ከዒድ ዋዜማ ጀምሮ ልንፈፅማቸው የሚገቡ ነገሮች
ዒድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲሁም በኢስላም የተደነገጉ ክብረ በአላት ኢድ-አልፈጥር እና ኢድ-አልአድሀ ብቻ መሆናቸውን ከተረዳን፤ በእነዚህ ሁለት ዒዶች ዋዜማ እና በእለቱ ምን ማድረግ ይወደዳል? ምንስ ይፈቀዳል? ምን ከማድረግ ልንከለከል ይገባል? ወደ ሚሉት ነጥቦች እንምጣ፡፡
በመጀመሪያ ከዒድ ዋዜማ ጀምሮ ልንፈፅማቸው ከሚያስፈልጉ ነገሮች ስንነሳ፤

1. በኢደል-ፊጥር ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዐት አንስቶ ሰላቱ እስኪጀመር በኢደል-አድሀ ደግሞ ከዙል
ሂጃ የዘጠነኛው እለት ፈጅር ሰላት አንስቶ የአስራ ሶስተኛው እለት ፀሀይ እስከምትጠልቅ ድረስ ተክቢራን ማድረግ
ይገባል፡፡
2. መታጠብ እራስን ማሰማመር እና ከልብሶች መካከል የተሸለውን እና ቆንጆውን መልበስ ከሰለፎች የተዘገበ ተግባር ነው፡፡
3. ሴቶችን በተመለከተ በዚህ እለትም ይሁን በሌላ ጊዜ ከቤታቸው እንዴት መውጣት እንዳባቸው በሸሪዐ የታወቀ ነው፡፡ እናም ከመገላለጥ እና ሽታ ያላቸውን ነገሮች ተጠቅመው ከመውጣት ተቆጥበዉ ከቤታቸው ወደ መስጊድ ወይም ወደ ዒድ መስገጃ ስፍራ ሊሄዱ ይገባል፡፡
የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ለጋብቻ የቀረቡና የደረሱ እንዲሁም በወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶችን ጨምሮ ወደ ዒድ ሰላት መስገጃ ቦታ ስፍራ እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ እንዲህ የሚል ጥያቄ ተጠይቀው ነበር ‹‹አንዳችን ጅልባብ ባይኖራት ምን ታድርግ?›› እሳቸውም እንዲህ አሉ ‹‹እህቷ (ጓደኛዋን) ታውሳት››
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
عَنْ زَيْدِ بْنِ خَالِدٍ الْجُهَنِيِّ، قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " لا تَمْنَعُوا إِمَاءَ اللَّهِ مَسَاجِدَ اللَّهِ ، وَلْيَخْرُجْنَ تَفِلاتٍ " رواه أحمد وأبو داود وصححه الألباني
በሌላውም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል ‹‹ሴቶችን መስጊድ ከመሄድ አትከልክሏቸው ነገር ግን ከቤታቸው ሽታ ያለው ነገርን ተጠቅመው እንዳይወጡ፡፡››
(አል-ኢማም አህመድና አቡዳውድ ሲዘግቡት አልባኒ ሰሂህ ብለውታል)
4. በዒደል ፊጥር ሰጋጁ ወደ መስገጃው ከመውጣቱ በፊት ዊትር (አንድ፤ ሶስት፤ አምስት …..) ቁጥር ያላቸውን ተምሮች በልቶ መውጣት ሱና ነው።
5. ለኢድ ሰላት ከመውጣት በፊት ዘካተል-ፊጥርን ለተገቢው ወገን መስጠት ያስፈልጋል።
6. ሰላተል ኢድን ለመስገድ ከፍተኛ ፍላጎትና ጉጉት ሊኖር ይገባል፡፡ ምክንያቱም ይህ ተግባር ከታላላቅ የኢስላም መገለጫዎች አንዱ ከመሆኑም ባሻገር የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) ሰላተል ዒድ ከተደነገገበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሕልፈታቸው ትተውት አያውቁም በተጨማሪም በመሰረቱ መስገድን የተከለከሉትን የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች ሳይቀር በቦታው ላይ እንዲገኙ አዋዘል፡፡
7. ሰላቱ ከተጠናቀቀ በኋላ በተቻለ አቅም ኹጥባን ማዳመጥ
8. ወደ ዒድ ሰላት ከሄዱበት መንገድ በሌላ መመለስ
9. የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት መለዋወጥ፡፡ ይህም ‹‹ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም›› የሚል ሲሆን የተለያዩ የኢስላም ሊቃውንት ከሰሃቦች መገኘቱን አረጋግጠዋል፡፡
10. ከኢድ ጋር በተያያዘ ዘካተል ፊጥርን መስጠት መታዘዙ የተለያዩ ችግረኞችን ማስታወስ እና አቅም በፈቀደ መጠን ችግራቸውን ለመቅረፍ ጥረት ማድረ የሚደገፍ ተግባር መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡
11. በአጠቃላይ ሸሪዐው ያዘዘባቸውን እና የፈቀዳቸውን ተግባራት በፈፀም የሚፈቀድና የሚወደድ ይሆናል።
ጣሀ አህመድ