Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነገሩ እንዴት ነው


በወንድማችን አቡ መርየም ሰሚ
ቢስሚላሂር-ራሕማኒር-ራሒም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም በመጨረሻው መልዕክተኛ ላይ
ይሁን በመቀጠልም: “አሽ-ሸሪዐቱ ወልሃያት” በሚል የአልጀዚራ ቲቪ ዝግጅት በ 03-04-2005 እ.አ.አ. ስለ የክርስትያኖቹ ቄስ የነበሩት ‘ባባ ቫቲካን’ ሕልፈተ-ሂወት አስመልክቶ ዶ/ር
ዩሱፍ አል-ቀርዳዊ እንዲህ አለ: “ለዚህ ‘ባባ’ ሓዘናችንን እንገልፃለን...... ለጥሩ ሰብአዊ ተግባራቱ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲያዝንለት እና ምንዳዉን እንዲከፍለው ከመለመን ዉጪ ምንም ማድረግ አንችልም..... አላህም ለክርስትያኒቷ ህዝብ የተሻለ እንዲያመጣላት እንጠይቀዋለን።”
ምላሽ: ዶ/ሩ ይህን ሰው አሞገሰ። ክርስትናን (ኩፍርን) የሚያስፋፋ ሰውን አሞገሰ። ሙስሊሞች ሃገር ላይ ክርስትናን የሚያስፋፋን ሰው አሞገሰ። ጭራሽ ሙገሳው እንዳይበቃው እንዲያዝንለት እና ምንዳውን እንዲከፍለው አላህን ጠየቀ። ከዛም አልፎ የተሻለ እንዲያመጣላቸው አላህን ጠየቀ። አላህም ሌላ “የተሻለ” ረሱልን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የሚሳደብ ባባ በተንክዶስ (በነዲክት)
የተባለ አመጣላቸው። ላ ኢላሃ ኢለላህ!!! ትኩረት ልሰጠው የፈልግኩበት ነጥብ “አላህ ሱብሓነሁ
ወተዓላ እንዲያዝንለት እና ምንዳዉን እንዲከፍለው ከመለመን ዉጪ ምንም ማድረግ አንችልም” የሚለውን ንግግር ነው። አላህን እና መልዕክተኛውን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የሚሳደቡ እና የሚጠሉ ብሎም በአላህ ላይ የሚያገሩ ከሃዲ ሰዎችን እንዴት ምህረት ይጠየቅላቸዋል??? በዶ/ሩ ቢያቆም እኮ እሺ። የቀድሞው የግብፅ መሪ የነበረው ሙሓመድ ሙርሲም እንደዛው ብልዋል። የክርስትያኖች ጳጳስ የነበሩት ባባ ሽኑዳህ ሲሞቱ የአላህን እዝነት ለመነ። ለነገሩ ኢኽዋኖ አንድ ናቸው።
ዋሸህ እንዳትሉኝ https://www.youtube.com/watch?v=5ifMoNVrTEg ይህን አንቀፅ የት እንውሰደው:
“ ﻟَﻘَﺪْ ﻛَﻔَﺮَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺛَﺎﻟِﺚُ ﺛَﻠَﺎﺛَﺔٍ ﻭَﻣَﺎ ﻣِﻦْ ﺇِﻟَﻪٍ ﺇِﻟَّﺎ ﺇِﻟَﻪٌ ﻭَﺍﺣِﺪٌ
ﻭَﺇِﻥْ ﻟَﻢْ ﻳَﻨْﺘَﻬُﻮﺍ ﻋَﻤَّﺎ ﻳَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﻟَﻴَﻤَﺴَّﻦَّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ ﻣِﻨْﻬُﻢْ ﻋَﺬَﺍﺏٌ ﺃَﻟِﻴﻢٌ ”
“እነዚያ አላህ የሶስት ሶስተኛ ነው ያሉ በርግጥ ካዱ። ከአምላክም አንድ አምላክ እንጅ ሌላ የለም። ከሚሉትም ነገር ባይከለከሉ ከነሱ እነዝያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በርግጥ ይነካቸዋል።” አል-ማኢዳህ - 73 ይሄንንስ:
ﺇِﻥَّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ ﻭَﻣَﺎﺗُﻮﺍ ﻭَﻫُﻢْ ﻛُﻔَّﺎﺭٌ ﺃُﻭﻟَٰﺌِﻚَ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻢْ ﻟَﻌْﻨَﺔُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﻟْﻤَﻠَﺎﺋِﻜَﺔِ
ﻭَﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﺃَﺟْﻤَﻌِﻴﻦَ ﺧَﺎﻟِﺪِﻳﻦَ ﻓِﻴﻬَﺎ ۖ ﻟَﺎ ﻳُﺨَﻔَّﻒُ ﻋَﻨْﻬُﻢُ ﺍﻟْﻌَﺬَﺍﺏُ ﻭَﻟَﺎ ﻫُﻢْ
ﻳُﻨﻈَﺮُﻭﻥَ
እነዚያ የካዱ እነርሱ ከሐዲዎች ኾነውም የሞቱ እነዚያ በነርሱ ላይ የአላህና የመላእክት የሰዎችም ሁሉ እርግማን አለባቸው፡፡ በውስጧ (በርግማንዋ ውስጥ) ሁልጊዜ ዘውታሪዎች ሲኾኑ ቅጣቱ ከነሱ አይቀለልም እነርሱም አይቅቆዩም (ጊዜ አይስሰጡም)፡፡ (አል-በቀራህ-161) ይሄንንስ:
ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ ﻟَﻬُﻢْ ﻧَﺎﺭُ ﺟَﻬَﻨَّﻢَ ﻟَﺎ ﻳُﻘْﻀَﻰٰ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻢْ ﻓَﻴَﻤُﻮﺗُﻮﺍ ﻭَﻟَﺎ ﻳُﺨَﻔَّﻒُ
ﻋَﻨْﻬُﻢ ﻣِّﻦْ ﻋَﺬَﺍﺑِﻬَﺎ ۚ ﻛَﺬَٰﻟِﻚَ ﻧَﺠْﺰِﻱ ﻛُﻞَّ ﻛَﻔُﻮﺭٍ ﻭَﻫُﻢْ ﻳَﺼْﻄَﺮِﺧُﻮﻥَ ﻓِﻴﻬَﺎ ﺭَﺑَّﻨَﺎ
ﺃَﺧْﺮِﺟْﻨَﺎ ﻧَﻌْﻤَﻞْ ﺻَﺎﻟِﺤًﺎ ﻏَﻴْﺮَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻛُﻨَّﺎ ﻧَﻌْﻤَﻞُ ۚ ﺃَﻭَﻟَﻢْ ﻧُﻌَﻤِّﺮْﻛُﻢ ﻣَّﺎ ﻳَﺘَﺬَﻛَّﺮُ
ﻓِﻴﻪِ ﻣَﻦ ﺗَﺬَﻛَّﺮَ ﻭَﺟَﺎﺀَﻛُﻢُ ﺍﻟﻨَّﺬِﻳﺮُ ۖ ﻓَﺬُﻭﻗُﻮﺍ ﻓَﻤَﺎ ﻟِﻠﻈَّﺎﻟِﻤِﻴﻦَ ﻣِﻦ ﻧَّﺼِﻴﺮٍ
እነዚያ የካዱትም ለእነርሱ የገሀነም እሳት አልላቸው፡፡ ይሞቱ ዘንድ በእነርሱ ላይ (በሞት) አይፈረድም፡፡ ከቅጣቷም ከእነርሱ አይቀለልላቸውም፡፡ እንደዚሁ ከሓዲን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ እነርሱም በርሷ ውስጥ እርዳታን በመፈለግ በኀይል ይጮሃሉ፡፡ «ጌታችን ሆይ! ከእዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላ በጎ ሥራን እንሠራ ዘንድ አውጣን» (ይላሉ)፡፡ «በእርሱ ውስጥ ያስታወሰ ሰው
የሚገሰጽበትን ዕድሜ አላቆየናችሁምን? አስጠንቃቂውም መጥቶላችኋል (አስተባብላችኋልም)፡፡ ስለዚህ ቅመሱ፡፡ ለበደለኞችም ምንም ረዳት የላቸውም» (ይባላሉ)፡፡
ﻫُﻮَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺟَﻌَﻠَﻜُﻢْ ﺧَﻠَﺎﺋِﻒَ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ۚ ﻓَﻤَﻦ ﻛَﻔَﺮَ ﻓَﻌَﻠَﻴْﻪِ ﻛُﻔْﺮُﻩُ ۖ ﻭَﻟَﺎ
ﻳَﺰِﻳﺪُ ﺍﻟْﻜَﺎﻓِﺮِﻳﻦَ ﻛُﻔْﺮُﻫُﻢْ ﻋِﻨﺪَ ﺭَﺑِّﻬِﻢْ ﺇِﻟَّﺎ ﻣَﻘْﺘًﺎ ۖ ﻭَﻟَﺎ ﻳَﺰِﻳﺪُ ﺍﻟْﻜَﺎﻓِﺮِﻳﻦَ ﻛُﻔْﺮُﻫُﻢْ
ﺇِﻟَّﺎ ﺧَﺴَﺎﺭًﺍ
እርሱ ያ በምድር ውስጥ ምትኮች ያደረጋችሁ ነው፡፡ የካደም ሰው ክህደቱ በእርሱው ላይ ብቻ ነው፡፡
ከሓዲዎችንም ክሕደታቸው ከጌታቸው ዘንድ መጠላትን እንጂ ሌላ አይጨመርላቸውም፡፡ ከሓዲዎችንም ክሕደታቸው ከሳራን እንጂ አይጨምርላቸውም፡፡
.
.
.
መደርደር ይቻላል። አይደለም ባባ ቫቲካን አቡ ጣሊብ (የረሱል ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም አጎት) እንኳ ምህረት እንዳይጠየቅለትየቁርአን አንቀፅ ወርዷል በረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጊዜ። አቡ ጣሊብ እንኳ ረሱልን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ረድቷል፣ አግዟል፣ ተንከባክቧል አይደለም እስልምናን
ሊጎዳ። ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ለአጎታቸው “በአላህ ይሁንብኝ! እስካልተከለከልኩ ድረስ ምህረት እጠይቅልሃለሁ” ባሉ ጊዜ አላህ ከታች ያለቿን አንቀፅ
አወረደ።
ﻣَﺎ ﻛَﺎﻥَ ﻟِﻠﻨَّﺒِﻲِّ ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺃَﻥْ ﻳَﺴْﺘَﻐْﻔِﺮُﻭﺍ ﻟِﻠْﻤُﺸْﺮِﻛِﻴﻦَ ﻭَﻟَﻮْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ
ﺃُﻭﻟِﻲ ﻗُﺮْﺑَﻰ ﻣِﻦْ ﺑَﻌْﺪِ ﻣَﺎ ﺗَﺒَﻴَّﻦَ ﻟَﻬُﻢْ ﺃَﻧَّﻬُﻢْ ﺃَﺻْﺤَﺎﺏُ ﺍﻟْﺠَﺤِﻴﻢِ ( 113 )
{ለነቢዩ እና ለነዛ ላመኑት ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶችቢኾኑም እንኳ እነሱ (ከሃዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መኾናቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ምሕረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም} አት-ተውባ - 113
እስቲ አስረዱን በመረጃ

Post a Comment

0 Comments