ወንድሜ!
የፖለቲከኞችን ሴራ ተከትለህ ማንንም በዘሩ ሳቢያ አታጥቃ። ሰዎችን በዘራቸው ሳቢያ መግደል ቀርቶ ማንቋሸሹ ብቻውን
የጃሂሊያ ስራ እንደሆነ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናግረዋል። "የእነከሌ ዘር ነው" በሚል ሸውራራ ምክንያት
በአሰቃቂ ሁኔታ ነፍስ ማጥፋት ሲታከልበት ወንጀሉ የት እንደሚደርስ አስበው።ነገ በቂያማ ቀን እንኳን ለበደለ በፍትህ ለቆመም እጅግ አስጨናቂ የሆነ ምርመራ አለ። መሀይማን የሆኑን ወገኖች በዘራቸው ምክንያት ለማጥቃት ሲነሱ ከቻልክ አስቁማቸው። ካልሆነ ለሚመለከተው ክፍል አሳውቅ። ካልሆነ ጥፋቱን ኮንን። ይህን በማድረግህ የምትሰጋው ተጨባጭ አደጋ ካለ ቢያንስ እራስህን ከወንጀለኞች አርቅ። ያለበለዚያ ተጠያቂ እንደምትሆን አትዘንጋ።
ሶሻል ሚዲያ ላይ በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጭፍን ውንጀላ ስታይ ዝም ብለህ አትለፍ። ቢያንስ "አላህን ፍሩ" በል። ሰዎች በትግሬነታቸው፣ በኦሮሞነታቸው፣ በአማራነታቸው፣ በበርታነታቸው፣… ብቻ ዘመቻ ሲከፈትባቸው በየትኛውም መልኩ አጃቢ የምትሆን ከሆነ ግን አትጠራጠር ከመሀይማኑ መንጋ ጋር ነገ ላህ ፊት በፅኑ ተጠያቂ ነህ።
ስንትና ስንት ጥሩ ትግሬዎች፣ ጥሩ ኦሮሞዎች፣ ጥሩ አማራዎች፣ ጥሩ በርታዎች፣ ጥሩ ሶማሊዎች፣ ጥሩ ዐፋሮች፣… አሉ። "የለም የትግሬ ጥሩ የለም" ፣ "የኦሮሞ ደህና የለም"፣ ወዘተ የሚል ካለ ስሜት የሚጋልበው ጥርብ መሀይም ነው። ስለ ሀገር ቢደሰኩርም ለሀገር ጠንቅ የሆነ አቀንጭራ ነው። እንዲህ አይነት ጅምላ ፈራጅ መንጋዎችን ፈርተን ዘረኝነትን ከመኮነን አፋችን ሊለጎም አይገባም።
ደግሞስ ከዚህ በላይ ምን እንጠብቃለን? ችግሩኮ በየቤታችን መጣ። አደጋው እኮ የህዝብን የሃገርን ህልውና አደጋ ላይ እየጣለ ነው። በኦሮሞና ሶማሊ ግጭት ሚሊዮን የቀረበ ህዝብ ነው የተጎዳው። በጉጂ ኦሮሞና በጌዲዎ ህዝብ ግጭት ከእልቂቱ ባለፈ ከግማሽ ሚሊዮን የበለጠ ህዝብ ነው የተፈናቀለው። ወላይታና ሶዶ አንዱ በሌላው ላይ ስለት መዟል፣ ዱላ አንስቷል። በርካታ አማራዎች በቤኒሻንጉል፣ በደቡብና በኦሮሚያ የጥቃት ሰለባ ሆነዋል። አፋርና አማራ፣ አፋርና ኦሮሞ፣ አፋርና ዒሳም በተደጋጋሚ በርካታ ነፍስ የጠፋበት ግጭት ይከሰታል። የጉራጌና የቀቤና ግጭትም የቅርብ ነው። ይሄው አሁን ደግሞ ትግሬዎች በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ኢላማ እየተደረጉ ነው።
ነገር ግን መንግስትም እርምጃ ሲወስድ ያውም ከወሰደ ችግሩን ከስሩ በሚቆርጥ መልኩ አይደለም ያውም ምናልባት ከብዙዎቹ ግጭቶች ጀርባ የመንግስት አካላት ረጃጅም እጆች ከሌሉ። ጋዜጠኛውም ሲዘግብ እየመረጠ ነው። ምናልባት ቤንዚን አርከፍካፊ ካልሆነ። እኛም አራጋቢ እንጂ የመፍተሄ አካል አይደለንም። ብዙሃኑ የሚያስጨንቀው ከራሱ ብሄር መወገኑ ነው። ሌላውን በስመ ትግሬነት፣ በስመ ኦሮሞነት፣… ለማጠልሸትና ለመፈረጅ ምንም አያመነታም። በህሊናው ሳይሆን በስሜቱ ይፈርዳል።
ብቻ ጥረት አይናቅምና የበኩላችንን እንወጣ። ሁሉም ህዝብ ደካማ የሚሆንበት ጊዜና ቦታ አለና ከደካሞች ጎን እንሰለፍ። ሁሉም ህዝብ አናሳ የሚሆንበት አካባቢ አለና አናሳዎች እንዳይበደሉ የበኩላችንን እንወጣ። የሃይማኖት አስተማሪዎች ሀላፊነታቸውን እንዳይዘነጉ እናስታውስ። ዘረኛ ፀሀፊዎችንና አጋጋዮችን (አክቲቪስቶችን) ከየትኛውም ብሄር ቢሆኑ እንኮንን። ካልሆነ ግን እሳቱ ሁላችንም ጋር ይደርሳል። አላህ ያግዘን። ስንትና ስንት ጥሩ ትግሬዎች፣ ጥሩ ኦሮሞዎች፣ ጥሩ አማራዎች፣ ጥሩ በርታዎች፣ ጥሩ ሶማሊዎች፣ ጥሩ ዐፋሮች፣… አሉ። "የለም የትግሬ ጥሩ የለም" ፣ "የኦሮሞ ደህና የለም"፣ ወዘተ የሚል ካለ ስሜት የሚጋልበው ጥርብ መሀይም ነው። ስለ ሀገር ቢደሰኩርም ለሀገር ጠንቅ የሆነ አቀንጭራ ነው። እንዲህ አይነት ጅምላ ፈራጅ መንጋዎችን ፈርተን ዘረኝነትን ከመኮነን አፋችን ሊለጎም አይገባም። ደግሞስ ከዚህ በላይ ምን እንጠብቃለን? ችግሩኮ በየቤታችን መጣ። አደጋው እኮ የህዝብን የሃገርን ህልውና አደጋ ላይ እየጣለ ነው። በኦሮሞና ሶማሊ ግጭት ሚሊዮን የቀረበ ህዝብ ነው የተጎዳው። በጉጂ ኦሮሞና በጌዲዎ ህዝብ ግጭት ከእልቂቱ ባለፈ ከግማሽ ሚሊዮን የበለጠ ህዝብ ነው የተፈናቀለው። ወላይታና ሶዶ አንዱ በሌላው ላይ ስለት መዟል፣ ዱላ አንስቷል። በርካታ አማራዎች በቤኒሻንጉል፣ በደቡብና በኦሮሚያ የጥቃት ሰለባ ሆነዋል። አፋርና አማራ፣ አፋርና ኦሮሞ፣ አፋርና ዒሳም በተደጋጋሚ በርካታ ነፍስ የጠፋበት ግጭት ይከሰታል። የጉራጌና የቀቤና ግጭትም የቅርብ ነው። ይሄው አሁን ደግሞ ትግሬዎች በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ኢላማ እየተደረጉ ነው።
ነገር ግን መንግስትም እርምጃ ሲወስድ ያውም ከወሰደ ችግሩን ከስሩ በሚቆርጥ መልኩ አይደለም ያውም ምናልባት ከብዙዎቹ ግጭቶች ጀርባ የመንግስት አካላት ረጃጅም እጆች ከሌሉ። ጋዜጠኛውም ሲዘግብ እየመረጠ ነው። ምናልባት ቤንዚን አርከፍካፊ ካልሆነ። እኛም አራጋቢ እንጂ የመፍተሄ አካል አይደለንም። ብዙሃኑ የሚያስጨንቀው ከራሱ ብሄር መወገኑ ነው። ሌላውን በስመ ትግሬነት፣ በስመ ኦሮሞነት፣… ለማጠልሸትና ለመፈረጅ ምንም አያመነታም። በህሊናው ሳይሆን በስሜቱ ይፈርዳል።
ብቻ ጥረት አይናቅምና የበኩላችንን እንወጣ። ሁሉም ህዝብ ደካማ የሚሆንበት ጊዜና ቦታ አለና ከደካሞች ጎን እንሰለፍ። ሁሉም ህዝብ አናሳ የሚሆንበት አካባቢ አለና አናሳዎች እንዳይበደሉ የበኩላችንን እንወጣ። የሃይማኖት አስተማሪዎች ሀላፊነታቸውን እንዳይዘነጉ እናስታውስ። ዘረኛ ፀሀፊዎችንና አጋጋዮችን (አክቲቪስቶችን) ከየትኛውም ብሄር ቢሆኑ እንኮንን። ካልሆነ ግን እሳቱ ሁላችንም ጋር ይደርሳል። አላህ ያግዘን።
1 Comments
sexxrsv drgf
ReplyDelete