Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሂድ

ተውሂድ
ተውኒድ ማለት አላህን በጌትነቱ በብቸኛ ተመላኪነቱ በስሞቹ እና በባህሪያቱ ብቸኛ ማድረግ ማለት ነው::
ተውኒድ በ 3 የሚከፈል ሲሆን እነሱም
ተውኒደ አል-ሩቡቢያህ
ይህ ተውኒድ አላህን በስራዎቹ አንድ ማድረግ ነው።
ይህም ማለት
መፍጠር

ሲሳይን መስጠት
ነገሮችን ማስተናበር
መግደል እና
ህያው ማድረግ
በመሳሰሉት ድርጊቶች አላህን ብቸኛ ማድረግ ነው።
ከአላህ ሌላ ፈጣሪ የለም።
ኣላህ ይህንን እንዲህ በማለት ይገልጽልናል
አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው) አል ዙመር 62
ከአላህ ሌላ ሲሳይ የሚሰጥ የለም። ይህንን በማስመልከት
አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለም ሲሳይ አላህ ዘንድ ያለ ቢሆን እንጂ:: ሁድ 6
ከአላህ ሌላ ነገሮችን የሚያስተናብር የለም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል
ነገርን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያስተናብራል:: አል-ሰጅዳህ 5
ከአላህ ሌላ ህያው ሊያደርግ እንዲሁም ሊገድል የሚችል የለም። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል
እርሱ ህያው ያደርጋል ይገላልም ወደርሱም ትመለሳላችሁ
ተውኒድ አል-ኡሉኒያህ
ይህ ተውኒድ አላህን በአምልኮት አንድ ማድረግ ነው። ይህም

በዱዓእ
በፍራቻ
በመመካት እና
እርዳታ በመጠየቅ ብቸኛ ማድረግ ነው።
ከአላህ ሌላ ማንንም አንለምንም።አላህ እሱን ብቻ መለመን እንዳለብን ሲነግረን እንዲህ ይላ፦
ጌታችሁም አለ! ለምኑኝ እቀበላችሁአለሁና
ከአላህ ሌላማንንም አንመካም።አላህ አማኞች በእርሱ ላይ ብቻ ሊመኩ እንደሚገባ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፦አማኞች እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ
ከአላህ ሌላ ፍጡራን በማይችሉት ጉዳይ ላይ እርዳታ ከአላህ ውጪ ከማንም አንጠይቅም ።ይህን በማስመልከት አላህ በሱረቱል ፋቲሃ ላይ ደጋግመን ምናነባቸው አንቀፆች አውርዷል።
አንተን ብቻ እናመልካለን ከአንተ ብቻ እርዳታ እንጠይቃለን።
ተውሂድ አል አስማዕ ወስሲፋት፦በቁርዓን እና ትክክለኛ በሆኑ የመልዕክተኛው ሀዲሶች ውስጥየመጡትን የአላህ ስሞች እና ባህሪያት ከማንም ስሞችና ባህሪያት ጋር ሳያመሳስሉ ፣ቃሉን ሳያዛቡ፣ ትርጉማቸውን ሳይለውጡ ወይም ሳያስተባብሉ ለአላህ እንደሚገቡ በማመን ማለት ነው። የአላህ (ሱ.ወ) ስሞች ብዙ ናቸው። ከነርሱም መካከል
አል-ራህማን
አል-ረሂም
አል-በሲር
አል-አዚዝ
አል-ሀኪም...........