Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የዓሊም #ሞት መቼም የማይደፈን #ቀዳዳ ነው#

 

የዓሊም #ሞት መቼም የማይደፈን #ቀዳዳ ነው#
የአንድ ዓሊም ሞት ምድርና ነዋሪዎቿ ላይ የሚያስከትለው ክፍተት እስከ ቂያማህ ቀን ድረስ ሊሸፈንና ሊደፍን የማይችል በጣም ትልቅ ክፍተትና ቀዳዳ ነው።
ዓሊምና ደጋግ ሰዎችን በሞት ማጣት የምድርን ከፊል አካል ወይም ከምድር ድርሻችን የሆነውን መቀመጫ ቤታችንን ከማጣት በላይ ነው።
ሰማይ ያለዋክብት ውበቷ እንደሚቀንሰው ሁሉ ምድርም ዑለማዎችን በሞት ስታጣ ውበቷን ታጣለች፤ በወንጀል ተሞልታ ከስፋቷ ጋር ለነዋሪዎቿ ትጠባለች።
የዑለማዎችን ምድር ላይ የመኖር ጥቅም ከሰው አልፎ አዕምሮ አልባ የሆኑ እንስሳት ሁሉ ያውቃሉ! ዓሳ ባህር ውስጥ፣ ጉንዳንም ጉድጓዱ ውስጥ ሆኖ ሰዎችን መልካም ነገር ለሚያስተምሩና የፍጡራን ሐቅ እንዲጠበቅ ለሚያደርጉ አዋቂዎች ኢስቲግፋር ያደርጋሉ!
ግን ብዙ አቅል የሚያንሳቸው ሰዎች የዒልምና የዑለማዎችን ደረጃ ዓሳና ጉንዳን የሚያውቀውን ያክል እንኳ አውቀው በህይወት እያሉ አይጠቀሙባቸውም ለዑለማዎች መሞትም የቅንጣት ያክል ቦታ አይሰጡም!
በተቃራኒው ግን አንድ ኳስ ተጫዋች ወይም የፊልም ተዋናይ "ጸረ-መልካም ጸባይ- ሞተ ቢባል መኖር ያስጠላቸዋል።
ያው ሁሉም እቃ ውስጡ ላይ የያዘውን አይደል የሚያፈሰው!?
በዛሬው ዕለት ምድራችን ታላቅ ዓሊም አታለች (ክቡር ሸይኽ ሳሊሕ አል-ሉሐይዳን "رحمه الله"
ሸይኹ ከዒልም ጋር ተግባርና መልካም ስነ-ምግባርን የታደሉ፣ የትምህርት መድረካቸው ላይ ከቃሉ ዒልም በላይ ከዒልም የሚፈለገውን ቁም ነገር ከአደብና ግርማ-ሞገሳቸው በተግባር የሚያስተምሩ ኢማም ነበሩ።
لعَمْرُكَ ما الرَّزِيَّة فَقْد مال
ولا شاةٌ تَمُوتُ ولا بَعِيرُ.
ولكنّ الرَّزِيَّة فَقْدُ فذ
يمُوتُ لِمَوْتِهِ خَلْقٌ كَثِيرُ.
"አደጋ ማለት ንብረትን ማጣት አይደልም፤
የበግ ወይም የግመል መሞትም አይደልም።
ይልቅ ከባድ አደጋ ማለት በርሱ መሞት ብዙ ሰዎች የሚሞቱ የሆነን አቻ የሌለውን ድንቅ ሰው ማጣት ነው።
ለሞቱ ዑለሞቻችን አላህ ይዘን
ያሉትን በዓፊያ ያቆይልን የምንጠቀምባቸውም ያድርገን!
اللهم اغفر لعبدك الصالح صالح اللحيدان وارفع درجته في عليين، "آمين".
إن القلب ليحزن وإن العين لتدمع ولا نقول إلا ما يرضي الرب وإنا على فراقك يا شيخنا ووالدنا لمحزونون، فإنا لله وإنا إليه راجعون.

Post a Comment

0 Comments