Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አላህ ሆይ! ለሰጠሀኝ እስልምና እና ለሱና አመሰግንሃለሁ፡፡፡፡


===============================
33፤33፤33፤1
33፤33፤34
33፤33፤33
10፤10፤10
11፤11፤11
25፤25፤25፤25

ከሰላት በኋላ ስድስቱ (6ቱ) የተረጋገጡ የዚክር አይነቶች
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከሰላት በኋላ አላህን 3 ግዜ ምህረት ይለምኑታል (ኢስቲግፋር በማድረግ) ከዛ ………… ከዛ
1) ሱብሃነላህ 33 ግዜ፤ አልሃምዱሊላህ 33 ግዜ፤ አላሁ አክበር 33 ግዜ እና ላኢላሃ ኢለላህ ዋህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሃምድ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር (ሙስሊም 597) ብሎ መጨረስ
2) ሱብሃነላህ 33 ግዜ፤ አልሃምዱሊላህ 33 ግዜ፤ አላሁ አክበር 34 ግዜ (ሙስሊም 596)
3) ሱብሃነላህ 33 ግዜ፤ አልሃምዱሊላህ 33 ግዜ፤ አላሁ አክበር 33 ግዜ (ቡኻሪ 843፣ ሙስሊም 595)
4) ሱብሃነላህ 10 ግዜ፤ አልሃምዱሊላህ 10 ግዜ፤ አላሁ አክበር 10 ግዜ (ቡኻሪ 6329)
5) ሱብሃነላህ 11 ግዜ፤ አልሃምዱሊላህ 11 ግዜ፤ አላሁ አክበር 11 ግዜ (ሙስሊም 595)
6) ሱብሃነላህ 25 ግዜ፤ አልሃምዱሊላህ 25 ግዜ፤ አላሁ አክበር 25 ግዜ እና ላኢላሃ ኢለላህ 25 ግዜ (ነሳኢ 1351 አልባኒ ሰሂህ ብለውታል)
አብደላህ ኢብን አምር እንዲህ ይላሉ ‹‹የአላህ መልክተኛን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በቀኝ እጃቸው (ጣቶች) ሲቆጥሩ አይቻለሁ›› አቡ ዳውድ 5065.
-የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እየቀያየርን ማለቱ ይመረጣል፡፡
-ሁሉም የነብያችን ሱናዎች ናቸው እና፡፡
-ሌላው ዚክርን በቀኝ እጅ ማድረግ፡፡
******
በጣም ልብ ሊባል የሚገባው ዚክርን በጣም እየፈጠኑ ‹‹የሚሉትን እስከማያውቁት ድረስ እና የእጅ ጣቶችን ፈጥኖ በማሸት›› ሳይሆን፤ ረጋ ብሎ አላህን ማውሳት ነው፡፡
የአላህ መልክተኛ ሁሉን ቅን መንገድ አሳይተዋል፡፡ አሰጋገዴን አይታችሁ ስገዱ ብለዋል፡፡ ከ13 አመት በላይ ሰላት ሲያሰግዱ በሰላት ውስጥም ይሁን ከሰላት ውጭ ምን ማድረግ እንዳለብን አሳይተዋል፡፡ እሱን ብቻ እንከተል፤ ይህ በቂያችን ነው፡፡
አላህን በእውቀት ከሚያመልኩት እና የመልክተኛውን ሱና ከሚከተሉት ያድርገን፡፡