Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጉድና ጅራት ከወደኋላ እንዲሉ . .

ጉድና ጅራት ከወደኋላ እንዲሉ . .

ሕንድ በሙምባይ ከተማ የሚገኘው ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ አንድ ትልቅ "የኢየሱስ" ሃውልት ይገኛል። ለበርካታ ዓመታት ይህ ሃውልት ለዚህ ቤተ-ክርስቲያን ከሃውልትነት ባለፈ ምንም ፋይዳ አልነበረውም። እስከ 2012 እ.ኤ.አ ድረስ። ከፈረንጆቹ 2012 በኋላ ግን የዚህች ቤተ-ክርስቲያን አማኞች በአንድ "ተዓርምራዊ ክስተት" ምክንያት ለሃውልቱ ከፍተኛ አክብሮት መስጠት ጀመሩ። ሃውልቱ አፍ አውጥቶ «ጌታ ነኝ!» ብሎ እንዳይመስላችሁ። አሊያም እጁ ላይ የተቸነከረበትን ሚስማር ነቅሎ ከተሰቀለበት መስቀል ወርዶም እንዳይመስላችሁ። ነገሩ ያለው ወዲህ ነው . . .

የሃውልቱ እግር ስር ድንገት ጠበል ፈለቀ !! ጉድ በል!!

ሳናል ኤድማሩኩ ይባላል። «የውሸት ተዓምራዊ አፈታሪኮችን እየተከታተልኩ አጋልጣለሁ!» ይላል። ታዲያ ይህ ግለሰብ ዘግይቶም ቢሆን ስለዚህ ተዓምራዊ ሃውልት ጠበል ሳይሰማ አልቀረም። ሺዎች ወደዚህ ሃውልት ሄደው በጠብታው አማካኝነት እንደተፈወሱ ሲናገሩ እሱ ግን ምጸት በተሞላበት መልኩ ያጣጥልባቸዋል።
መቀመጫውን ሙምባይ ያደረገው የTV9 ቻናል በዴልሂ የጣቢያው ቅርንጫፍ አቶ ሳናልን በፕሮግራሙ ላይ አቅርቦ ስለዚህ ተዓምራዊ ጠበል ጠየቀው። ሳናልም ይህ የሐሰት ወሬ እንደሆነና ጭራሽ «ሃውልት ውሃ አፈለቀ» የሚባለውን አሉባልታ እንደማይቀበል ተናገረ። ሆኖም ምንም አይነት ሳይንሳዊ ገለጻ ለመስጠት ግን ቦታው ላይ ሄዶ የማጣራት ስራ ሳይሰራ ለመናገር እንደማይደፍር አሳወቀ። የቻናሉ አስተዳደሮች ወደ ሙምባይ መጥቶ ቤተ-ክርስቲያኑ ድረስ በመሄድ ካስፈለገው እንዲያጣራ ጋበዙት። የቤተክርስቲያኑ ሰዎችም ፈቀዱ።

ግብዣውን ተቀብሎ አቶ ሳናል ከመሃንዲስ ጓደኛው ጋር ወደ ቦታው አቀና። ከዚያ በኋላ ቦታው ላይ ምን እንዳገኘ እንዲህ ሲል በራሱ አንደበት ያጫውተናል . . . .

« I had a close look at a nearby washroom and the connected drainage system that passed underneath the concrete base of the cross. I removed some stones from the drain and found it was blocked. I touched the walls, the base, and the cross and took some photographs for documentation. It was very simple: Water from the washroom, which had been blocked in the clogged drainage system, had been transmitted via capillary action into the adjacent walls and the base of the cross as well as into the wooden cross itself. The water came out through a nail hole and ran down over the statue's feet. »

« . . ቦታው እንደደረስኩኝ አቅራቢያ የሚገኘውን መጸዳጃ እና ከመስቀሉ ሃውልት መሰረት በስር በኩል የሚያልፉትን ከርሱ ጋር የተገኛኙትን ፍሳሽ ማስወገጃ ሲስተሞች በሚገባ ተመለከትኩኝ። ከፍሳሽ ማስወገጃ የተወሰኑ ድንጋዮችን አስወገድኩ። ከዚያም የተዘጋ (የተከለለ) ሆኖ አገኘሁት። ግድግዳውን፣ መሰረቱን እና መስቀሉን ነካዋቸው። የተወሰኑ ፎቶግራፎችንም አነሳሁና ዶክሜንቶችንም ያዝኩ። ነገርየው በጣም ቀላል ነበር። ከመጸዳጃው ውስጥ የሚወጣ ውሃ በተዘጋው (ከተደፈነው) ፍሳሽ ማስወገጃ ሲስተም በኩል የጋራ መገናኛ ላላቸው ግድግዳዎች እና ለመስቀሉ ብሎም ለእንጨቱ (የሃውልት) መስቀል በራሱ በውሃ ርቆት ማስተላለፊያ በኩል የሚመጣ (እንጥብጣቢ) ነው። ውሃው በሃውልቱ የጥፍሩ ቀዳዳ በኩል የሚወጣ ሲሆን እስከ ሃውልቱ እግርጌ ድረስ ይወርዳል። . . . »

ይህ ሁሉ ሺዎች የሚመላለሱበትና የሚፈወሱበት "ተዓምር" የውሃ ማስተላለፊያ ትቦ ብልሽት ምክንያት የሚመጣ የመጸዳጃ ቤት ውሃ መሆኑ ዘይገርም!! ነው አይደል? ታዲያ ይህን እውነታ ሁሉም በጸጋ የሚቀበለው መስሏቿልን?
አቶ ሳናል ይህንን ኬዝ በቀጥታ ቴሌቪዥን ስርጭት ባቀረበበት ቅጽበት የቴሌቪዥን ጣቢያው በራፍ በቁጣ ያበዱ ብዛት ያላቸው የእምነቱ አባላት "እውጭ ትወጣና ጨረስንህ!" ብለው ሰልፍ አካሂደውበታል። ለምን አጋለጥክብን ነው ነገሩ!?

በቀጣዮቹ ሳምንታት በሙምባይ በሚገኙ ሶስት ፖሊስ ጣቢያዎች አቶ ሳናል ላይ "የጌታን ስም በማጉደፍ" ክስ የተመሰረተበት ሲሆን በሕንድ በጥላቻ ንግግር ኮድ ፋይል ተከፍቶበታል። በተጨማሪም አቶ ሳናል በሁለት የቤተክርስቲያን ተቋማት አመራሮች ከበድ ያለ ክስ የተመሰረተበት ሲሆን የክሱ ጭብጥ. .

"deliberately hurting religious feelings and attempting malicious acts intended to outrage the religious sentiments of any class or community.”

« ሆን ብሎ የእምነት ስሜትን ለመጉዳት በመሞከር እና በተንኮል ተግባር የአንድን ወገን ወይንም ሕብረተሰብ የእምነት አስተሳሰብ ለመበደል በመሞከር » የሚል ነው።
አቶ ሳናል እንደሚናገረው ከዚህም ባለፈ ከፖሊሶች ለርሱ በሚደወሉለት የስልክ ጥሪዎች ላይ ማስፈራሪያ እየተደረገበት እንደሆነና ማስፈራሪያው በኦንላይንም ላይ እንደቀተጠለ ተናግሯል።

አሁን ላይ አቶ ሳናል ለህይወቱ በመስጋት ከሃገሩ ሸሽቶ ፊንላንድ ላይ ጥገኝነት በመጠየቅ ኑሮውን እዚያ ማድረጉን ቢቢሲ ዘግቧል።