Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እምነትህን ጠብቅ ትምህርት ቁጥር 2 ተውሂዱ ሩቡቢያ

እምነትህን ጠብቅ
ትምህርት ቁጥር 2
ተውሂዱ ሩቡቢያ
ተውሂዱ ሩቡቢያ ማለት አላህ ብቸኛ ፈጣሪ ተቆጣጣሪና ንጉስ መሆኑን ህያው አድራጊ ገዳይ ሲሣይ ለጋሽ እሱ ብቻ እንደሆነና ባጠቃላይ በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ብቸኛ እንደሆነና አጋር እንደሌለው ማመን ማለት ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
خَلَقَ السَّمَاوَاتِ بِغَيْرِ عَمَدٍ تَرَوْنَهَا وَأَلْقَى فِي الْأَرْضِ رَوَاسِيَ أَنْ تَمِيدَ بِكُمْ وَبَثَّ فِيهَا مِنْ كُلِّ دَابَّةٍ وَأَنْزَلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَنْبَتْنَا فِيهَا مِنْ كُلِّ زَوْجٍ كَرِيمٍ هذا خَلْقُ اللَّهِ فَأَرُونِي مَاذَا خَلَقَ الَّذِينَ مِنْ دُونِهِ بَلِ الظَّالِمُونَ فِي ضَلَالٍ مُبِينٍ
‹‹ሰማያትን ያለምታዩዋት አዕማድ (ምሰሶዎች) ፈጠረ፡፡ በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ፡፡ በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በተነ፡፡ ከሰማይም ውሃን አወረድን፡፡ በእርሷም ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን፡፡ ይህ የአላህ ፍጡር ነው፡፡ እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ፡፡ በእውነቱ በዳዮቹ በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው፡፡
(ሉቅማን 1ዐ-11)
قُلْ أَرَأَيْتُمْ مَا تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ أَرُونِي مَاذَا خَلَقُوا مِنَ الْأَرْضِ أَمْ لَهُمْ شِرْكٌ فِي السَّمَاوَاتِ
“ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን አያችሁን? ከምድር ምንን እንደፈጠሩ አሳዩኝ፤ ወይም በሰማያት ለነሱ (ከአላህ ጋር) መጋራት አላቸውን?”
(አል አህቃፍ 4)
ይህ የተውሂድ ክፍል ከእምነት ክፍል ውስጥ አንዱ ቢሆንም አንድ ሰው ይህንን ብቻ በማመኑ በአላህ አመነ አይባልም እንዲያውም በነብዩ ላይ ጦርነት የከፈቱ አጋሪዎች በዚህኛው የተውሂድ ክፍል ያምኑ እንደነበር አላህ በብዙ የቁርዓን አንቀፆች ገልጿል፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَلَئِنْ سَأَلْتَهُمْ مَنْ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَسَخَّرَ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ لَيَقُولُنَّ اللَّهُ فَأَنَّى يُؤْفَكُونَ
‹‹ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይሉሃል፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ፡፡
(አንከቡት 61)
وَلَئِنْ سَأَلْتَهُمْ مَنْ نَزَّلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَحْيَا بِهِ الْأَرْضَ مِنْ بَعْدِ مَوْتِهَا لَيَقُولُنَّ اللَّهُ قُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْقِلُونَ
‹‹ከሰማይም ውሃን ያወረደና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደረጋት ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ምስጋና ለአላህ ነው» በላቸው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
(አንከቡት 63)
وَلَئِنْ سَأَلْتَهُمْ مَنْ خَلَقَهُمْ لَيَقُولُنَّ اللَّهُ فَأَنَّى يُؤْفَكُونَ
‹‹ማን እንደፈጠራቸውም ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይላሉ፡፡ ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ይዞራሉ፡፡
(ዙኽሩፍ 87)
«ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ብትኾኑ (ንገሩኝ)» በላቸው፡፡ በእርግጥ ‹‹የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ታዲያ አትገሰጹም ፡፡ የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው? «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ እንግዲያ አትፈሩትምን፡፡ የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው፡፡ በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው፡፡
(አል ሙእሚኑን 84-89)
ከዚህ የምንረዳው በተውሂዱ ሩቡቢያህ ማመን ብቻ አንድን ሰው ከቅጣት እንደማያድነው እና ሙስሊምም እንደማያሰኘው ነው፡፡ ስለዚህ በአላህ አማኝ ሙስሊም ለመሆን አምልኮን ለአላህ ብቻ በማድረግ በአምልኮው ላይ ከማጋራት መጠንቀቅ ግዴታ ነው::
የዳዕዋ አቅጣጫችንም ሊያተኩር የሚገባው ወደ አላህ ብቸኛ ፈጣሪነትና ረዛቂነት ሳይሆን ወደ ብቸኛ ተመላኪነት መሆን ይገባዋል!!!
አላህ ያግዘን!!!
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት…
http://www.facebook.com/emnetihintebiq
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!