ምላሳችን ከእርግማንና ከስድብ እንቆጥብ!
�� አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦
"ነቢዩ( ﷺ) ተሳዳቢ፣አስቀያሚ ንግግርን ተናጋሪ ሆነ ተራጋሚ አልነበሩም።"
��【ቡኻሪ ዘግበውታል】
�� የአላህ መልክተኛ( ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦
"እኔ ተራጋሚ ሆኜ አልተላኩም…።"
【ሙስሊም ዘግበውታል】
��የአላህ መልክተኛ( ﷺ) እንዲህም ብለዋል፦
"አንድ የአላህ ባሪያ አንዳችን ነገር በሚራገም ግዜ ፦እርግማኗ ወደ ሰማይ ከፍ ብላ ትወጣለች፣ ከዚያም የሰማያት በር ይዘጉባታል፣ከዚያም ወደ ምድር ዝቅ ብላ ትወርድና በሮች በሙሉ ጥርቅም ብለው ይዘጋሉ፣ከዚያም ወደቀኝና ግራ ትመለከታለች ፣ መግቢያ ስታጣ ወደ ተረጋሚው ትመለሳለች ለእርግማን ተገቢ ከሆነ እርግማኑ ይደርስበታል፣ ካለሆነ ግን ወደ ተራጋሚው ትመለሳለች።"
��【አቡ ዳዉድ ዘግበውታል】
��"አንድን አማኝ መርገም ነፍሱን እንደ ማጥፋት ይቆጠራል።"
��【ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል】