Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ላሰው / ላሺውየፈለገ ደረጃ ቢኖርህ/ሽ፤ የፈለግከውን ብትለብስ/ሽ አትፈር / አትፈሪ

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ አንድ የኢስላምን ውበት ያላወቀ ሰው የተናገረውን ይዤ ነው፡፡ እርሱም እንዲህ ሲል ተናገረ‹‹የእኛ ሰው ነው ያልሰለጠነው፡፡ ሸራተን ገብቶ ጣቱን ይልሳል››፡፡ ይህ በጣም ከባድ ንግግር ነው፡፡ ይህ ሰው የኢስላምን እውቀት አለማወቁ እንጂ ዛሬ ሳይንቲስቶች በእጅ መብላት፤ ጣትን መላስ ያለውን ጥቅም ደርሰውበት ኢስላምን እየተከተሉ ነው፡፡
የአላህ ባሪያ ሆይ! ዶክተር ብትሆን፤ ባለስልጣን ብትሆን፤ ሃብታም ብትሆን፤ በማህበረሰቡ የተከበርክ ሰው ብትሆን፤ የእውነተኛ የአንድ ሰው ትልቅነት የሚለካው የነብዩ ((ﷺ)) ሱና የትም ቦታ ላይ ሳያፍርበት ሲተገብረው ነው፡፡

መርሳት የሌለብን ነብዩ ሙሃመድ ((ﷺ)) ማለት የአላህ መልክተኛ ናቸው፡፡ የአላህ መልክተኛ ብቻ መሆናቸው ይበቃናል፡፡ አላህ ማለት ያ የፈጠረን፤ አምልኮ ለእርሱ ብቻ የሚገባው፤ ስም እና ባህሪያት ያሉት፤ የሚጠቅመንን እና የሚጎዳንን የደነገገ እና የከለከለ፤ በመልክተኛው አማካኝነት አብራርቶ ያሳየ ነው፡፡

አንዳንዶች ደግሞ ምግብ እየበሉ በግራ እጃቸው መጠጥን ይጠጣሉ፡፡ በቀኝህ ጠጣ ተብሎ ሲጠየቅ እንዲህ ሲል ወይንም ስትል መልስ ትሰጣለች ‹‹ብርጭቆው ከሚቆሽሽ ብዬ ነው››፡፡ ሸይኽ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ሲሉ መለሱ ‹‹የአላህ ዲን ከሚቆሽሽ ብርጭቆው ይቆሽሽ››፡፡ የሚገርመው ግን አብዛኛው ሰው ‹‹ሰው በጠጣበት አልጠጣም››፤ ‹‹ንፁህ ብርጭቆ ስጡኝ›› ይላል፡፡ ታድያ ለምን ይሆን የነብያችንን ((ﷺ))ሱና ትቶ፤ ነብያችን ((ﷺ))እንዳሉት ‹‹ሸጥጧን በግራው ይበላል ይጠጣል›› ለምን ሸይጧንን ይመሳሰለል?????

ኢስላም ባስቀመጣቸው ህግጋቶች፤ መንገዶች፤ እና ተግባሮች እያፈሩ ዘመናዊነት እና ስልጣኔ አለን???
ካሃዲያን ሃይማኖታችንን ተቹብን እያሉ ሁሌ ከመጮህ መጀመሪያ እራሳችን ሃያማኖታችን ላይ ባሉ ህግጋቶች ወደን ተቀብለናልን???
መጀመሪያ እራሳችንን ይህን ጥያቄ እንጠይቅ፡፡

በአላህ ጌትነት፤ በኢስላም ሃይማኖትነት፤ በሙሃመድ ነብይ እና መልክተኝነት ወደድኩ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኛው፤ በቤተሰቦቻችው፤ በባልደረቦቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

መርሳት የሌለብን ነብዩ ሙሃመድ ((ﷺ)) ማለት የአላህ መልክተኛ ናቸው፡፡ የአላህ መልክተኛ ብቻ መሆናቸው ይበቃናል፡፡ አላህ ማለት ያ የፈጠረን፤ አምልኮ ለእርሱ ብቻ የሚገባው፤ ስም እና ባህሪያት ያሉት፤ የሚጠቅመንን እና የሚጎዳንን የደነገገ እና የከለከለ፤ በመልክተኛው አማካኝነት አብራርቶ ያሳየ ነው፡፡
አንዳንዶች ደግሞ ምግብ እየበሉ በግራ እጃቸው መጠጥን ይጠጣሉ፡፡ በቀኝህ ጠጣ ተብሎ ሲጠየቅ እንዲህ ሲል ወይንም ስትል መልስ ትሰጣለች ‹‹ብርጭቆው ከሚቆሽሽ ብዬ ነው››፡፡ ሸይኽ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ሲሉ መለሱ ‹‹የአላህ ዲን ከሚቆሽሽ ብርጭቆው ይቆሽሽ››፡፡ የሚገርመው ግን አብዛኛው ሰው ‹‹ሰው በጠጣበት አልጠጣም››፤ ‹‹ንፁህ ብርጭቆ ስጡኝ›› ይላል፡፡ ታድያ ለምን ይሆን የነብያችንን ((ﷺ))ሱና ትቶ፤ ነብያችን ((ﷺ))እንዳሉት ‹‹ሸጥጧን በግራው ይበላል ይጠጣል›› ለምን ሸይጧንን ይመሳሰለል?????
ኢስላም ባስቀመጣቸው ህግጋቶች፤ መንገዶች፤ እና ተግባሮች እያፈሩ ዘመናዊነት እና ስልጣኔ አለን???ካሃዲያን ሃይማኖታችንን ተቹብን እያሉ ሁሌ ከመጮህ መጀመሪያ እራሳችን ሃያማኖታችን ላይ ባሉ ህግጋቶች ወደን ተቀብለናልን???መጀመሪያ እራሳችንን ይህን ጥያቄ እንጠይቅ፡፡
በአላህ ጌትነት፤ በኢስላም ሃይማኖትነት፤ በሙሃመድ ነብይ እና መልክተኝነት ወደድኩ፡፡የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኛው፤ በቤተሰቦቻችው፤ በባልደረቦቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡