Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ላ ኢላሀ ኢለላህ


ላ_ኢላሀ_ኢለላህ (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም )የመካ አጋሪዎች (ሙሽሪኮች) ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሠለም) " ላ ኢላሀ ኢለላህ " በሉ ሲሏቸው ይህንን መልስ ሰጡ [ እኛ ለእብድ ባለ ቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን ምንተው ነን? ይሉም ነበር። ] እዚህ አንቀፅ ላይ ምንረዳው ሙሽሪኮቹ ይህንን መልስ የሰጡበት ምክንያት " ላ ኢላሀ ኢለላህ " ካሉ ከአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ውጪ የሚመለኩ ነገሮችን በሙሉ ሰውም ይሁን ጂኒ መላኢካም ይሁን ነብይ ባጠቃላይ እርም ብለው መተው ግድ እንደሚሆንባቸው በሚገባ ስለተረዱ ነበር ። በሌላውም ሁኔታ ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አጎታቸው አቡ ጣሊብ የሞት አፋፍ ላይ ባለበት ሰአት ላይ እንዲህ አሉት " አጎቴ ሆይ ላ ኢላሀ ኢለላህ " በል ይህንን ንግግር ብቻ አላህ ዘንድ ስለ አንተ ምክንያት ማቅረቢያ ይሆነኛል። ሲላቸው
አጠገባቸው አቡ ጀህልና አብደላህ ቢን አቢኡ መያ ነበሩና እንዲህ ሲሉ ከዚህ ታላቅ የምስክር ቃል ከለከሏቸው። " ከዓብዱል ሙጠሊብ እምነት ትዞራለህን? " በማለት ። አሁንም እዚህ ጋር በደንብ በሚገባ ልብ በሉልኝ ። ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ለአጎታቸው ያሉት " ላኢላሀ ኢለላህ " ን በል ነው። ነገር ግን በተለመደ ግንዛቤያቸው አቡ ጀህልና ጓዱ አቡ ጣልብ ይህን ቃል ከመሰከሩ " የአብዱል ሙጠሊብን መንገድ ማለትም ከአላህ ውጪ ያሉ ነገሮች የሚመለኩበት የሆነው የሽርክ መንገድን እርም ማለቱ ስለገባቸው ከዚህ ቃል በአፅንኦት ከለከሉት ። ታዲያ ሙስሊሞች ነን በማለት ይህንን ቃል ሌሊትና ቀን እንደ ትንፋሽ እየደጋገሙ በአላህ ላይ የሚያጋሩ ፡ ነብዩ ድረሱልኝ ሰይድና ኽድር አድኑኝ ፡አብዱል ቃዲር ጀይላኒ
ልጅ ስጡኝ ፡ ሸኾቼ ጌቶቼ ባንቱ ሸሸሁ ፡ሌላም ሌላም። ያ አላህ አያሳዝንም ? አቡ ጀህል የተገነዘበውን እንኳ ብዙ ሙስሊሞች መገንዘብ አልቻልንም። እንዲያውም በዚህ ግንዛቤ እርሱ ተሽሏል ። ምክንያቱም ይህንን ቃል እያነበነበ በተግባሩ ግን እያፈረሰው ትርጉሙን አላበላሽም። አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ የርሱን ንግግ በጥልቀት ከሚገነዘቡት ያድርገን ። አሚን " ላ ኢላሀ ኢለላህ " (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም )
 
by  Sadat Kemal Abu Nuh