Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ የእናት ክብረ በአል (ዒዱልኡም) ተብሎ የሚታወቀውን በአል ማክበር እንዴት ይታያል? (ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል- ኡሰይሚን ረሒመሁላህ)

'‎ጥያቄ፦ የእናት ክብረ በአል (ዒዱልኡም) ተብሎ የሚታወቀውን በአል ማክበር እንዴት ይታያል? 

መልስ፦ ሸርዓዊ የሆኑ በዓላትን የሚፃረሩ በዓላት ሁሉ ቢድዐ (ፈጠራ) የሆኑ በዓላት(ዒዶች ናቸው)። «በሰለፍ አስሰላህ» ዘመን አይታወቁም። እነዚህን በዓላት ከኢስላም ውጭ የሆኑ ሰዎች ሊሆኑም ይችላሉ። እናም እነሱን ማክበር ከአላህ ጠላቶች ጋር መመሳሰልም ሊሆን ይችላል።ሸሪዓዊ በዓላት በሙስሊሞች ዘንድ የታወቁ ናቸው።እነሱም፦ ዒደል-ፊጥር፣ ዒድ-አል-አድሃ እና ሳምንታዊው የጁምአ ዒድ ናቸው። ከነዚህ ሶስቱ በዐላት ውጭ በኢስላም ውስጥ ሌላ በዐል የለም። ከነዚህ በዐላት ውጭ የተፈጠሩ በዐላት ወደ ፈጣሪውቻቸው ተመላሾች ናቸው። በአላህ ሸሪአ ዘንድም ውድቅ ናቸው ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) «በዚህ ሃይማኖታችን ውስጥ ከሱ ያልሆነውን አዲስ ነገር ፈጥሮ ያስገባበት እሱ (ፈጠራው) ተመላሽ ይሆንበታል።» ብለዋል (ቡኸሪና ሙስሊም)። ስራው ተመላሽ ይሆናል በአላህ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ማለት ነው:: በሌላ አገላለፅ ደግሞ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) «እኛ ያላዘዝነውን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ይሆንበታል።» ብለዋል። (ሙስሊም)። ይህ ግልፅ ከሆነ በጥያቄው የተጠቀሰው የእናቶች ቀን ክብረ በዓል(ዒዱልኡም) በዒድ መልክ ሊከበር አይገባም። በዓል ብሎ ደስታን መግለፅ፣ ስጥታ መሰጣጠትና የመሳሰሉትን መፈፀም አይፈቀድም። አንድ ሙስሊም በሃይማኖቱ መኩራት አለበት። በዚህ አላህ ለባሮቹ በወደደላቸው ትክክለኛ ዲን ውስጥ አላህና መልክተኛው የወሰኑትን ብቻ መፈፀም አለበት። መጨመርም መቀነስም የለበትም። ሙስሊም ሁሉን ነገር ተቀባይና ተከታይ መሆን የለበትም። ራሱን በአላህ ሀይማኖት ማደራጀት አለበት። አስከታይ እንጂ ተከታይ መሆን የለበትም።ጥሩ አርአያ እንጂ መጥፎ ምሳሌ መሆን የለበትም። አላህ ምስጋና ይገባውና የአላህ ሀይማኖት በሁሉም መልኩ የተሟላ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

ِ ۚ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا ۚ ٌ
 
«… ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡» (አል-ማኢዳ 5፥3) 
እናት በአመት ውስጥ አንድ ግዜ ብቻ ከሚከበርላት በዓል የበለጠ ሐቅ አላት። እናት በልጆቿ ላይ ብዙ መብቶች አሏት። ልጆች በሁሉም ጊዜና ቦታ እናታቸውን መጠበቅ፣ መንከባከብ፣ ለርሷ ማሰብና አላህን እንዲወነጅሉ እስካለዘዘቻቸው ድረስ በሁሉም ሊታዘዟት ይገባል።

(ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል- ኡሰይሚን ረሒመሁላህ)‎'
ጥያቄ፦ የእናት ክብረ በአል (ዒዱልኡም) ተብሎ የሚታወቀውን በአል ማክበር እንዴት ይታያል?

(ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል- ኡሰይሚን ረሒመሁላህ)