Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፈጣሪ ለመኖሩ ማስርጃው ምን ድን ነው?

ፈጣሪ ለመኖሩ ማስርጃው ምን ድን ነው?

አንድ ጊዜ ሰዎች አቡ ሀኒፋ ዘንድ መጡና ፈጣሪ ለመኖሩ ማስርጃው ምንድን ነው? ምን ማስርጃ አለ??? ብለው ጠየቁ  እሳቸውም በሚቀጥለው ቀን እንዲመጡ ነግረው ሸኛቸው ::

በቀጣዩ ቀን መጥተው መረጃ አገኘህ አሏቸው?

እሳችውም እንዲህ አሉ:- አይ ቆይ እሱን ተዉና እኔ በዚህ ሰዓት በከባድ ሁኔታ በሃሳብ ተዘፍቅያለው

ጠያቂዎቹ:- ምንድን ነው ምያሳስብህ?

እሳችውም :- አንዲት ትልቅ መርከብ በውሃ ላይ ትሄዳለች በውስጧ በጣም ብዙ ነገሮች ተጭነዋል አቅጣጫዋን ጠብቃ ሄዳ ሄዳ
የተፈለገበት ቦታ ስትደርስ ዕቃውም ይወርዳል ሁሉም ክንውን በአግባቡ ይከ ናውናል መንገድም አትስትም ነገር ግን ይህች መርክብ ሹፌር
(ሚቆጣጠራት) አካል በላዩዋ ላይ የለም አላቿው::

ጠያቂዎቹ:- ይሄማ የማይምስል ነገር ነው እንዴ ጭንቅላት የለህም እንዴ? እንዴት ይሆናል???

እሳቸውም :- እናንትስ ታዲያ  አሏቸው! ይህ ትልቁ ዓለም
ከላይም ከታችም የምታዩት ነገሮች በዚህ መልኩ በረቂቅ ሁኔታ የሚከናወነው ክስትት የሚቆጣጠረው አካል የለም ትላላቹ??? የቱ ነው
ሚበልጠው??? ብለው መልስ ሰጧቸው::



እንዲሁም በሌላ አጋጣሚ አንድ መምህር በክፍል ውስጥ ሕጻናት ልጆችን ስብስቦ እያስትማረ እንዲህ ይላቸዋል

መምህር:- ልጆች ሆይ ይህን ሰሌዳ ትመለከታላቹ ?

ልጆቹ:- አዎ!!!

መምህር:-ስለዚህ ሰሌዳ አለ ማለት ነው

ልጆቹ:- አዎ

መምህር:- እሺ ይህን  ጠረጴዛውን ትመለከታላቹ ?

ልጆቹ:- አዎ!!!

መምህር:-ስለዚህ ጠረጴዛው አለ ማለት ነው

ልጆቹ:- አዎ

መምህር:- እሺ አላህን ትመለከታላቹ ?

ልጆቹ:- አናይም!

መምህር:-ስለዚህ  አላህ የለም ማለት ነው :: ሚታይ ነገር
ብቻ ነው ያለው አላቸው::

በዚህ ጊዜ አላህ በሰዎች ላይ ሁጃውን (ማስርጃውን) ሊያቆም ሲፈልግ ከመሀከላቸው አንዱ ልጅ ተነሳና

ቲቸር ጥያቄ አለኝ አለ! ፈቀደለትና ወቶ ከመምህሩ ጎን ቆመና :-

ልጁ:-ተማሪዎች የአስተማርያችንን ዐቅል (አዕምሮ) ትመለከታላቹ?

ልጆቹ:-አናይም!!!

ልጁ:-ስለዚህ ዐቅል (አዕምሮ) የለውም መጅኑን (እብድ) ነው አላችው!!

መምህሩ ምን ማድርግ ይችላል የራሱ አካሄድ ነው:::

በሰፈሩት ቁና ..... ይልሃል ይሄ ነው!!
ከ ኡስታዝ ኢልያስ አህመድ በአላህ ማመን ከሚለው ደርስ የተወሰደ