Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ በቁርአን መማል እንዴት ይታያል? (ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል- ኡሠይሚን ረሒመሁላህ)

'ጥያቄ፦ በቁርአን መማል እንዴት ይታያል?
መልስ፦ ለዚህ ጥያቄ ሰፍ ያለ መልስ መሰጠት ያስፈልጋል። በአንድ ነገር መማል ማዩ ያን የማለበትን ነገር በተለየ ሁኔታ ማላቁንና ማክበሩን ያሳያል። ስለዚህም ማንም ሰው በአላህ እንጂ መማል አይችልም።በስሞቹወይም በባህሪያቱ መማል ይችላል። ለምሳሌ ወላህ እንዲህ አደርጋለሁ፤ በካዕባ ጌታ ይሁንብኝ እንዲህ አደርጋለሁ፤ በአላህ ሀይል ይሁንብኝ እንዲህ አደርጋለሁ እና የመሳሰሉትን በማለት መማል ይችላል።
ቁርአን የአላህን ቃል ይዟል።የአላህ ቃል ደግሞ የርሱ ባህሪይ (ሲፈት) ነው። ስለዚህ በቁርአን መማል ይችላል። በቁርአን ይሁንብኝ ብሎ መማል ይችላል። በውስጡ የያዘውን የአላህን ቃል በማሰብ ማለት ነው። የሐንበሊ ዑለሞችይህ ነገር እንደሚቻል በጽሁፍ አስፍረዋል። ከመሆኑም ጋር ሰው መማል ያለበት ሌላውን ሰው(ሰሚውን) ግራ በማያጋባ ሁኔታመሆን አለበት። በአላህ ስም ቢምል ይመረጣል። ወላህ፣ በከዕባ ጌታ (ወረበል ከዕባ)፣ ነፍሴ በእጁ ባለችው፣ እና በመሳሰሉት ቢምል ይመረጣል። ምክንያቱም ሰውን ግራ የማያጋቡ ናቸውና። ሰዎችን ማናገር በሚያውቁትና ልባቸው እርጋታን በሚያገኝበት ነገር ሲሆን ይሻላል።
መማል የሚቻለው በአላህ በስሞቹናበባህሪያቱ ብቻ ነው። ከአላህ ውጭ በማንም በምንም መማል አይቻልም።በነቢዩም(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሆነ በጅብሪል፣በካዕባም ሆነ በሌላ ማንኛውም ፍጡር መማል አይቻልም።ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) «የሚምል ሰው በአላህ ይማል ያለዚያ ዝም ይበል ብለዋል» (ቡኸሪና ሙስሊም)። በሌላ ሐዲስ ደግሞ «ከአላህ ውጭ ባለ ነገር የማለ ሰው በእርግጥከፈረ ወይምአጋራ።» ብለዋል(ቲርሚዚ)። አንድ ሰው ሌላውን በነቢይወይም በነቢዩህይወት ወይም በሌላ ሰው ህይወት ሲምልካየው ከዚህ ድርጊቱ ይከልክለው። ይህ ነገር ሀራምመሆኑን ያብራራለት። ነገር ግን መከልከሉና ማብራራቱ ጥበብበተሞላበት ለስላሳና ለዘብ ባለ ንግግር መሆን አለበት። እርሱን በመምከርና ከዚህ ሐራም በማውጣት ፍላጎት መሆን አለበት። ምክንያቱም አንዳንድ ሰው ሲታዘዝ ወይም ሲከለከል እልህ ይይዟል። ይቆጣል።ፊቱ ይቀላል። ደምስሮቹ ይወጣጠራሉ። ሊበቀለው አስቦ የከለከለው ሊመስለውም ይችላል። ሸይጣን ይህንን ነገር በልቡ እንዲያስብ ያደርገዋል። አንድ ሰው ሰዎችን ሲጠራ እንደሆኔታቸውና ደረጃቸው ቢጣራ፣ በጥበብ፣በለስላሳና በሚስብ ንግግር ቢጣራ የበሐጠ ተቀባይነት ያገኛል። ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) «አላህ በሐይል የማይሰጠውን በለዘብተኝነት (ሪፍቅ) ይሰጣል።» ብለዋል (ሙስሊም):: አንድ ባላገር ወደ መስጂድ መጥቶ መስጂድ ውስጥ ሲሸና ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያሳዩትን ለዘብተኝነት አብዛኛው ሰው የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ሰዎች ተቆጡትጮሁበት ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ግን ከለከሉዋቸው። ሰውየው ሽንቱን ሸንቶ ሲጨርስ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጠሩትና « መስጂድ እኮ ተክቢራ፣ ተስቢህና ቁርአን በውስጡ ይቀራበታልእንጂ ከዚህ ውጭ ለቆሻሻ ማራገፊያነት መጠቀም አይቻልም።» አሉት (ሙስሊም)። ከዚያም በሽንቱ ላይ አንድ ባልዲ ውሃ እንድጨምሩበት ሰሃቦቻቸውን አዘዙዋቸው። በዚህም ዘዴ አለመግባባቱተወገደ። ቦታውም ፀዳ። መሐይሙን ባላገር የመምከር አላማም ተሳካ። በዚህ መልኩ ነው የአላህን ባሮች ወደ አላህ ሀይማኖት መጥራትያለብን። ሰዎች እውነት እንዲቀበሉ እውነት ወደ ልቦቻቸው እንዲገባ የሚያስችል ቀለል ያለ መንገድ መጠቀም አለብን። ትክክለኛውን መንገድ የሚያሳየው አላህ ነው።
(ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል- ኡሠይሚን ረሒመሁላህ)'
ጥያቄ፦ በቁርአን መማል እንዴት ይታያል?

(ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል- ኡሠይሚን ረሒመሁላህ)