አንጠራጠር ተራራን ሊንድና ሊያንኮታኩት የደረሰ ተዓምር የኛን ልብ የማያርድበት ምክንያት ፈፅሞ አይኖርም።እንከንና ወለምታው የኛ ሆኖ ነው እንጂ።አላህ(ሱብሀነሁ ወተዓላ) ይህንን ሲናገር እንዲህ ብሏል።
"ይህንን ቁርዓን በተራራ ላይ ብናወርደው ኖሮ ከአላህ ፍራቻ(የተነሳ) ተዋራጅና ተሰንጣቂ ሆኖ ባየኸው ነበር።ይህችንም ምሳሌ ያስተነትኑ ዘንድ ለሰዎች እንገልፃታለን።" (አል ሃሽር 21)
እንግዲህ ይህ ከሆነ እውነታውና ተጨባጩ ሙስሊሞችን፤በተለየ መልኩ ደግሞም ከነርሱ ውስጥ ከቁርዓን የራቁና አሊያ የሚቀሩት ሆነው ግና ለፊደሎቹና ለድምፁ በመጨነቅ ላይ ብቻ ተወጥረው በርሱ መስራትንና በርሱ መኖርን ግን አይኑን ላፈር ላሉ፤እንዲሁም ሙስሊም ላልሆኑና የሰላምን ፍኖት በህይወታቸው ለሚያቀነቅኑ ሁሉ ወደዚህ ታላቅና እንከን የለሽ ቅዱስ መፅሀፍ እንዲመጡ፤ያዘዘውን የሚስጥር ካዝና እንዲመረምሩ ልባዊ ጥሪያችንን እናቀርብላቸዋለን።
እንዴታ በርሱ የተናገረ እውነተኛ ነው።
በርሱ የፈረደ ፍትሀዊ ነው
በርሱ የኖረ ነፃ ነው።
በእርግጥም አንብበው መርምረው የህይወት መመርያ የሚገባው ብቸኛው መፅሀፍ ቁርአን ነው።
መክንያቱም፦
፠የሰው ልጆች ወደ ትክክለኛ መንገድ ይመራል።
"ይህ ቁርአን ወደዘከያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ሆነችው መንገድ ይመራል።" (ኢስራእ 9)
፠ከፅልመት ወደ ብርሀን ያቀጣል።
"አሊፍ ላም ራ ይህ ቁርዓን ሰዎችን በጌታቸው ፍቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሀን አሸናፊ ምስጉን ወደሆነው ጌታ መንገድ ታወጣበት ዘንድ ያወረድነው መፅሀፍ ነው።"( ኢብራሂም 1)
፠ፈውስና መድሀኒት ነው።
"እርሱ ለነዚያ ላመኑት መመርያና መፈወሻ(መድሀኒት) ነው።" (ፉሲለት፡44)
፠የሰው ልጆች ያለርሱ ህይወት አልባ ናቸው።ስለዚህ ቁርአን ደግሞ ሀይወት ይዘራባቸዋል።
"እንደዚሁም ወደ አንተ ከትአደዛዛችን ሲሆን ህይወት ሰጭን(ቁርአንን) አወረድን።"(ምእራፍ ሹራ፡52)
መቼም ቁርአን ቁርአን ስል ሱናን የት ጥለሽው ነው የሚል ጥያቄ ይነሳል ብዬ ፈፅሞ አላልምም።ምክንያቱም ቁርአንን ያለ ሱና መረዳት ፈፅሞ የማይቻል በመሆኑ።ሱና የቁርአን አብራሪና ገላጭ ነው።ሁለቱን ለመነጣጠል የሙሞክር ካለ ፈፅሞ የራቀ ጥመትን ጠሟል።አላህ(ሱብሀነሁ ወተዓላ) እንዲህ ሲል ተናግሯል።
"ወደ አንተም ለሰዎች የተወረደውነወ ልትገልፅላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ማሰደታወሻውን(ቁርአንን)አወረድን።" (ምእራፍ ነህል ፡44)
፨፨መንሀጁ ቲላዋ ከሚል የተጅዊድ መፅሀፍ የተወሰደ
ዝግጅት ኡሙ አብደላህ ነፊሳ ሙሐመድ
Abdurezak Temam Abul Abas
0 Comments