Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አንዳንድ ሴቶች እና ክረምት



=====================================================================================================================
አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ለወንድም ሆነ ለሴት የአለባበስም ሆነ ስነ ምግባራቸው ምን መምሰል እናደለበት አስቀምጧል፡፡ ክረምት ዝናብ የሚጥልበት ወቅት ነው ይሁን ከክረምት ውጭ፡፡ ዝናብ ደግሞ ጡሃራ (ንፁህ) ነው፡፡ አንዳንድ ሴቶች ልብሳቸውን ውሃ እንዳይነካው በማለት በአንድ እጃቸው ከፍ አድርገው ይይዙታል፡፡ በዚህም አማካኝነት የሴት ልጅ አካሏ (ብሎም ድምፆ አውረት ነው) እየተባለ እነሱ ለአጅነብይ ወንዶች ለአላፊ አግዳሚው ሁሉ እግራቸውን ያሳያሉ፤ የሴት ልጅ ቁርጭምጭሚት ደግሞ አውረት (ሀፍረተ ገላ) ነው፡፡

ድንገት ይሉ ይሆናል መሬት ላይ ያለው ውሃ እንዳይነጅሰን ብለን ነው፡፡ እውነታው ግን ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሴት ልጅን ልባስ መሬት መጎተት አስመልክተው ‹‹ነጃሳ ቢነካው ጡሃራ (ንፁሁ) መሬት ያፀዳዋል›› ብለዋል፡፡
ሴት ልጅ ተገላልጣ በመሄዷ እና ወንዶች እሷን አይተው በሚሰሩት ወንጀል እነሱን ብቻ ሳይሆን እሷንም ከነሱ ላይ ወንጀሉ ሳይቀነስ ያገኛቸዋል፡፡ ታድያ እህቶቻችን እራሳችሁን እስላም ያስቀመጠውን አለባበስ መተግበር ግድ ይላል፡፡

እህቶቻችን ሆይ! ብዙ ማለት አያስፈልግም እውነታው የታወቀ ነው፡፡ የአላህን ትዕዛዝም ተከተሉት፡፡
ውበት ማለት የሚያጓጓው በየአደባባዩ እንደ እቃ ማስታወቂያ ሲታይ ሳይሆንያ አላህ ላንቺ ብሎ ያዘጋጀልሽ ውድ ባልሽ ብቻ ተደብቆ የተቀመጠ ነው፡፡
ውበት ሲለካ ሂጃብ ነው ለካ፡፡
አላህ ምክሩን ከሚቀበሉ ያድርጋችሁ፡፡ አላህ ወንዶችንም ሴቶችንም ጥሩ የእርሱ ባሪያዎች ያድርገን፡፡ድንገት ይሉ ይሆናል መሬት ላይ ያለው ውሃ እንዳይነጅሰን ብለን ነው፡፡ እውነታው ግን ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሴት ልጅን ልባስ መሬት መጎተት አስመልክተው ‹‹ነጃሳ ቢነካው ጡሃራ (ንፁሁ) መሬት ያፀዳዋል›› ብለዋል፡፡ ሴት ልጅ ተገላልጣ በመሄዷ እና ወንዶች እሷን አይተው በሚሰሩት ወንጀል እነሱን ብቻ ሳይሆን እሷንም ከነሱ ላይ ወንጀሉ ሳይቀነስ ያገኛቸዋል፡፡ ታድያ እህቶቻችን እራሳችሁን እስላም ያስቀመጠውን አለባበስ መተግበር ግድ ይላል፡፡እህቶቻችን ሆይ! ብዙ ማለት አያስፈልግም እውነታው የታወቀ ነው፡፡ የአላህን ትዕዛዝም ተከተሉት፡፡ውበት ማለት የሚያጓጓው በየአደባባዩ እንደ እቃ ማስታወቂያ ሲታይ ሳይሆንያ አላህ ላንቺ ብሎ ያዘጋጀልሽ ውድ ባልሽ ብቻ ተደብቆ የተቀመጠ ነው፡፡ውበት ሲለካ ሂጃብ ነው ለካ፡፡አላህ ምክሩን ከሚቀበሉ ያድርጋችሁ፡፡ አላህ ወንዶችንም ሴቶችንም ጥሩ የእርሱ ባሪያዎች ያድርገን፡፡

 Sadat Kemal Abu Nuh