Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለ High School and college ተማሪዎች በ Graduation አላህ ይመሰገናል እንጂ አይታመፅም!!!!

                                 






 


Sadat Kemal Abu Nuh

ለ High School and college ተማሪዎች

በ Graduation አላህ ይመሰገናል እንጂ አይታመፅም!!!!

ሱብሃነላህ ሸይጥጧን ሰዎችን ማጥመም ሲፈልግ ለነሱ አሳቢ መስሎ ሹክ ይላቸዋል፡፡ ሸይጧን 2 አይነት ነው፤ የሰው እና የጂን፡፡ ሁለቱም አሳቢ መስለው ሰዎችን አላህን ከመገዛት ይልቅ የአላህን ቁጣ የሚያደርስባቸውን ተግባር ይጠቁሟቸዋል፡፡
ወደ አርስቱ ስንመለስ

ዛሬ ዛሬ እየተለመደ የመጣ ‹‹ኢስላማዊ ምርቃት (Graduation)›› በማለት መጥፎ ስራን ለማስለም ቆርጠው የተነሱ ሰዎች ያውም በጀመዐ የሚንቀሳቀሱ ሞልተዋል፡፡ 


‹‹የሙስሊም ተማሪዎችን እናስመርቃለን›› ይላሉ፡፡ ከዛ ‹‹ኢስላማዊ›› ብለው፤ አላህ የከለከለውን ነገር ‹‹በኢስላማዊ›› ስም ይተገብሩታል፡፡

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን እናስመርቃለን ብለው፤ ‹‹የእናት፤ የአንዳርጌ፤ የእስኩል ኦፍ ቶሞሮ፤ የሂል ቶጵስ፤ የካቲድራል፤ የሲንት ሜሬ›› እና የመሳሰሉትን ተማሪዎች ወንድ እና ሴቶችን ፎቶ ተነሱ ብለው

- ከለር ፎቶ፤ ቆመው፤ ተቀምጠው፤ በጀመዐ፤ አይናቸውን ተኩለው፤ 45 ዲግሪ ዞረው፤ ወደ ዝሙት እንደሚጣሩ ሴቶች አይናቸውን እያቁለጨለጩ 

- ሴቶች ልፒስቲክ፤ ቻፒስቲክ እና መሰሉን ተቀብተው

- ኢሜል እና ፌስቡክ አድራሻቸውን አብረው መፅሄቱ ላይ አስቀምጠው (ጥሪ የሚመስል)

ሱብሃነላህ፤ ይህ ሁሉ አልበቃቸው ብሎ፤ እነዚሁኑ ተማሪዎች አዳራሽ ውስጥ ያለ መጋረጃ እየተያዩ አስቀምጠው፤ ደግሞ አያፍሩም አሁንም ‹‹ለኢስላም ነው የምንሰራው፤ ኢስላማዊ ምርቃት ነው›› ይላሉ፡፡

ምኑ ላይ ነው ‹‹ኢስላማዊነቱ›› ???

- ሴቶቻችንን ወደ ዝሙት እንደሚጣሩ ሴቶች የሚብለጨለጭ ፎቶ አስነስቶ፤ አይናቸውን ተኩለው፤ የመፅሄት ማስታወቂያ ማድረግ???

- አዳራሽ ላይ፤ ወንድ እና ሴትን ያውም በጣም አፍላ እድሜ ላይ ያሉ ሰዎችን ለዝሙት ፈተና መዳረግ???


ውድ ወንድም እና እህቶች እነዚህን መፅሄት እናዘጋጅላችሁ፤ ‹‹ኢስላማዊ›› ብለው የሚቀርቧችሁን ሰዎች ተጠንቀቋቸው፡፡ የአላህን ቁጣ የምታተርፉበትን ተግባር ነው ‹‹በኢስላም›› ስም የሚተገብሩባችሁ፤ የሚያስተገብሯችሁ፡፡


በ Graduation አላህ ይመሰገናል እንጂ አይታመፅም!!!!

ለውድ እህቶቼ ሆይ! የአማኞች እናት አኢሻ (ረድየላሁ አንሃ) ታላቅ ተምሳሌታችሁ ትሁን፤ እንዲህም ትላለች ‹‹ኡምር ኢብነል ኸጣብ (ረድየላሁ አንህ) እኔ ቤት ከተቀበረ ጀምሮ ፀጉሪን ተገልጪ አላውቅም››፡፡ ታድያ እናንተ እነዚህ አሳሳች ሰዎች ‹‹ለኢስላም›› ነው ብለው እናንተን እየሳቃችሁ፤ የተብለጨለጨ ልብስ ለብሳችሁ መፅሄት ላይ ተነሱ የሚሏችሁ ሰዎች ወደ ጥፋት እየጠሯችሁ አይደለምን???

አላህን እንፍራ ሁላችንም፡፡ መፅሄት አታሚዎች በሙስሊም ሴት እህቶቻችን መነገድ ይቅርባችሁ፤ አላህን ፍሩ፡፡ ሴት ብቻ አይደለም ፎቶውን እንዳይለቅ የተከለከለው፤ ወንዶችም ጭምር እንጂ፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው፤ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡