Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሳያውቁት ሃርድ ላይ መውደቅ….. በ facebook and social media’s


አላህ ይጠብቀን፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! አላህ በጣም ከሚጠላው እና ከከባድ ወንጀሎች ቁጥር አንዱ፤ ሽርክ ነው፡፡ ነብያቶች ለህዝባቸው እያንዳንዱን ጉዳይ ከማብራራት አልተቖጠቡም፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሽርክ አይቶቹን ዘርዘርውልና፡፡
-ታላቁ
-ትንሹ እና
- ድብቁ
ዛሬ ነፍሴን በመጀመሪያነት ከዛ እናንተን ማስታወስ የፈለግኩት ስለ ትንሹ ሽርክ እና እኛ ለዲን ነው ብለን እየተጠቀምን ስላለነው facebook and social media’s ነው፡፡

አላህ በሃዲሰል ቁድስ ላይ ሶስት ሰዎችን የውመል ቂያማ መጀመሪያ ፍርድ እንደሚሰጣቸው እና ሶስቱም ወደ እሳት እንደሚሄዱ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ተናገሩ፡፡ ሙጃሂድ፤ አሊም፤ እና ሀብታም ነበሩ፡፡ ስራን ሰርተው ነበር፤ አላህ እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ ዱንያ ላይ ጀግንነት፤እውቀት፤ ገንዘብ እንደሰጣቸው እና ምን እንደሰሩበት ሲጠየቁ፤ እነሱም የአላህን ዲን የበላይ ለማድረግ እንደሞቱ፤ እንዳስተማሩ እና ገንዘብ እንደሰጡ ሲናገሩ፤ አላህ ሁሉንም ዋሽታችኋላ ይላቸዋል፡፡

ይህ ሃዲስ እንደሚታወቀው ስራቸውን ለአላህ እየሰራን ነው ብለው፤ ለሰዎች ይዩልኝ እና ይስሙልኝ ጉድ የከተታቸው ናቸው፡፡ አላህ ከዚህ አስከፊ በሽታ ይጠብቀን፡፡

facebook and social media’s ላይ ፖስታችን like ተደረገ ወይንስ አልተደረገም ብለን የሚያሳስበን ሰዎች በጣም ስራችንን ልንመረምር ይገባናል፡፡ ምክንያቱም የእኛ ስራ አላህ የደነገገውን እስልምና ለሰዎች ቢመራቸውም ሃቁን ማስተላለፍ እንጂ like ማግኘት አይደለም፡፡

እኛን ሊያሳስበን የሚገባው አላህ ስራችንን ወዶታል ወይ የሚለው ብቻ ነው፡፡ አላህ ደግሞ አንድን ስራ ይወዳት ዘንድ፤ ኢኽላስ እና ሙታበአ ማሟላት ግዴታ ነው፡፡

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ለአላህ የእውነተኛ ባሪያ መሆናችንን እና የአላህ መልክተኛን ሱና ሙሉ በሙሉ በቻልነው አቅም ለመከተል መጣራችንን እናረጋግጥ፡፡

ስራቸው ለአላህ የሚያጠሩ፤ የመልክተኛውን ሱና የሚከተሉ ያድርገን፤ ሙስሊሞች ሆነንም ይግደለን፡፡
አላህ ሰላት እና ሰላም በሁሉም መልተኞች ላይ ይሁን፡፡