Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሒድን በ3 መክፈል ቢድዐ ነው ?





ተውሒድ ተውሒዱ ሩቡቢያተውሒዱል ኡሉሂያእናተውሒዱል አስማእ ወስሲፋትየተሰኙ ሶስት ክፍሎች እንዳሉት በሰፊው ይታወቃል ፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች አንዳንድ የስሜት ተከታዮች የተውሒድን በዚህ መልኩ ለሶስት መከፈል መጤ ቢድዐህ ነው በማለት በፅኑ ሲያወግዙ ይታያሉ፡፡ አንዳንዶቹም የዚህ ክፍፍል ጠንሳሽ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንደሆኑ ይሞግታሉ ፡፡በርግጥ የተውሒድን ለሶስት መከፈል የሚቃወሙ ሰዎች የተቃውሟቸው ቀዳሚ ሰበብ በተውሒዱል ኡሉሂያህ እና በተውሒዱል አስማእ ወስሲፋት ላይ ያላቸው ብልሹ አቋም እርቃኑን እንዳይቀር መስጋት ነው፡፡ ብዙዎቹ እነዚህ አካላት በሚሰቀጥጥ መልኩ የሙታን አምልኮ ውስጥ የተነከሩ ናቸው፡፡ ከዚህም አልፎ በአላህ ስሞችና መገለጫዎች ጉዳይ ከጥንቶቹ ጀህሚያህ እና ከሙዕተዚላህ ጥመቶች በሰፊው ይጋራሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህን ጥፋቶች እንደ ፅድቅ የሚቆጥር አካል በቅጡ ባልያዘው የተውሒድ ትምህርት ላይ ትችት ቢሰነዝር ብዙም የሚደንቅ አይደለም ነገር ግን መታወቅ ያለበትተውሒድ ለሶስት ይከፈላልየሚሉ ሰዎች ማስረጃዎችን ተከትለው ከማስተጋባታቸው ባለፈ በምንም መልኩ ኢስላም ውስጥ አዲስ
ነገር አለመጨመራቸው ነው፡፡ ያለውን አልካዱም፡፡ የሌለንም አልጨመሩም፡፡ ለነኚህ የተውሒድን ለሶስት መከፈል በፅኑ ለሚያወግዙ ሰዎች ጠቅለል ያለ መልስ መስጠት ይቻላል፡፡

          ሶስቱም የተውሒድ ክፍሎች ቁርኣን ውስጥ ያሉ ናቸው እርግጥ ቃል በቃልተውሒድ ለሶስት ይከፈላልየሚል የቁርኣን አንቀፅ ወይም ሐዲሥ የለም፡፡ ይሁን እንጂ ቁርኣንን እና ሱናን በጥሞና ለሚከታተል የሶስቱም የተውሒድ ክፍሎች መልእክት ፍንትው ብሎ ይታያል፡፡ (አላህ የሁሉም ነገር ፈጣሪ ነው፡ ) ( ትፈሩት ዘንድ እናንተንም ከናንተ በፊት የነበሩትንም የፈጠራችሁ ነው፡፡ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይን ጣራ ያደረገላችሁ፣ ከሰማይም ውሃን ያወረደላችሁ፤ በሱም ለናንተ ሲሳይ ይሆን ዘንድ ከሰብል ያበቀለላችሁ ነው) እና የመሳሰሉ ስለ አላህ ፈጣሪነት፣ ስለ ስልጣኑ፣ ስለ ሲሳይ ሰጪነቱ፣ ስለ ሁሉን አስተናባሪነቱ የሚያትቱት ማስረጃዎች "የተውሒዱ ሩቡቢያን" መልእክት እንደያዙ ህሊና ላለው ሁሉ አይሰወርም፡፡

          (ሀይማኖትን ለሱ ጥርት አድርገው አላህን እንዲያመልኩት እንጂ አልታዘዙም፡፡)አላህን አምልኩ ከሱ ሌላ አምላክ የላችሁም) (በየህዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣኦትንም ራቁ፡፡ በማለት በርግጥም መልእክተኛን ልከናል፡፡) (አንተን ብቻ ነው የምናመልከው ባንተ ብቻም ነው የምንታገዘው) የሚሉትና መሰል መልእክት የያዙ አንቀፆች ተውሒዱል ኡሉሂያ የሚባለውን የተውሒድ ክፍል እንደያዙ ግልፅ ነው፡፡ 

          (የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡)(በልእሱ አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው፡፡ አልወለደም፤ አልተወለደም፡፡ ለእሱም አንድም ብጤ የለውምየሚሉትና መሰል አንቀፆች የተውሒዱል አስማእ ወሰሲፋትን መልእክት እንደያዙ ለማን ይሰወራል?! 

 ታዲያ የትኛው የተውሒድ ክፍል ነው በቁርኣንም በሱናም ውስጥ የሌለው? የነዚህ ሰዎች ተቃውሞ

            ቁርኣን ውስጥ የሚገኙ ምእራፎችን ቆጥሮ 114 እንደሆኑ መናገርቢድዐህ ነው፡፡ ቁርኣን ውስጥ 114 ሱራዎች አሉ የሚል ቃል የለምናከማለት ተነጥሎ የሚታይ አይደለም፡፡ እንዲህ አይነት ሂሳብ በህሊና ላይ ማመፅ እንጂ ሌላ ሊባል አይችልም፡፡ እንጂማ ጌታችን አላህ የሶስቱንም የተውሒድ ክፍሎች መልእክት ደግሞ ደጋግሞ በቁርኣኑ ላይ ገልጿል፡፡ 

           ለምሳሌ ሶስቱም የተውሒድ ክፍሎች በአንድ አንቀፅ ላይ የተገለፁበትን እንመልከት፡፡ (እሱ) የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ላለው ጌታ ነው፡፡ ስለሆነም ተገዛው፤ እሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ ለእሱ አምሳያ ታውቅለታለህን?” [መርየም፡ 65]

ያስተውሉ!!! በመጀመሪያው አረፍተ-ነገር ላይ የጌትነቱ ተውሒድ አለ፡፡ በሁለተኛው ላይ ደግሞ የአምልኮት ተውሒድ አለ፡፡ በሶስተኛው ላይ ደግሞ የስሞቹና የመገለጫዎቹ ተውሒድ አለ፡፡ ስለዚህተውሒድ ለሶስት ይከፈላልሲባል ቁርኣን ውስጥ ያሉ ተውሒድ-ነክ ማስረጃዎችን መርምሮ ሶስት መልክ እንዳላቸው ማስፈር እንጂ ያለ ማስረጃ አዲስ ትምህርት መፍጠር አይደለም፡፡ ይህን አስመልክተው ሸይኽ አብዱርረሕማን ኢብኒ ናሲር አልበራክ እንዲህ ይላሉ፡-
አንዳንድ የስሜት ተከታዮችና ብልሹ አላማ ያነገቡ ሰዎች ይህን የተውሒድን ለሶስት መከፈል ይቃወማሉ፡፡ ፈጠራ እንደሆነም ይገልፃሉ፡፡ ይሄ ከንቱ ማሳሳቻ ነው፡፡ ይሄ አከፋፈል ፈጠራ ከሆነ በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች፣ በተለያዩ ርእሶችና የአሕካም ስያሜዎች ላይ የሚገኙ ከዑለማእ የተላለፉ ክፍፍሎች ሁሉ ፈጠራ ናቸው ማለት ነው፡፡ እውቀቶቹ በተጨባጭ በነብዩ ዘመን የነበሩ ናቸው፡፡ ነገር ግን የአከፋፈሉ ስያሜዎችና ሙያዊ ቃላት አልነበሩም፡፡ ልክ እንዲሁ የተውሒድ ክፍሎችም ሁላቸውም በቁርኣንና በሱናህ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ያም ሆኖ ግን ሙያዊ ቃላቱ ማለትም ተውሒድ ለዚህ ለዚህ ከፈላል የሚለው በነዚህ ገለፃዎች መግለፁ አዲስ ነው፡፡ [ሸርሑ ተድሙሪያህ፡ 47]

     በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች ብናስስ ተመሳሳይ ክፍፍሎች ይገኛሉ፡፡ በሶላት፣ በውዱእ፣ በዘካህ፣ በፆም፣ በሐጅና በሌሎችም የፊቅህ ብይኖች ብንገባ በቁርኣንና በሐዲስ ቃል በቃል ያልተጠቀሱ በተለያዩ ቁጥርና ስያሜ የተገደቡ መስፈርቶችን፣ ግዴታዎችን፣ ህግጋትና ደንቦችን፣ ሙስተሐቦችን የሚጠቁሙ ክፍፍሎችንና ሙያዊ ቃላትን በብዛት ማገኘት ይቻላል፡፡ ይህን እውነታ ጀማሪ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኪታቦችን ያንቧተረ ሁሉ አያጣውም፡፡ እነኚህን ክፍፍሎች ሲመለከት ማንም የቢድዐህ አጀንዳ ውል አይልበትም፡፡ ምክንያቱም በቁርኣንና በሱናህ ውስጥ በተጨባጭ የሚገኙ እውነታዎችን ለማስተማር በሚመች መልኩ ተንትኖ መመደብ እንጂ ማስረጃ ውስጥ የሌሉ ጉዳዮችን መሰንቀር እንዳልሆነ ግልፅ ነውና፡፡ ተውሒድን ለሶስት ስንከፍልም በተመሳሳይ፣ ቁርኣንና ሱናህ ውስጥ ያሉ የተውሒድ መልእክቶችን በሶስት መደብ ማስቀመጥ እንጂ አዲስ ፈሊጥ መፍጠር አይደልም፡፡ ስለዚህ በየትኛውም
የእውቀት ዘርፍይህን ያህል ክፍሎች አሉትይህን ያህል መስፈርቶች አሉትየሚያበላሹት ይህን ያህል ናቸው” … ማለት እውቀትን አመቺና ቀላል በሆነ መልኩ ለማቅረብ እንጂ ቁጥሮቹ በራሳቸው አምልኮት ሆነው አይደለም፡፡ እናም ክፍፍሉ የአቀራረብ ስልት እንጂ በራሱ ግብ አይደለም፡፡ ዲያ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ በተውሒድ ትምህርት ላይ ቂም ያረገዙ አካላት ያለወትሯቸው ቢድዐን የሚዋጉ በመምሰል የተውሒድን ለሶስት መከፈል ከፈጠራ ጋር በማቆራኘት አልፎም ከስላሴ ጋር በማመሳሰል ሲያወግዙ ማየት የሚደንቅ ነው፡፡ ምነው ደግሞ ወጥ በሆነ መልኩ ሁሉንም ቢድዐ በየእርከኑ በተዋጉ፡፡ ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ በሌላ መልኩ እንመልከተው፡፡ ሶስቱም የተውሒድ ክፍሎች በተቃራኒያቸው የበለጠ ግልፅ ይሆናሉ፡፡ የነኝህ የተውሒድ ክፍሎች ተቃራኒ ሶስት መልክ ያለው ሺርክ ወይም ክህደት ነው፡፡ በነዚህ የተውሒድ ክፍሎች መልእክቶች የማያምን ያለጥርጥር ከተቃራኒያቸው ላይ ይወድቃል፡፡ የነኝህን የተውሒድ ክፍሎች መልእክት ሙስሊም ሆኖ የሚያስተባብል አይገኝም፡፡ በአላህ ብቸኛ ፈጣሪነት፣ በብቸኛ አምላክነቱና ልዩ በሆኑ ስሞቹና መገለጫዎቹ የሚያስተባብል ሙስሊም ከቶ ከወዴት ይገኛል?! እንዲያውም ላኢላሃ ኢለላህየምትለዋ ቃለ-ተውሒድ ሶስቱንም የተውሒድ ክፍሎች ጠቅልላ እንደያዘች ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ ይናገራሉ፡፡ ከአላህ ሌላ በሐቅ የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን ማሳየቷ የተውሒዱል ኡሉሂያን መልእክት በቀጥታ ያመላክታል፡፡ የተውሒዱ ሩቡቢያን መልእክትም እንዲሁ በውስጧ አቅፋ ይዛለች፡፡ መፍጠር፣ መለገስ፣ ማቀናበር፣የማይችል አምላክ እውነተኛ አምላክ ሊሆን አይችልምና፡፡ ተውሒዱልአስማእ ወስሲፋትንም እንዲሁ ታመላክታለች፡፡ መልካም ስሞችና ሙሉእ የሆኑ መገለጫዎች የሌለው ሙሉእ አይደለምና፡፡ ሙሉእ ካልሆነ ደግሞ እውነተኛ አምላክም ፈጣሪም ሊሆን አይችልም፡፡ [አልሙኽተሶሩልሙፊድ፡ 24]

አሁን ደግሞ የተውሒድን ለሶስት መከፈል ከጠቆሙ ዑለማዎች ውስጥ ጥቂቶቹን እንጥቀስ፡፡

1. አቡ ሙሐመድ ዐብዱላህ ኢብኒ ሙሐመድ አንነይሳቡሪይ አልሒሪይ ረሒመሁላህ (328 .)-
የተውሒድ መሰረቶች ሶስት ናቸው፡ አላህን በጌትነቱ ማወቅ፤ በአንድነቱ ለሱ ማፅደቅ እና በጥቅሉ ከሱ ባላንጣዎችን መንሳትይላሉ፡፡ [አልሒልያህ፡ 10/356]
2. ኢብኑ በጧህ አልዑክበሪ (387 .) እንዲህ ይላሉ፡-
በፍጡር ላይ ግዴታ የሆነው በአላህ ላይ የማመን መሰረቱ ሶስት ነገር ነው፡፡ አንደኛ፡ ባሪያው የአላህን ጌትነት በማመን በፈጣሪ መኖር ከማያምኑ አራቋቾች የተለየ ሊሆን ነው፡፡ ሁለተኛ፡ የአላህን አንድነት በማመን በፈጣሪ መኖር አምነው ግን ከሱ ጋር ተጋሪ ካደረጉት አጋሪዎች የተለየ ሊሆን ነው፡፡ ሶስተኛ፡ አላህ እራሱን የገለፀባቸው እንደ እውቀት፣ ችሎታ፣ ጥበብና ሌሎችም መገለጫዎች ባለቤት እንደሆነ ማመን፡፡” [አልኢባናህ፡ 693-694]
3. አቡበክር አጥጦርጡሺ ረሒመሁላህ (520 .)-
በጌትነቱ፣ በብቸኛነቱ እንዲሁም ለራሱ በመሰከረባቸው መልካም ስሞቹ፣ በላቁ መገለጫዎቹ እና በሙሉእ መታወቂያዎቹ እንመሰክራለንይላሉ፡፡ [ሲራጁልሙሉክ፡ 1/7]

እነዚህ ሶስቱም ዐሊሞች 728 .. ከሞቱት ኢብኑ ተይሚያ በብዙ ዘመን የቀደሙ መሆናቸውተውሒድን ለሶስት መክፈል በኢብኑ ተይሚያ የተጀመረ ነውየሚሉ ሰዎች ሙግት ከንቱ ቅጥፈት እንደሆነ የሚያጋልጥ ነው፡፡
4. ኢብኑ አቢልዒዝ አልሐነፊይ ረሒመሁላህ (792 .) እንዲህ ይላሉ፡-
ተውሒድ ሶስት ክፍሎችን ያካትታል፡፡ አንዱ የአላህ መገለጫዎችን የሚመለከት ርእስ ነው፡፡ ሁለተኛው ጌትነቱን የሚመለከት ተውሒድ ሲሆን አላህ ብቻ የሁሉ ነገር ፈጣሪ እንደሆነ መግለፅ ነው፡፡ ሶስተኛው የአምልኮቱ ተውሒድ ነው፡፡ እሱም ጥራት ይገባውና የላቀው አምላክ በብቸኝነት ሊመለክ ባለ ሐቅ መሆኑንና ተጋሪ እንደሌለው የሚገልፀው ነው፡፡” [ሸርሑ አጥጦሓውያህ፡ 1/77]

         በነገራችን ላይ እነዚህ የተውሒድን ለሶስት መከፈል የሚቃወሙ ሰዎች መልኩን ይቀይራሉ እንጂ እነሱም ተውሒድን ይከፍላሉ፡፡ ለምሳሌ ከዒልመል ከላም አንጃዎች ውስጥተውሒዱን ፊዝዛትተውሒዱን ፊስሲፋትእናተውሒዱን ፊልአፍዓልብለው ለሶስት የሚከፍሉ አሉ፡፡ [አልሚለል ወንኒሐል፡ 1/42] [ሪሳላህ ዒልሚትተውሒድ፡ 40] [ኒሃየቱልኢቅዳም፡ 90]
ሌሎችም እንዲሁየተራው ህዝብ ተውሒድየልዩዎች ተውሒድእናየእጅግ ልዩዎች ተውሒድብለው ለሶስት መደብ የሚከፍሉ አሉ፡፡ ለእንዲህ አይነቱ ብልሹ አከፋፈል የዝሆን ጆሮ ይስጠን ያሉ ሰዎች ቁርኣን እና ሱናን መሰረት በማድረግ እንዲሁም ታላላቅ ዑለማዎችን በመከተል ተውሒድን ለሶስት መክፈልን ሲቃወሙ ማየት እጅጉን የሚደንቅ ነገር ነው፡፡ የአላህ ፈቃዱ ከሆነ በቀጣይ በሌላ ርእስ እንገናኛለን፡፡

ኢብኑ ሙነወር (አስ ሱንና መጽሔት ግንቦት 2009 የተወሰደ)

Post a Comment

1 Comments