Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኩፍር ንግግር ‹‹ዛር ቆሞለታል››


‹‹ዛር ቆሞለታል›› ===========ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው ይላል የአገሬ ሰው ፡፡ ያለንበት ወቅት የሃይማኖት እውቀት እየመነመነ የመጣበት መሆኑን የሚያሳዩ ስንት እና ስንት ነገሮች አሉ፡፡ ሸሪአን አለመገንዘብ አንዳንዶችን ‹‹ኩፍር›› ንግግር ሁሉ እንደቀልድ እንዲናገሩ አድርጓቸዋል፡፡
‹‹ዛር›› ማለት አገራችን ላይ አብዛኛው እናት እና አባቶች በጣም የሚፈሩት እና የሚከተሉትን ስሞች በተጓዳኝነት ያሉት ናቸው ‹‹ሩሃንያ፤ጢሽጣጣ፤ ቆሌ፤ ሙወከል፤ የእናት አባት አምላክ፤ አቴቴ….›› ይህ ሁሉ ለጂን አምልኮ የተሰጠው ስም ነው፡፡ ስንቶች ጠንቋይ ቤት ይሄዱ እና ዱንያን ፍለጋ (ያው ዱንያን ሰጪው አላህ ብቻ ሆኖ ሳለ) ለፈተና ትንሽ ሰሞን ለጂን ያርዱ እና የተሳካላቸው ይመስላል; በጣም የሚገርመው ከበግ፤ ከዶሮ፤ ብሎም ከከብት የተለያዩ ከለሮችን ለጂን እንዲያርዱ ይታዘዛሉ፡፡ ወለድ ያለው ብድር ተበድረው መኪናዎች፤ ቤቶች ይገዛሉ፡፡

በሙሳ ዘመን የቃሩንን ሀብት አይተው የተሞኙ ሞኞች እንደነበሩት ሁላ፤ በዘመናችን ያሉ ስንቶች ደግሞ ይህን (የጠመጠመ ይሁን ያልጠመጠመ) ጠንቋይ ቤት ሄዶ ለጌዜው ያለፈለት የሚመስል ሰው ሲያዩ ‹‹ዛር ቆሞለታል›› ይላሉ፡፡

ለጊዜው ሰይጣን አምላኪዎች እና ወንጀለኞች የተሳካላቸው ቢመስሉም እውነታው ግን መጨረሻው ያማረው አላህን ለሚፈሩት ነው፡፡
አላህን ከሚፈሩት ያድርገን፡፡ አላህ ሆይ! እውቀትን ጨምርልን፤ አንተን ያማረ ማምለክ እንድናመልክ አግዘን፡፡