Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስልጣን ፈላጊው የነ ሃሰን ታጁ ቡድን እንዲህ ይላል

ስልጣን ፈላጊው የነ ሃሰን ታጁ ቡድን እንዲህ ይላል
==========================
‹‹ሃሰን ታጁ ሃያትህን አላህ ያርዝመው የዚህ አለም ብቸኛው አስተማሪ !!!!!››
በከፈሩት ፔጅ ‹‹ዾክተር ኢድሪስ እና ኡስታዝ ሐሰን›› በሚባለው ላይ፤ በዚሁ ፔጅ ስም የሚከተለው ኮሜንት ተፅፋል
‹‹ማህይም ብሎ ማለት በነፍስያው የሚሄድ ነው ። አዋቂን መዝለፍ ማለት ከሞትም በላይ ሞት ነው ። ሃሰንን እንዲህ አለ ብሎ ማለት እውቀትን መጨፍለቅ ነው ።ሃሰን ታጁ ሃያትህን አላህ ያርዝመው የዚህ አለም ብቸኛው አስተማሪ !!!!! ›› November 22 at 11:45pm
ትንሽ መልስ እንስጣቸው
1) ‹‹ማህይም ብሎ ማለት በነፍስያው የሚሄድ ነው›› ብለዋል፡፡ ጥሩ ነው፤ ታድያ ሃሰን ታጁ ራድዮ ላይ ቀርቦ የሃዲስ እውቀት ሳይኖረው ‹‹ስለ ሙዚቃ መሳሪያ የመጡት ሃዲሶች በጠቅላላ ደኢፎች ናቸው›› ብሏል፡፡ እውነታው ግን አል-ቡኻሪ በሰሂሃቸው ላይ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹ከኔ ኡመቶች ሙዚቃ መሳሪያ የሚፈቅዱ አሉ…..››፤ ስለ ፊልም ሲፈላሰፍ እና በሌሎችም ጉዳዬች ላይ ሀሰንም ይሁን ኢድሪስ ነፍሳቸውን ነበር ሲከተሉ የነበረው፤ የሸሪዓ ልጓም ስሜታቸውን ፍሬን አስይዞለት አያውቅም
2) ‹‹አዋቂን መዝለፍ ማለት ከሞት በላይ ሞት ነው›› ብለዋል፡፡ ማን ነው አዋቂው??? ኡለማዎችን ወደ ሃቅ የሚጣሩ ሰዎችን ‹‹ጠባቦች›› እያለ የሚጠራው ማን ነው??? ማን ነው የተዘለፈው??? ሃሰን ታጁም ይሁን ሌላ ሰው ስህተት አለበት ማለት መዘለፍ ነው ወይ??? መዝለፍ እና የባጢል ባለቤቶችን ማንገስን ለምን ለይተን አናውቅም፡፡
የማንም ሰው ክብሩ ሊነካ አይገባም፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ዲንን ሲንድ እያየን ዝም እንበለው ማለት አይደለም፡፡ ‹‹መዝለፍ›› የሚለውን እናንተ እንዳላችሁት ከሆነ፤ ከናንተ በላይ ዘላፊ የለም፡፡ ማስረጃውም ሁሌ የምትደጋግሙት ነገር አለ ‹‹ወጣቱ የሌሎችን ሃሳብ አይቀበልም›› ያው ሃቅ አንድ ስለሆነ ‹‹ሽርክ እና ቢድዓን›› ወጣቱ አይቀበልም፡፡ ዛሬ ግን እናንተ ሰውን የምትወቅሱበትን ተግባር ከወጣቱ በላይ ተክናችሁበታል፡፡ እሱም የናንተን ሃሳብ ሰው ስላልተቀበላችሁ ‹‹ሆደ ሰፊ›› መሆን አቅቷችሁ ‹‹ወጣቱንም›› ይሁን ሌላውን የናንተን ሃሳብ ያልተቀበለ ሁላ ትሞልጫላችሁ፤ ብሎም ‹‹ሃሰንን እንዲህ አለ ብሎ ማለት እውቀትን መጨፍለቅ ነው›› ብላችሁ ወደ ቡድናዊነታችሁ እና ‹‹ከናንተ ውጭ ያለን እንደማትቀበሉ›› የናንተን ሃሳብ እስካልተቀበለ ድረስ አሳያችሁን፡፡ ከዚህ የበለጠ ጠባብብነት አለ ‹‹በራሳችሁ ሎጊክ›› መሰረት??? ፖለቲከኞች ከሁለት ፊት በላይ ነው ያላቸው በተመቻቸው እና ያስኪደናል ባሉት ፊት ይቀርቡሃል፤ ሁሌም ውርደት እንዳጋጠማቸው ነው፡፡ የከፋው ፖለቲከኛ ደግሞ ይህን ታላቅ ሃይማኖት ‹‹ኢስላም›› ስልጣን ለመያዝ ሽፋን የሚጠቀምበት ነው፡፡
3) ‹‹ሃሰንን እንዲህ አለ ብሎ ማለት እውቀትን መጨፍለቅ ነው›› ብለዋል፡፡ አደለም ሃሰን ታላላቅ ኡለማዎች እንኳን ሲሳሳቱ ‹‹እዚህ ጋር ተሳስተዋል›› ይባላሉ፡፡ ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ ‹‹ሁላችንም ንግግራችን የሚያዝለት እና የሚጣልበት አለ፤ የዚህ ቀብር ባለቤት ብለው (የነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቀብር አሳዩ›› ታድያ ሃሰን ታጁ ያውም የት እንደቀራ የማናውቀው ተርጓሚ፤ ያውም የትርጉም ስራው ላይ (የራሱን ሃሳብ በመጨመር እና እርሱ ያልተመቸውን በመቀነስ) የሚታወቅ ሰው ተሳስቷል ብሎ ለምን ተነገረ ብሎ መደስኮር ‹‹ጠባብነት ነው›› ይልቁንስ ከሀሰን እና እድሪስ ወጣ በሉና ቁርዓን እና ሀዲስን የጥንት የጠዋት የሰለፍ ኡለማዎችን ተመልከቱ፤ ምን ያህል እውቀት ይዘው ግን እራሳቸውን ዝቅ እንደሚያደርጉ ታያላችሁ፡፡
4) ‹‹ሃሰን ታጁ ሃያትህን አላህ ያርዝመው የዚህ አለም ብቸኛው አስተማሪ !!!!! ›› ብለዋል፡፡ በጣም የሚገርመው ‹‹የዚህ አለም ብቸኛው አስተማሪ !!!!! ›› የሚለው ነው፡፡ ጅራፍ እራሱን ገርፎ እራሱ ይጮሃል አሉ፡፡ እነ ሀሰን በፅሁፎቸቸው ላይ ከሚታወቁበት ውስጥ ‹‹የነሱን ሃሳብ ያልተቀበለን ቡድንተኛ፤ የአንድ ሰው ተከታዬች›› አድርጎ ማቅረብ ሲሆን፤ ዛሬ ይሀው የነሱ ደረሳዎች እነ ሃሰን በቀረፃቸው መሰረተ ‹‹የዚህ አለም ብቸኛው አስተማሪ !!!!! ›› ብለውት ቁጭ አሉ፡፡ ይህ ሌሎች ኡለማዎችን አስተማሪዎችን በጅምላ መጨፍጨፍ አይሆንምን???
‹‹ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም›› እነዚህ ሰዎች መቼ ይሆን የሚማሩት ሁሌ ‹‹ወጣቱ፤ ወጣቱ›› እያሉ እራሳቸውን በጣም እንደ ትልቅ በመውሰድ ገደል ገቡ፡፡ ወጣትን ያላግባብ መውቀስ ምን ይባላል፡፡ የነሱ ተከታዮችም ወጣቶች ናቸው፤ ያውም ሱሪያቸውን መሬት ለመሬት የሚጎትቱ፤ ፂማቸውን የሚላጩ፤ ፊልም እና ድራማ እያሉ፤ ሴት እና ወንድ የሚደበልቁ፡፡ የነርሱ ተከታይ ወጣቶች የፖለቲካ ቻናላትንን እና ዜና አውታሮችን ሲያገላብጡ ይኖራሉ፡፡ ቂርዓትም አሊም ስር ቁጭ ብለው ቀርተው አያውቁም፡፡ በሳምንት እሁድ ፒያሳ አወልያ ከሚሰጣቸው ‹‹የፖለቲካ እና ስልጣን›› ትምህርት ውጭ፡፡
ታድያ ለምን ይሆን ተከታይ ወጣቶቻቸውን የማይመክሩት???
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹በወጣቶች ድልን ተሰጥቼያለሁ›› ብለዋል፡፡ ስለዚህ ወጣቱን ዝም ብሎ ሁሌ ከመውቀስ ይልቅ ከወጣቱም ተማሩ፡፡ በግድ እንምራችሁም አትበሉን ‹‹ስልጣን የሚፈልግን ሰው አላህ አይረዳውም፤ ከናንተ ውስጥ ስልጣን የማይፈልገውን ሰው ሹሙት›› ብለዋል ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኞቹ ሁሉ ላይ ይሁን፡፡