Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አቤት ያምርጥ እና አደበኛው ትውልድ


አቤት ያምርጥ እና አደበኛው ትውልድ  የሰሃባዎች፣ የታቢኢዬች፣ የአትበአ ታቢኢን፣  ተውሂድ እና ሱናን ጨብጦ፣ ከሽርክ እና ቢድአ ተጠብቆ፣ የጌታው ውዴታ አግኝቶ፣  ከነብያችን ጋር ጉርብትና በጀነት ላይ ቃል ተገብቶለት፣ ዱንያ ላይ በጠላቶች ላይ ድልን ተጎናፅፎ፣ ለሚከተለው ትውልድ ሃይማኖቱን በሰላም ሲያስተላልፍ። ከዛ ምርጥ ትውልድበሀኀላ በራሳቸው የቢድአ አስተያየት የሚደነቁ፣ ያልታዘዙትን የሚሰሩ፣ የሚናገሩትን የማይሰሩ ሰዎች ተተኩ። በቢድአቸውም ላይ ዘወተሩ፣ አላህም መልክተኛውን  በመቃረናቸው ውርደትን አቀመሳቸው። የበላይ የሆነውን እስልምና፣ "የበላይ ልናደርገው ነውበማለት ሃይማኖቱ ላይ የሌለን ድሪቶ ተበተቡበት። አላህ ጠላትን በነሱ ላይ ሾመባቸው። ነብያችን እና ሰሃባዎች፣ ከዛም ምርጡ ትውልድ ያልሰራውን በመስራት  ወደአላህ እንቃረባለን ከማለት የበለጠ ጥመት ምን አለ??? የሚከተሉትን ቢድአዎች ይመስል።  

         1) ሽርክ እና ድንበር ማለፍ የሞላው መውሊድ  
         2) ከሰላት በሀኀላ ኢማሙ ወደ ህዝቡ ዞሮ ዱአ ማድረግ  
         3) ሸእባን 15; ሚእራጅ እና የመሳሰሉት በጣም የሚገርሙት ደግሞ  የዘመናችን ሌላው መጤ የጥመት ቡድን፣ የፖለቲካ ድርጅት የሆንው (እስልምናን ለስልጣን የሚጠቀመውኢኽዋነል ሙስሊሚን ደግሞ የተከታዩ ቁጥር እንዳይቀንስበት  ሽርክ እና ቢድአ ሲወገዝ "አትበታትኑን"ይላሉ። መቼ አንድ ተሆነና??? ሽርክ እና ቢድአመቼ አንድ ያደርጋሉ??? ነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምእና ምርጡን ትውልድ የተከተለ በቁጥር ቢያንስም እስከ ቂያማ ድረስ የበላይ እና የድል ባለቤቶች መሆናቸው በነብያችን አንደበት ተነግሯል። ነፍሴንም ወንድም እና እህቶቼንም አላህን በመፍራት፣  የነብያችን እና የሰሃባዎችን መንገድ አጥብቆ በመያዝ ላይ አደራ አደራእላለሁ።             ተውፊቅ ከአላህ ነው።

Post a Comment

0 Comments