Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የ facebook ጠንቋዬችን ጠንቀቅ፡፡


የት እንደምንሞት እና መቼ እንደምንሞት የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው‹‹የምትሞትበትን ቀን›› እነግርሃለሁ የሚል ፕሮግራም…. ተሰርቶ ሰዎች ፖስት እያደረጉት ነው፡፡ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ኢማሙ ቡኻሪ በሰሂሃቸው በዘገቡት፤ ስለ አላህ አንድነት፣ ተውሂድ የሚለው ምዕራፋቸው ላይ የሚከተለውን ያሰፍራሉ
‹‹አላህ ብቻ የሚያውቃቸው ማንም የሚያውቃቸው የሩቅ ቁልፎች አምስት ናቸው፡፡1) ማህፀን ውስጥ ያለውን ማንም አያውቅ አላህ እንጂ2) ነገ ምን እንደሚከሰት አላህ እንጂ ማንም አያውቅም 3) መቼ እንደሚዘንብ አላህ እንጂ ማንም አያውቅም 4) ማንም (ሰው) የት እንደሚሞት አያውቅም አላህ እንጂ (የሚያውቀው)5) ቂያማ መቼ እንደሚቆም ማንም አያውቅም አላህ እንጂ››
አላህ በመቀጠልም እንዲህ ይላል إِنَّ ٱللَّهَ عِندَهُۥ عِلْمُ ٱلسَّاعَةِ وَيُنَزِّلُ ٱلْغَيْثَ وَيَعْلَمُ مَا فِى ٱلْأَرْحَامِ ۖ وَمَا تَدْرِى نَفْسٌ مَّاذَا تَكْسِبُ غَدًا ۖ وَمَا تَدْرِى نَفْسٌۢ بِأَىِّ أَرْضٍ تَمُوتُ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌۢአላህ የሰዓቲቱ ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ዝናብንም ያወርዳል፡፡ በማሕፀኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም ነገ የምትሠራውን አታውቅም፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት አታውቅም፡፡ አላህ ዐዋቂ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡
አንቀፁ ግልፅ የሚያሳየው የት እንደምንሞት እና መቼ እንደምንሞት የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው፡፡አንዳንዶች facebook ላይ ሽርክ አለ ወይ ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ምክንያቱም ጠንቋይ የሚያውቁት መጋረጃ ጋርዶ ብቻ የነገን አውቃለሁ የሚለውን ነው፡፡ ልክ አሁን አዚህ ፖስት ላይ እንደተደረገው የኮምፑተር አፕሊኬሽን ‹‹መቼ እንደምትሞት›› እነግርሃለሁ እያለ አይደለ ወይ??? በሲኒ ይጠንቆል፤ በጋዜጣ ጥንቆላ ጥንቆላ ነው፤ ኩፍርም ነው፡፡ 
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሚከተሉትን ይላሉእንደሚታወቀው ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የነገን አውቃለሁ ስለሚል ሰው የሚከተለውን ተናግረዋል፡፡
የነገን የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹የነገን እውቃለሁ ባይ ዘንድ የሄደ እና እሱን የጠየቀ የ40 ሌሊት ሰላቱን አይቀበለውም፡፡›› ሙስሊም ዘግበውታል
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹የነገን እውቃለሁ ባይ ዘንድ የሄደ እና እሱን የጠየቀ የ40 ለሊት ሰላቱን አይቀበለውም፡፡›› አልባኒ ሰሂህ አ-ተርጊብ ወተርሂብ
አቡ ሑረይሪ እንደተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ወደ ጠንቋይ በመሄድ የሚለው የተቀበለ ሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል›› አቡ ዳውድ አህመድና ሃኪም
ሽርክን እንጠንቀቀዉ፤ ሽርክን አቅልለን አንየው፤ የተውሂድ መሪ፤ የነብያት አባት ኢብራሂም አለይሂ ሰላም ‹‹ጌታዬ ሆይ! እኔን እና ልጆቼን ጣኡት ከማምለክ ጠብቀን›› ነበር ያሉት፡፡ኢብራሂም አለይሂ ሰላም የአላህ ኸሊል፤ የነብያት ሁሉ አባት ከመሆናቸው ጋር ሽርክን ይህን ያህል ከፈሩ እና ከተጠነቀቁ፤ እኛ በጣም ልንጠነቀቀው ይገባል፡፡
አላህ ከማንኛውም አይነት ትልቁም፤ ትንሹም፤ ድብቁም ሽርክ ይጠብቀን፡፡የአላህ ሰላት እና ሰላም በሁሉም የአላህ መልክተኞች ላይ ይሁን፡፡