይዳንም፡፡

3)ነብያችንም በጣም ለሚወዱዋት አይን ማረፊያ ልጃቸው ፋጢማ (ረድየላሁ አንሃ) ‹‹ከገንዘብ የፈለግሺውን ጠይቂኝ፤ (በአኸይራ ጉዳይ) ነፍስሽን ከእሳት አድኝ›› አሉዋት፡፡ ሁላችንም ተውሂድ እና ሱና ልንይዝ ግድ ይለናል፡፡

4)አላህ ከኑህ ጋር ነጃ ስለወጡት ሰዎች ሲናገር ‹‹ከእርሱ (ከኑህ) ጋር አብረው ጥቂቶች እንጂ አላመኑም››፡፡ ጥቂት ቢሆኑም ግን አላህን በብቸኝነት አምልክው፤ ነብየላህ ኑህን ስለታዘዙ (ሱናውን በመያዝ) አላህ ነጃ አወጣቸው፡፡ ይህም ኡመት ሽርክና ቢድዐን ካልራቀ፤ የአላህ ቅጣት ሲመጣ ኢማሙ ማሊክ እንዳሉት መርከቡዋ ላይ አይሳፈርም፡፡ መርከቡዋ ላይ ያልተሳፈረ ይሰምጣል፡፡
አላህ በተውሂድ እና በሱና ብቻ አንድ ያድርገን፡፡ አላሁመ አሚን፡፡