Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሱናን መያዝ ማለት ሰዎችን በጭፍን መከተል ማለት አይደለም፡፡

ሱናን መያዝ ማለት ሰዎችን በጭፍን መከተል ማለት አይደለም፡፡ ግዴታ እነ እገሌ ፍቃድ ያልሰጡት ችግር አለበት የሚባል ሱና የለም ቡድንተኝነት እንጂ፡፡ ኡለማዎች በሱና ላይ መሰባሰብ ስኬት ነው ያሉት በሱና ላይ ስለመሰባሰብ እንጂ በቡድንተኝነት ላይ አይደለም፡፡ የሱናን ዳእዋ ለማድረግ አንድ ሰው ከሱና ኡለሞች እስከተማረ ድረስ እነ ኡስታዝ እንትና ጋር አልቀራም ወይንም ፍቃድ አላገኘም የነሱን ይሁንታ ስላላገኝ ችግር አለበት አይባልም፤ ይሄ የቡድንተኝነት አካሄድ ነው፡፡ ችግር ያለበት ሰው ችግሩ በማስረጃ ተጠቅሶ ይነገራል፡፡ ሸሪዓዊ ማስረጃን ጥሶ የተገኘ ማንም ይሁን ማን መልስ ይሰጥበታል፡፡ የሱና ሰዎች ልክ እንደ ሱፍዩች ‹‹ለሸይህህ ልክ ጀናዛ ለአጣቢው እንደሚሆነው ሁንለት፤ ሸሆቼ የገቡበት እገባለሁ›› የሚባል አባባል የላቸውም፡፡ ሸህም ይሁን ኡስታዝ ብሎም ሙፍቲ ከማስረጃ ሲወጣ መልስ ይሰጠዋል፡፡ ማንም ሰው ንግግሩ ከማስረጃ ጋር ከሆነ እንቀበለዋለን፤ ከዛ ውጭ የሌለን ነገር እየፈጠረ በሱና፤ በሂክማ፤ ምክር እና ሌላም በሚል ስም ቢሰብክ አንሰማውም፤ አንቀበለውም፡፡ አላህ ከፍጡር ተከተሉት እሱን መታዘዝ እኔን እንደመታዘዝ ነው ያለላቸው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ብቻ ነው፡፡
አላህ ከቡድንተኝነት ይጠብቀን፤ እውቀትነ ከተቅዋ ጋር ይስጠን፤ በሱና ላይ ኖረው ወደ ሱና ተጣርተው፤ በዛ መንገድ ላይ ኖረው ከሚሞቱት ያድርገን፡፡