Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወተት ሻጭዋና ዑመር ኢብኑል ኸጣብ

'ወተት ሻጭዋና ዑመር ኢብኑል ኸጣብ
አስለም እንዳወሩት፦ ዑመር አንድ ቀን በከተማዋ ያለውን ሁኔታ ለመከታተል
በወጡበት አጋጣሚ ከርሳቸው ጋር ነበርኩ። በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ ወደ አንድ
ግድግዳ ተጠጉ፤ በዚህም ወቅት አንዲት ሴት ለልጇ እንዲህ ስትል ሰሙ፦
“ተነሽና እዚያ ወተት ላይ ውሃ ቀላቅሊበት! ልጅቷም ለእናቷ “የሙእሚኖች
መሪ ምን አዋጅ እንዳስተላለፈ አላወቅሽምን?” አለቻት። እናቷም “ምን ነበር
ያወጀው ልጄ?” አለቻት። ወጣቷም “አዋጅ ባዩን ወተት በውሃ እንዳይቀላቀል
ብሎ እንዲያውጅ ነው ያስደረገው” አለቻት። እናትም እየቀለደች “አይ ልጄ
ሆይ! ይልቁንስ ተነሽና ውሃ ቀላቅሊበት አሁን ያለሽው ዑመርም ሆነ የዑመር
ተጣሪ ከማያዩበት ነው” አለቻት። ልጅቷም ተቆጥታ ለእናቷ “አይሆንም እናቴ!
በግልጽ ልታዘዘው በስውር ደግሞ ትእዛዙን እምጥስ አይደለሁም። ዑመር
ባይኖር (ባያየን) ከዑመር ጌታ እይታ እንሰወራለን?” አለቻት። ዑመር ሁሉንም
ንግግር ሰሙ። ለአስለምም በሩን ምልክት አድርግበት፣ “ቦታውንም በትክክል
እወቅ አሉት”። ከዚያም ሄዱና ሲነጋ አስለምን “ሂድና ቦታውን ተመልከት”
አሉት። “ተናጋሪቱ ማን እንደሆነችና የምትመልስላትስ ማን እንደነበረች፣ ባልስ
አላት ወይ? የሚለውን አጣርተህ ተመለስ” አሉት። እኔም ከቦታው መጣሁና
ልጅቷም ሆነ እናቷ ባል እንደሌላቸው ነገርኳቸው። ዑመር ልጆቻቸውን ሰበሰቡና
“ከመካከላችሁ ሚስት የምድረው ማን አለ? አባታችሁ ስሜት ቢኖረው ኖሮ
ይህችን እንስት ማንም አይቀድመውም ነበር” በማለት ጠየቁ። ከዓሲም ኢብኑ
ዑመር በስተቀር ሁሉም ሚስት ስለነበራቸው ዓሲም አገቧት። እርሷም ዑመር
ኢብኑ ዓብዱል ዓዚዝን(5ኛ ኹለፋእ ራሺዲን በመባል የሚታወቁትን) (አላህ
ሥራቸውን ይውደድላቸውና) ወለደች።'

ሥራቸውን ይውደድላቸውና) ወለደች።