Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢትዮጵያ፣ የገጠር ልጅ፣ የከተማ ልጅ ዘረኝነት፣ ፖለቲከኞች፣ አንድ አምላክ አላህ።


ኢትዮጵያ፣ የገጠር ልጅ፣ የከተማ ልጅ ዘረኝነት፣ ፖለቲከኞች፣ አንድ አምላክ አላህ።
– ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካ ውስጥ የምትገኝ ሀገር ናት፣
– በውስጧ 80 የሚጠጉ ብሄር ብሄረሰቦች አሉ፣
– ሀገሪቱ ላይ መጥፎም ጥሩም ታሪኮች አልፏል፣
መናናቅ፣ አንዱ እራሱን የበላይ ማድረጉ ሌላውን የበታች ማድረጉ ለማንም አይበጅም።
እዚህች ሀገር ላይ ያሉ ብሄር ብሄረሰቦች በንግድ፣ በጋብቻ ተሳስረዋል።
አንዱ አንዱን አልፈልግም ወይንም አይፈልጉኝም ሊል አይገባም።
ሁሉም በዚህች ሀገር ላይ የየራሱ ድርሻ አለው።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አብዛኛው ቀለባቸው ከክፍለ ሀገራት ነው የሚመጣው።
የክፍለ ሀገር ሰዎች መድሀኒቶች ሌሎች የእለት ከለት መገልገያ ቁሶች ከዋናው ከተማ ነው የሚደርሳቸው (በአውሮፕላን የሚገባው)።
ስለዚህ የአዲስ አበባ ሰው ከተማይቱ ብትሰለጥን በአስተሳሰብ ከፍ ያለ ቢመስለውና የክፍለ ሀገር ሰው በአስተሳሰቡ ደካማ ቢመስለው ከባድ ስህተትን እየፈፀመ ያለው የከተማ ሰው ነኝ ባዩ ነው።
የገጠር ቤተሰቦች መሰረተ ልማት ሳይሟላላቸው በከባድ መከራ ልጆች ያሳድጋሉ። የቋንቋ፣ የ exposure ክፍተት እና ጉድለት አለ። በዚህ ሁኔታ አንድ አንዱን መናቅ ሳይሆን መተዛዘን እና መከባበር ነው ያለብን።
ፖለቲከኞች ሆይ! ሆደ ሰፊ እና አስተዋይ ሁኑ። አንድ ሀገር ላይ የመጠፋፋት፣ የመናናቅ ፖሊሲ የትም አያደርስም።
በንግድና በጋብቻ የተሳሰረ ዜጋ አንዱ የአንዱን ቋንቋ እና ባህል እያከበረ እና ሳይንቅ ሊኖር ይገባዋል።
ሀገሪቱ ትልቅ ችግር ውስጥ ገብታለች። ይህ ችግር አንዱን ዘር ወይንም አንዱን ክልል አለየም። ሁሉም የችግሩ ተጠቂ ነው። ስለዚህ ችግሮቻችንን በጋራ ለመፍታት ሁሉም በጋራ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በመሳተፍ ሁሉን (ገጠሬውንም ከተሜውንም) ተጠቃሚ ያደረገ መፍትሄ እንድናገኝ አንድ አምላክ፣ ብቸኛው ፈጣሪ አላህን እንለምነው።
ይህች ሀገርም ይሁን ሌሎች ሀገሮች ሀይል አለን፣ ብቃት አለን ብለው ፈጣሪን በረሱ ቁጥር ለውድቀት እና ለእርስ በእርስ ችግር ይዳረጋሉ።
የፖለቲከኞችን ስም እና ገድል አላህ ለእኛ ከዋለው ውለታ እና ውዳሴ በላይ ስናወሳቸው ዝቅጠት ውስጥ እንወድቃለን።
ሃይልም ጥበብም የአላህ ነው። ሀገራችን ላይ ብዙ ጊዜ ከእናት በላይ አዛኝ የሆነው አላህ ብዙ ደም አፋሳሽ ጉዳዮችን ሲያሳልፍልን አይተናል። እኛ ግን ውለታውን ከማመስገን ይልቅ በዘፈን መደለቅ፣ መጮህ ብሎም የፖለቲካ ሰዎችን ከአላህ በላይ ማወደስ ላይ ተውጠናል።
ዘረኝነት እየተባለ አንዱ አንዱን ሲከስ ይታያል። ዘረኝነት የጥቂቶች መገለጫ አይደለም። ዘረኝነት ማለት የራስን ዘር ከፍ ማድረግና የሌላን ዘር መናቅ ነው። ይህ በሽታ ሁሉ ያለበት ዘረኛ ነው። ይህ በሽታ አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ አብዛኛው ተለክፎበታል። አንድ ሰው በራሱ ቋንቋ ስላወራ ዘረኛ አይባልም። ይህ ማንነቱ ነው። ቋንቋ መግባቢያ ነው። እንዲያውም ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ጠንካራ ሀገር ስላልሆነች እንጂ ትምህርት "በእንግሊዘኛ" የሚሰጥባት፣ እንደ ቻይና ጀርመን ያሉ ሀገራት በራሳቸው ቋንቋ ነው ዶክትሬት ድረስ የሚማሩት። የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሌላ የሀገሩን ቋንቋ ቢያውቅ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ አይሆንም። አሳዛኙ ሰዎችን በዘረኝነት የሚፈርጀውን ሰው እራሱ ሙልጭ ያለ ዘረኛ ሆኖ ታገኘዋለህ። ዘረኝነት ማለት የራስን ዘር ከፍ ማድረግ ወይንም የሌላን ዘር መናቅ ነውና ይህ በሽታ ከሌለብህ ብቻ ዘረኛ አይደለሁም በል እንጂ ከዚህ ውጭ አንተም ከምትኮንነው ነገር አልጠራህም።
ስጨርስ ኢትዮጵያዊያን ሆይ! በመከባበር፣ ባለመናናቅ የዚህችን በጣም ብዙ resource ያላት ሀገር ለማናችንም በቂ ሆና እናገኛታለን። በመናናቅ በመተቻቸት እነዚህን ሁሉ ማንም ሳይጠቀምባቸው ከስረው ይቀራሉ።
አላህ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን። መሪንም ተመሪንም ያስተካክለን። እውነተኛ መከባበር፣ መቻቻል ያለባት ሀገር ያድርግልን።
https://t.me/SadatTextPosts

Post a Comment

0 Comments