Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አላህ ከአርሽ በላይ መሆኑን የማያምኑት አህባሾች እና አሻኢራዎች ከየት የመጣውን ሰላት ነው የሚሰግዱት?




 
አላህ ከአርሽ በላይ መሆኑን የማያምኑት አህባሾች እና አሻኢራዎች ከየት የመጣውን ሰላት ነው የሚሰግዱት?
============
ሰላትን ማን ነው ያዘዘው?
አላህ፡፡
ሰላትን አላህ ለነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የት ነው ያዘዛቸው?
ከሰባቱ ሰማያት በላይ፡፡
አላህ በስንት ሰላት አዘዛቸው?
በ50 ሰላት አዘዛቸው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) 50 ሰላት ይዘው ሲመለሱ 6ተኛው ሰማይ ላይ ነብዩ ሙሳን (አለይሂ ሰላም) አግኝቷቸው ምን አላቸው?
ጌታህ (ከ7 ሰማያት በላይ የነበረው) በምን አዘዘህ?
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በ50 ሰላት አዘዘኝ ሲሉ መለሱ፡፡
የሙሳም መልስ ወደ ጌታህ (ከ7ኛው ሰማይ በላይ ወዳለው አላህ) ተመለስ (ሰላቱን) አስቀንስ፡፡
ከ50 ሰላት ተቀነሰላቸው አሁንም ሲመለሱ ሙሳ አለይሂ ሰላም
“ጌታህ በምን አዘዘህ”
በእንዲህ ያህል ሰላት
ሙሳም (አለይሂ ሰላም) ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
“ወደ ጌታህ (ከ7ኛው ሰማይ በላይ ወዳለው አላህ) ተመለስ አስቀንስ እያሏቸው” ሰላት 5 እስኪደርስ ድረስ ወደ ጌታችን አላህ ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ ከአርሽ በላይ ወዳለው ተመለሱ፡፡
============ ============
ይሄ ጌታችንን አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ከሰባት ሰማያት፣ ከአርሽ በላይ መሆኑን ልባችንን ሞልተን ከምንናገርባቸው ሀዲሶች ውስጥ አንዱ እና ዋናው ነው፡፡
ይሄ ሚእራጅን እናከብራለን ለሚሉ ያልታዘዙትን ለሚሰሩ በተገላቢጦሹ የአላህን ከፍጡራኑ በላይ መሆን ለማይቀበሉ መነቃነቂያ የሌለው ራስምታት የሆነ ማስረጃ ነው፡፡
ጌታን አላህ በዛቱ ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ ከአርሽ በላይ ነው፡፡ ጌታችን አላህ በእውቀት፣ በመስማቱ፣ በማየቱ ፍጡራኑን ያካበበ ነው፡፡
አላህ ሆይ! እውቀት ጨምርልን፡፡ በሃቅ ላይም አጽናን፡፡