Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዱዓአችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምን ማድረግ አለብን?



ዱዓአችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምን ማድረግ አለብን?

 ዱዓአችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች የትኞቹ ናቸው?

ዱዓአችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በትንሹ አምስት መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅብናል::

  1.  አል-ኢኸላስ:- ዱዓአችን በፍጹም ለአላህ ብቻ ተብሎ የሚደረገ መሆን አለበት። ከእዩልኝ እና ይስሙልኝ እንዲሁም ለማንኛውም ምድራዊ ፍላጎት የጠራ መሆን ይጠበቅበታል።
  2.  ሙታበዓ፡‐ የመልእክተኛውን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፈለግ እና ተስተምህሮ የተከተለ መሆን አለበት።
  3. በአላህ ላይ መተማመን እርሱ ምላሹን ይሰጠኛል ብሎ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል። ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም " ጌታችሁን እርሱ ምላሽ የሚሰጣችሁ መሆኑን በመተማማን እርግጠኛ ሆናችሁ ለምኑት " ብለዋልና።
  4. ዝንጉ አለመሆን፡‐ አላህን በምንለምንበት ወቅት ከመዘናጋት ርቀን በንቃት ልባችን ለአላህ የተናነሰ እና እሱን የሚከጅል ሆኖ መሆን አለበት። ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም " በዝንጉ ልቦና የሚደረግን ዱዓእን የማይቀበል መሆኑን እወቁ " ብለዋልና።
  5.  ያለምንም ማወላወል በቁርጠኝነት አላህን መለመን ያስፈልጋል።  የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም « አንዳችሁ "አላህ ሆይ!  ከፈለክ ማረኝ"፣ "አላህ ሆይ!  ከፈለክ እዘንልኝ" ብሎ አይበል። ይልቁን አላህን ሲለምን በቁርጠኝነት ጥያቄውን ያቅርብ፤ አላህ ይፈልገውን ያደርጋል እሱን የሚያሰገድደው የለም።» ብለዋልና።


ዱዓችን ተቀባይነት እንዳይኖረው የሚያደርጉ ነገሮች የትኞቹ ናቸው? 

ዱዓችን ተቀባይነት እንዳይኖረው የሚያደርጉ ነገሮች ብዙ ናቸው። ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።

⛔️ የተከለከሉ ነገሮችን መብላት፣ መጠጣት፣ መልበስ እና በእነሱ አካልን ከመገንባት ለመቆጠብ ፍቃደኛ አለመሆን።

⛔️ መቻኮል እና ዱዓእን መተው። ማለትም ለዱዓው በቶሎ ምላሽ ለማግኘት መቻኮል እንዲሁም ምላሽ አላገኘሁም ብሎ ዱዓን ከማድረግ መቆጠብ።

⛔️ ከዱዓው በኃላ አላህ የከለከላቸውን ነገሮች በመፈፀም የአላህ እዝነት እንዳይወርድ ሰበብ መሆን።

⛔️ አላህ ግዴታ ያደረጋቸውን ነገሮች መተው አለመፈፀም። ለምሳሌ በመልካም ከማዘዝ ከመጥፎ ከመከልከል መቆጠብ።

⛔️ በወንጀል ወይም ዝምድናን በመቁረጥ ዱዓእ ማድረግ።


✍️ ጣሀ አህመድ

Post a Comment

0 Comments