Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኤሽ ዲሞክራሲ

‪#‎ኤሽ_ዲሞክራሲ‬ ?
ታላቁ የሀገራችን ዐሊም የነበሩት ሸህ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁላህሸህ ሙሐመድ ወሌ እንዲህ አሉ "… ሶስተኞቹ(ከቢድዓ ሰዎች) ደግሞ ዲሞክራሲ የሚሉት ናቸው፡፡ ዲሞክራሲ¡ ኤሽ ዲሞክራሲ? ዲሞክራሲማለት የሀይማኖትን ገመድ በጥሶ ወጥቶ በህዝብ ድምጽ መተዳደር ማለት ነው፡፡ በአጭሩ፤ ወሳኙ ፈላጭ ቆራጩ ህዝብ መሆን አለበት (የሚል ነው)፡፡ የምን ቁርዓን የምን ሐዲስ፤ እነዚህ ሰዎች እስልምና ውስጥ ዲሞክራሲን የሚያስገቡት ከእስልምና ጋር የማይገናኝ እሳትና ውሀ ነው፡፡ እስልምና የሚፈርደው የሚቆርጠው በቁርዓንና ሀዲስ ነው፡፡ በቃ ሌላ ፍርድ የለንም፡፡ ዲሞክራሲ የተሰበተሰቡ የፈስ አቁማዳ(ደካማ) ሁላ ተሰብስቦ ያ በድምጽ ብልጫ የሚሉት ነው፡፡ ኤሽ ድምጽ ብልጫ? አንድ ቀን ውዱ አድርጎ የማያውቀው፣ አንድ ቀን ወደ ቂብላ ዞሮ የማያውቅ፣ ኻሊቁን(ፈጣሪውን) የማያውቀው ተሰብስቦ እጅህን አንሳ ይባላል ገባውም አልገባውም እጁን ያነሳል፤
አበቃ፡፡ ፓርላማ ነው ይሄን የወሰነው ማለት ነው፡፡ ሀላል ነው ሀራምነው የለም! ለነፍሳቸው ብቻ የሚስማማ መሆኑን አይተው ውሳኔ ማስተላለፍ ነው፡፡ ይሄ ከእስልምና ጋር ባዕድ ነው! አይገናኙም!
ዝምድናም የላቸውም በጭራሽ፡፡ ይህ ነው ዴሞክራሲ፡፡ ይሄ ሶስተኛው በጣም አለሙን የጎዳ፣ ያስቸገረ፤ እንደውም ኢስላማዊ ዴሞክራሲ አለ ብለው የአቡዘር ዲሞክራሲ፣ የአቢበክር ዲሞክራሲ፣
የኡመር ዲሞክራሲ፣ የፉላን(የእገሌ) ዲሞክራሲ ብለው ኪታብ አበጅተው አለሙን የለወጡ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ሀሳባቸው ነው፡፡ ያለፉም(የሞቱ) አሉ ደግሞም ያሉም አሉ፡፡ እነሱ አለም ያበላሹ እነሱ
ናቸው፡፡ . . . "ቢድዓ ምንድነው? ከሚለው ካሴት የተወሰደ ከ17-19 ደቂቃ —

Post a Comment

0 Comments