Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የከባድም ከባድ

=============
አብደላህ (ረድየላሁ አንሁ) የአላህ መልክተኛን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አላህ ዘንድ ታላቁ ወንጀል የቱ ነው? ብዬ ጠየቋቸው፡፡
እሳቸውም ‹‹አላህ ብቻውን ፈጥሮህ ሲያበቃ፤ በእርሱ ላይ ባላንጣን (ሸሪካን፤ ቢጤን) ማድረግ››
‹‹ይህ ታላቅ በደል ነው›› አልኩ
ከዚህ ቀጥሎስ? ብዬ ጠየቅኩ
እሳቸውም ‹‹ልጄ ምግቤን ይሻማዋል ብለህ ልጅህ መግደል›› ነው፡፡
ከዚህ ቀጥሎስ? ብዬ ጠየቅኩ
እሳቸውም ‹‹ከጎረቤትህ ሚስት ጋር ዝሙት መፈፀም›› ነው አሉ፡፡ ሰሂህ አል ቡኻሪ 6/4477

ከሃዲሱ የምንወስደው ትምህርት
==========================
ሁሉም ወንጀል እኩል አይደለም፡፡ ወንጀሉ አንድ አይነት ሆኖ፤ ከቦታ እና ሁኔታ አኳያ ይለያል፡፡ ለምሳሌ ነፍስ ማጥፋት ከባድ ወንጀል ሆኖ ሳለ፤ የገዛ ልጅህን ምግቤን ይሻማኛል ብሎ መግደል ደግሞ ከባድ ነፍስ ማጥፋ ነው፡፡

ጎረቤት ሃቁ ሊጠበቅለት፤ እሱ ለስራም ይሁን ለዘመቻ በሄደበት፤ ሚስት እና ልጆቹን በአማና ጥሎ ሄዶ ከእርሱ ሚስት ጋር ዝሙት መስራት እንደማንኛውም ዝሙት አይደለም፡፡

የወንጀሎች ሁሉ ታላቅ ወንጀል፤ በአላህ ላይ ማሻረክ እና ማጋራት፡፡ አላህ ብቸኛው ፈጣሪ ከሆነ ለምን የአምልኮ ክፍሎች ከእርሱ ውጭ ለፍጡራን ይደረጋሉ? ይህ ነው የበደሎች ሁሉ በደል፡፡

የመካ ሙሽሪኮች ሲጠየቁ ሰማይ እና ምድርን ማን ነው የፈጠረው? አለሙን የሚያስተናብረው ማን ነው? እናንተን የፈጠራችሁ ማን ነው? እና ሌሎች የአላህን ብቸኛ ፈጣሪነት የሚያረጋግጡ ጥያቄዎች ሲጠየቁ ‹‹አላህ›› ብለው መልስ ይሰጣሉ፡፡

ነሳራዎች ሰማይ እና ምድርን ማን ነው የፈጠረው ሲባሉ ‹‹አንድዬ›› ብለው አንድ መሆኑን እና ብቸኛ ፈጣሪ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

ታድያ ለምን ይሆን ከአላህ ውጭ ያሉ መላኢካም ይሁን (ጂብሪልን፤ ሚካኤልን (አለይሂሙሰላም)) ይመስል፤ ነብያት (ኢሳን፤ ኡዘይርን፤ ሙሃመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም))፤ ሷሊሆችን (አልይ፤ ሁሴን፤ ሀሰን፤ ፋጢማ (ረድየላሁ አንሁማ)) እና የመሳሰሉት ይመስል ከአላህ ውጭ ፍጡራን ሆነው ሳለ የሚመለኩት????????????

አላህ ለእርሱ ፍፁም አምልኮዋቸውን ካደረጉት ባሪያዎቹ ያድርገን፤ ከከባባድ ወንጀሎችም ይጠብቀን፡፡