ዒድ ማለት ምን ማለት ነው?
ኢብኑል ዓረቢዕ ‹‹ዒድ›› (ዒድ) ብሎ ስለመሰየሙ ሲናገሩ በየአመቱ አዲስ ደስታን ይዞ የሚመለስ ከመሆኑ አንፃር መሆኑን እና ‹‹ዓደ›› (ተመለሰ) ከሚለው ቃል የተወሰደ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ እዚህ ላይ ልብ ልንልን የሚገባው (ዒድ) ቂያማ እስቂቆም ተመላልሶ የሚመጣ ቢሆንም እኛ ግን የሚቀጥለውን ለመድረስ ምንም ዋስትና እንደሌለን ነው፡፡ ስለሆነም ከአላህ ህግ ፈፅሞ ልንወጣ አይገባም፡፡
عَنْ أَنَسٍ-رضي الله عنه- قَالَ: قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ- الْمَدِينَةَ، وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ:(مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ؟) قَالُوا: كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ-: (إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الْأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ) رواه أبو داود
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ይላሉ ‹‹የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) መዲና ከተማ ሲመጡ የመዲና ሰዎች በመሀይምነት ዘመን (ደስታቸውን የሚገልፁባቸው) የሚጫወቱባቸው ሁለት ክብረበዓላት ነበሩዋቸው። ይህንን ባዩ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡፡ በእነዚህ በሁለቱ ምትክ ከእነርሱ በተሸሉ ሁለት ክብረበዓላትን ቀየረላችሁ፤ እነሱም የፈጥር እና የአድሀ በዓላት ናቸው፡፡››
(አቡዳውድ እና አህመድ እንደዘገቡት)
ከዚህ ሀዲስ ጋር በተያያዘ ኡለማዎች የተረዷቸዉን ሁለት ቁም ነገር ልናስተውል ይገባል።
አንደኛ ፡- ከሌሎች (ከእስልምና ውጭ) ካሉ ማህበረሰቦች ጋር መመሳሰል የተከለከለ መሆኑ እና፣
ሁለተኛ ፡- በኢስላም የተደነገጉ ክብረ በአላት ሁለት ብቻ መሆናቸውን ነው ፡፡