Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts


ዶሮን ሲያታሏት እንደሚሉት 
‹‹ኢስላማዊ ፊልም እና ድራማ››
ሃይማኖትን ለቢዝነስ ሽፋን ማድረግ ይቅር፡፡

==============
by Sadat Kemal Abu Nuh
በጣም እየገረመኝ እና እየደነቀኝ የመጣ ነገር አለ፡፡ ኢስላማዊ ፊልም እና ድራማ አየተባለ፤ ሙስሊሞችን ከቀጥተኛው መንገድ፤ የሰይጣን መጫወቻ ሊያደርጓቸው ቀን ከሌሌት እየሰሩ ነው፡፡

ተመልከቱ በሁለቱ መሃል ያለው ልዩነት ምንድን ነው
1) የኩራባቸው ደነቀ ፊልም
2) የአህመድ ኑርዬ ፊልም፡፡

ፊልም ኩራባቸው ደረሰው አህመድ ምንድን ነው ልዩነቱ??? አህመድ የደረሰውን ድርሰት ‹‹አስተማሪ ነው›› ብሎ ያስብ ይሆናል ሽፋንም ሲፈልግ ‹‹ኢስላማዊ›› ብሎም ይጠራዋል፡፡ ታድያ እነ ኩራባቸውም ‹‹አስተማሪ›› ብለው፤ ግን ሃይማኖትን ሽፋን ሳያደርጉ ነው የሚያወጡት፡፡

‹‹ኢስላማዊ›› እያሉ የሚሰሩት ፊልሞች ላይ ‹‹አላህ የከለከላቸው ወንጀሎች (ዘፈን፤ መጠጥ ይመስል)›› ጭምር ይኖራቸዋል፡፡ ለምንድን ነው ተብለው ሲጠየቁ፤ ‹‹ለማስተማር ነው›› ብለው ይሞግታሉ፡፡ ይህ ታላቅ ሃይማኖት ኢስላም እንዴት ማስተማር እንዳለብን አስቀምጦ ሲያበቃ፡፡

የመጠጥን መጥፎነት ለማስተማር ግዴታ ሰው ጠጥቶ ፊልም መስራት አለበት የሚል ‹‹የማሃይማን›› እና ኢስላምን የማያውቁ የግሪክ ፍልስፍና ያወራቸው ሰዎች አካሄድ በጣም አላዋቂ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ አሁን እነዚህ ናቸው ወይ ኢስላምን የሚያስተምሩን???

በመቀጠል አርቲስት መሰረት ሰራችው፤ ፎዚያ የምትባል ሴት ሰራችው ምንድን ነው ልዬነቱ??? የነኩራባቸው ፊልም ላይ ለፊልም ነው ተባብለው ይጨባበጣሉ ይሳሳማሉ፤ እዚህ የእኛዎቹ ጋርም ምን ቀረ???

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እነዚህን በህይወታችሁ እና በገንዘባችሁ የሚያላግጡባችሁ እና የሚያሾፉባችሁን፤ በናንተ ላይ ቢዝነስ የሚሰሩባችሁን ሰዎች አንጠነቀቃቸውምን????

ከጥቂት አመት በፊት ያሰቡ መስለው ‹‹የነብያት ፊልም›› ብለው ፊልምን ‹‹አስልመው›› ከዛ ወደራሳቸው የትወና ስራ መጡ፡፡ ተጠንቀቋቸው አስጠንቅቋቸው፡፡

መስጊዶች ከማንኛውም ምስል መፅዳት ሲገባቸው፤ የመስጊድ በሮች ያውም አጅነቢ የሆነች ሴት፤ የአላህን እርግማን የወረደባት ቅንድቧን በመቀንደብ፤ ሊፒስቲክ በመቀባት ከወንድ ጀርባ ወይንም በፊት አክተር ተብላ እንደነ እዛኛዎቹ መሰሎቿ መስጊድ እያበላሹ ነው ያሉት፡፡

‹‹ቢላል የፊልም አዋርድ›› ብለውም ‹‹ሃገር ፍቅር ቲያትር›› ብለው መስከረም 26 ቀጠሮ ነበራቸው፡፡
1) የፊልም ፌስቲቫል የማን ሱና ይሆን ‹‹ሺዓዎች›› ናቸው፡፡ ‹‹የኢራን ፊልም ፊስቲቫል›› እያ በየ አመቱ የሚያከብሩት፡፡
2) ይህ ተግባር ቢላልን ‹‹ማዋረድ›› አይደለምን??? በታላቁ ሰሃባ ስም ኢስላም የጠላውን ተግባር ያውም ‹‹ቅንድባቸውን የተቀነደቡ ሴቶች›› አላህ የረገመው ተግባር ያለበትን፡፡ ፊልም ምርቃት የሚሉት ላይ ‹‹ወንድን እና ሴት›› ያለ መጋረጃ የሚተያዩበትን…….

በጣም የሚገርመው ረመዳን ላይ ነው ልዩ ዝግጅት አድርገው ሰውን ከቀጥተኛው መንገድ የሚያዘናጉት፡፡
አላህ እነሱንም እኛንም ይምራን፡፡ በጣም የሚገርመው ግን ረመዳን ሸይጧን ታስሮበታል በተባለው ወር፤ ሰራዊቶቹ እኛን ወደ አላህ እንዳንቃረብ ቁርዓን በመቅራት ሊያዘናጉን መጥተዋል፡፡ አላህ ከነሱ ተንኮል ኡማውን አላህ ይጠብቀው፡፡

Post a Comment

0 Comments