Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የተዛዙትን ላለመስራት ሰብብ መፈለግ አለም ይጮሃል፤ ማን እንዲሰማው…….


የተዛዙትን ላለመስራት ሰብብ መፈለግ
አለም ይጮሃል፤ ማን እንዲሰማው…….
ከፅሁፉ መሃል የተወሰደ ‹‹ታድያ እኛ ከአምላካችን ጋር ያለን ግንኙነት ሳይቀየር፤ አለም ላይ ያሉ መሪዎች ቢቀያየሩ ምድር ትቀየራለች ተብሎ ይገመታልን???››
አላህ ይህቺን ምድር በትዕዛዙ ከኖርንባት፤ እርሱን በብቸኝነት ካመለክነው እውር አሞራን እንደሚቀልበው ለእኛም ብዙ ሳንጨነቅ ኑሮዋችንን ሊያሳምርልን ቃል ገብቷል፡፡ ከዚህም አልፎ ታላቁን የሚቀጥለው አለም ጀነት ሊያጎናፅፈን ቃል ገብቷል፡፡
የሚያሳዝነው ማናችንም ቢሆን ይህን እውነት እናውቀዋለን፡፡ ከአምላካችን ጋር ያለን ግንኙነት እየተበላሸ መጥቷል፤ ከወላጆቻችን ጋር ያለውም እንደዛው፤ እናት እና አባቶቻችንን ማሸማቀቅ፤ በእኛ ብሶ እነሱን መቆጣት እና ብሎም እናት እና አባትን መሳደብ ብሎም እናቱን የደበደበም አለ፡፡

ታድያ እኛ ከአምላካችን ጋር ያለን ግንኙነት ሳይቀየር፤ አለም ላይ ያሉ መሪዎች ቢቀያየሩ ምድር ትቀየራለች ተብሎ ይገመታልን???

ጥንቆላ፤ ምቀኝነት፤ ግብረሰዶም፤ ዝሙት፤ ወለድ፤ አምላክ የሚጠላው ሁሉ በዘመናችን እየተሰራ ነው፡፡ ፊልም እና ኳስ እያየ አላህ ያዘዘውን ነብያቱ ሁሉ ሰግደው ያሳዩትን ሰላት የሚተው አለ፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሰው ስሞታውን ለማንም አያሰማም፤ መከራውን ‹‹የተባበሩት መንግስታት፤ ዩኒሲፍ፤ ሌላም ሌላም›› በለው ቢሰሙት ቢሰበሰቡ፤ ቢጮህ፤ ዲያስፖራ ቢጮህ ማንም ቢጮህ ምንም አያመጣም፡፡

ፊርአውንን የሚያክል የአለማችን ቁጥር አንድ እርኩስ፤ ነብየላህ ሙሳን (አለይሂ ሰላም) እና ያመኑትን ከነ ሰራዊቶቹ ተከተላቸው፤ አማኞቹ ለሙሳ እንዲህ አሉት ‹‹አረ ደረሱብን›› ሙሳም ‹‹ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው ይመራኛል (ይረዳኛል)›› ሙሳም ያሉት ሆነ ህዝቦች ከአምላካቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ሲስተካከል፤ ከፍጡራን ጋር ያላቸውም ግንኙነት ይስተካከላል፡፡

እስቲ 100 አመት ከመጮህ እና ፍጡራንን ስሙን መከራችንን እዩልን ስሙልን ከማለት፤ መጀመሪያ ለሰራነው ወንጀል ሁላችንም አላህን ምህረት እንለምን፡፡ ከዛም ነብየላህ ያእቁብ(አለይሂ ሰላም) ልጃቸው ነብየላህ ዩሱፍ (አለይሂ ሰላም) ጠፍቶ ያሉትን እናስታውስ፤ ስሞታቸውን ለአለማቱ ጌታ ምንም ለማያቅተው ቻይ አምላክ አላህ ነው ብለው እንዲህ ይላሉ «ጭንቀቴንና ሐዘኔንና የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡» አላቸው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አለም ጦር ሲሰብቅባቸው ‹‹ሃስቡበላህ ወኒእመል ወኪል (አላህ በቂዬ ነው፤ ምንኛ ያማረ ረዳት)›› ነበር ያሉት፡፡

እስቲ የምናፈጥባቸውን የምንገላምጣቸውን አብረናቸው ልንሄድ የምናፍረውን ሽንት እና ሰገራችንን ጠርገው ያሳደጉንን የአደጋ ጌዜ ተጠሪ በመባል የሚታወቁትን፤ ማንም ቢሸሸን የማይሸሹንን እናት እና አባት እስቲ ውለታን ለመመለስ መሞከር ቢቀር በፍቅር አይን እንመልከታቸው፡፡

ሰው የሰራውን ያጭዳል ይባላል፡፡ እኛ ደካማዎች ነን፤ አምላካችን አላህ ግን ሁሉን ነገር በማድረግ ላይ ቻይ ነው፡፡ እሱን ብቻ መፍትሄ እንጠይቅ፤ እሱ በጣም ጥበበኛ ነው፤ ፍርዱም ያማረ ነው፡፡ ቀንም ለሊትም እርሱን እንማፀነው፡፡ እስቲ አላህ መልስ ይሰጠናል የሚለውን ከልባችን እንመንበት፡፡ ለምን እኛ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምንችል ሆነን ለመታየት እንሞክራለን፡፡

አላህ ሁሉን ነገር በማድረግ ላይ ቻይ ነው፡፡

ይብቃኝ ውስጥ ስለሚያደማ ከዚህ በላይ ያለው…… አላህ ሆይ! እኛን አስተካክለን፤ ያንተን ትእዛዝ ከሚሞሉት አድርገን፤ በሃይማኖታችን ላይ ፈተና አታምጣብን፤ ካንተ ጋር ጥሩ ግንኙነት ከሚኖራቸው አድርገን፡፡
አላህ ሆይ! ላንተ ሁሉ አይከብድህ እኛንም በእኛ ላይ የሾምካቸውንም አስተካክለን፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም የአደም ልጆች ፈርጥ ላይ፤ በቤተሰባቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እናም እስከ ቂያማ ድረስ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡