Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሸይኽ ፈውዛን (ሃፊዘሁላህ) ምክር ‹‹ሃውድን መጠጣት ከፈለግክ በመንሃጅ ላይ ቀጥ በል››

የሸይኽ ፈውዛን (ሃፊዘሁላህ) ምክር
=====================
‹‹ሃውድን መጠጣት ከፈለግክ በመንሃጅ ላይ ቀጥ በል››
ሸይኽ ፈውዛን፡ ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀውድ መጠጣት ከፈለግክ አላህ እና መልክተኛውን ታዘዝ፡፡ የሙሀመድ ኡመት ነኝ ብሎ ነገር ግን የመልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መንሀጅ የማይታዘዝ፤ የማይተገብር እና የማይከተል ይህ ሰው ኢስላም ከሚለው ስም አይጠቀመም፡፡ ይልቁንስ ሰዎች በተጠሙበት ሰዓት ሃውድን አይጠጣም አላህ ይጠብቀን እና፡፡
እናም ከዚህ ሀውድ መጠጣት የፈለገ ሱናን አጥብቆ ይያዝ (ይተግብር)፤ ሱናን አጥብቆ መያዝ ደግሞ ቀላል ነገር አይደለም፤ ፈተና እና መከራ አለው፡፡ የሚያነውሩህ፤ የሚያስቸግሩህ፤ ክብርህን የሚያጎድፉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡
‹‹ይሄ ሰው ፅንፈኛ፤ ጠርዘኛ፤ እናም ሌላም›› ይሉሃል፤ ወይንም በንግግር ብቻ ላያበቁ ይችላሉ ይገሉሃል፤ ወይንም ያስሩሃል፡፡
ነገር ግን ታገስ ደህንነትን እና ከሃውድ መጠጣትን ከፈለግክ፡፡ የአላህ መልክተኛን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀውድ ላይ እስክታገኝ ድረስ ሱናን በመያዝ ላይ ታገስ (ፅና)፡፡
ምንጭ
شرح الدّرة المضيّة في عقد أهل الفرقة المرضية